Quantcast
Channel: ርዕሰ አንቀጽ
Viewing all 290 articles
Browse latest View live

‹‹ከማኅበር ወጥተን ፌዴሬሽን መሆናችን እንደ አገር እያሰብን እንደ አገር እንድንሠራ ያስችለናል››

$
0
0

  አቶ ፍትሕ ወልደሰንበት፣ የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት

አቶ ፍትሕ ወልደሰንበት በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ማስተርስ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፣ በUSAID/IQPEP ኃላፊ ሠርተዋል፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ የዞን አምስት ሲሆኑ የውድድር ዝግጅት ኮሚሽነር፣ የባለ አራት ኮከቡ የሴንትራል ሐዋሳ ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅና የሐዋሳ ከተማና አሁን በአዲስ የተመሠረተውን የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ለብዙ ዓመታት ማኅበር ሆኖ የቆየውና በቅርቡ ወደ ፌዴሬሽን ያደገውን የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎችና በተያያዥ ጉዳዮች እንዲሁም ወደፊት ፌዴሬሽኑ ምን ሊሠራ እንዳቀደ ታምራት ጌታቸውአቶ ፍትሕን  አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የኢትዮጵያ ሆቴሎች ማኅበር መቼ ተመሠረተ? ምን ዓላማ በማድረግ ነበር የተመሠረተው?

አቶ ፍትሕ፡-በኢትዮጵያ እንደ ሌሎች ማኅበር ምስረታ ሁሉ ዓላማው በሆቴል ኢንዱስትሪ ያለውን ሁኔታ አንድ በመሆን ችግር ቢመጣ ለመቋቋምና እርስ በርስ ለመረዳዳት በ1967 ታሪክ እንደሚያስረዳው 17 የሚሆኑ በታሪክ የሆቴል ባለቤቶች ነበር የተመሠረተው፡፡ በወቅቱ ስሙ የኢትዮጵያ ሆቴል አሠሪዎች ማኅበር ይባል እንጂ ሆቴሎች በብዛት የነበሩት አዲስ አበባ ውስጥ ስለነበሩ ማኅበሩም አገልግሎቱ በዚሁ አካባቢ የተወሰነ ነበር፡፡ በወቅቱ ነፃ ገበያ ስላልነበር መንግሥት የወሰነውን ዋጋ በመደራደር እንዲያሻሸል በማድረግ ብዙ ችግሮችን በመቋቋምና በመፍታት በቅርቡ እንደ አዲስ በ2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎች ማኅበር ተብሎ እስከተቋቋመበት ድረስ አንጋፋ ማኅበር ሆኖ ነበር የቀጠለው፡፡

ሪፖርተር፡- እንደ አዲስ ለማቋቋም ለምን አስፈለገ? መሰል አገልግሎት ሰጪ የሚባሉትስ እነማን ናቸው?

አቶ ፍትሕ፡- የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎች ማኅበር ብለን ከስድስት ወር በፊት ነበር እንደ አዲስ የተመሠረተው፡፡ በቅርቡ ደግሞ ፌዴሬሽን እስከሆነበት ድረስ ከስሙ ስንጀምር ዛሬ የሆቴሎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን ከእነሱ ጋር የሚሠሩ ካምፓኒዎች ቁጥር መብዛታቸውና ተደራሽነቱም በየክልሉ በማድረግ እንደ አገር በማሰብ ለአገር ለመሥራት ነው፡፡ ሌላው መሰል የሚባሉት ደግሞ አስጎብኚዎች ሱፐር ማርኬቶች፣ የመኪና አከራዮች፣ የጉዞ ወኪሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ሎጆች፣ የሆቴል ዕቃ አቅራቢዎችና ሌሎችም እነዚህ ማለት አንድ ቱሪስት ሲመጣ ከአየር መንገድ ጀምሮ ሆቴል፣ ለጉብኝት፣ ዕቃ የሚገዙበት ሱፐርማርኬትና የሚንቀሳቀስበት መኪና ሁሉም ማለት ይቻላል፡፡ ከሆቴል ኢንዱስትሪ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ቁርኝት ያላቸው ናቸው፡፡ ከእነሱ ጋር ማኅበር መመሥረት ኢንዱስትሪውን ከማሳደግ ባሻገር በተበጣጠሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር የነበረው ግንኙነት በአንድ ድምፅ ለማሰማትም ይሁን ለመደራደር የተሻለ ስለሚሆን ነው ትልቁ ምስል ደግሞ የቱሪዝሙን ዕድገት ስለሚያቀላጥፈው ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም በአንድ ስለሚገኙ፣ አገልግሎት ለማግኘት ደንበኛው ሳይንገላታ መገልገል ይችላል፡፡ ብዙ ሒደት ውስጥ ደግሞ ልምድ ልውውጥ ይኖራል፡፡  ሥራዎች እንዳይደራረቡ ይረዳል፣ በማናቸውም ሥራ ላይ የአገልግሎት አሳጣጥ ችግር ቢኖር ተጠያቂነቱም ችግሩንም ወዲያው ለመፍታት ቀላል ነው፡፡ በአጠቃላይ የነዚህ በአንድ ላይ መጣመር በኢንዱስትሪው ትልቅ ለውጥ ያመጣል ብለን በማሰብ ነው እንደ አዲስ ፌዴሬሽኑ እንዲመሠረት ያሰብነው፡፡

ሪፖርተር፡- ማኅበሩ ወደ ፌዴሬሽን አድጓል፡፡ ምንድነው ልዩነቱ ማኅበሩ አይበቃም?

አቶ ፍትሕ፡- ማኅበር ማለት በቅርበት ያሉ ሰዎች የሚያቋቁሙት ነው፡፡ አገልግሎታቸውም በዛው ቦታ የሚወሰን ነው፡፡ ፌዴሬሽን ማለት ደግሞ የማኅበሮች ስብስብና እንደማኅበር ሳይሆን የሚታሰበው እንደ አገር ነው ችግሮችን ለመፍታት፣ ለመቋቋም፣ ከመንግሥት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ፌዴሬሽን ትልቅ ድምፅና አቅም ይኖረዋል፡፡ በእነዚህና በመሰል ምክንያቶች እነዚህን ማኅበር ወደ ፌዴሬሽን ማሳደግ ትልቅ ጥቅም ነው ያለው፡፡ የኢትዮጵያ ሕግም በተመሳሳይ ሥራ የተሰማሩ ማኅበሮች ወደ ፌዴሬሽን እንዲያድጉ ከዛም ፌዴሬሽኖች ወደ ኮንፌዴሬሽን እንዲያድጉ ይደነግጋለ፡፡ ስለዚህ የእኛም ፌዴሬሽን በማደጉ በመላው ኢትዮጵያ በመንቀሳቀስ መሥራት ያስችለዋል፡፡ ይህም ከአገር ውስጥና ብልጭ ካሉ አቻ ፌዴሬሽኖች በመገናኘት በየቀኑ የሚያድገውን የሆቴል ኢንዱስትሪ ልምድ በመለዋወጥ የአገራችንን የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎች እኩል ማራመድ ያስችለናል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ከመንግሥት ጋር ኢንዱስትሪውን በተመለከተ ለሚወጡ ፖሊሲዎችና በተለያዩ ጉዳዮች ይማከራል፣ ይደራደራል፣ የአባላቱን ጥቅም ያስከብራል ማለት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በምን ያህል ማኅበራቶች ነው ፌዴሬሽን መሆን የቻለው? ምን ያህል ሠራተኛ ይዟል?

አቶ ፍትሕ፡-ፌዴሬሽኑ የተመሠረተው 13 በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የሆቴል የሪዞርት እንዲሁም መሰል አገልግሎት ሰጪ ማኅበራቶች ነው፡፡ አንዱ ማኅበር በስሩ ምናልባት 20 ሆቴሎችን አንዱ ደግሞ 50 ተቋማትትን ለሌሎች የተለያየ ቁጥር የያዙ አሉ፡፡ በእነዚህ ውስጥ ደግሞ በትንሹ አንዱ ሆቴል ወይም ተቋም ከ30 እስከ 300 የሚደርሱ  ሠራተኞችን ይይዛሉ፡፡ ገና መጠይቅ ልከን እየጠበቅን ቢሆንም በሥራቸው በርካታ ሠራተኛ እንደሚንቀሳቀሱ ይገመታል፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ ፌዴሬሽኑ ለመግባት የግድ በማኅበር መሆን አለበት?

አቶ ፍትሕ፡- በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለ እንደ ማኅበርም እንደ ግለሰብም መግባት ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- ከዚህ በፊት የአሠሪዎች ማኅበርም ይሁን ፌዴሬሽን በሆቴል በኩል ሠራተኛን ያለማደራጀት ችግር እንዲሁም ቋሚ የሥራ ዕድል የመንፈግ ሁኔታዎች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ እንደማሳያ በሁለት ትላልቅ ሆቴሎች የተጠረ አለመግባባት በፍርድ ቤት የታየበት ጊዜ ነበር፡፡ አዲሱ ፌዴሬሽን ይህንን ችግር እንዴት ሊፈታው ተዘጋጅቷል፡፡ ሠራተኛስ ተበድያለሁ ብሎ ወደእናንተ መምጣት ይችላል?

አቶ ፍትሕ፡- አዲሱ ፌዴሬሽን የመጀመሪያ ሥራው የሚሆነው ከዚህ በኋላ የተለመደ አሠራሮችን በማስቀረት የሆቴል አሠሪን ማብቃት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕግ በአብዛኛው ወደ ሠራተኛው ነው የሚደለው ይህም በአሠሪው ላይ ጫናን ያመጣል፡፡ የሠራተኛ ማኅበራትን እንዳይቋቋሙ የሚከለክለውም ምናልባት በዚህ ምክንያት ይመስለኛል እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ሲመጡበትም በእጅ ወይም በጠበቀ ነው ለመከላከል የሚሞክረው በአብዛኛው የአሠሪው አዋጅን ምን እንደሚል ብዙም ግንዛቤ የለውም፡፡ በዚህም መብቱንና ግዴታውን ለመውጣትም ይቸግረዋል፡፡ በእነዚህ ምክንያት ሁሌ ጭቅጭቅ ይፈጠራል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትም የአሠሪ መብትና ግዴታው የሠራተኛው መብትና ግዴታው የሚለውን ጨምሮ የሠራተኛ ማኅበር ቢያቋቋሙ ሁለቱም እንዴት እንደሚጠቀሙ ለአባሎቻችን ትምህርት በመስጠት ችግሩ የሚቀርፈው ይመስለኛል፡፡ ሌላው ሥራው ቀጥይነት እስካለውና 45 ቀን ከሞላው አንድ ሠራተኛ ምንም ክርክር የለውም በነጋታው ቋሚ የማድረግ የሆቴል ባለቤቱ ግዴታ ነው፡፡ ይህን ባያደርግ ሕጉ አይደግፈውም፡፡ ይህም ከዕውቀት ማነስ የሚፈጠር በመሆኑ ለዚህም ትምህርት በመስጠት የሚስተካከልበትን መንገድ አቅደናል፡፡ አንድ ሠራተኛ ወይም የሠራተኛ ማኅበር በአሠሪዬ እንደዚህ ዓይነት በደል ወይም የሕግ ጥሰት ተፈጽሞብኛል ካለ ጉዳዩን ወደ ፌዴሬሽኑ ማምጣት ሙሉ መብት አለው፡፡

ሪፖርተር፡- በዚህ ሒደት ውስጥ ያጋጠሟችሁ ችግሮች ምንድናቸው?

አቶ ፍትሕ፡- ከተቋቋመ ገና አጭር ጊዜ በመሆኑም የጎላ ችግሮች አላጋጠሙንም፡፡ አንዳንድ ሆቴሎች ወደ ፌዴሬሽኑን ለመቀላቀል ከመዘግየት በስተቀር፡፡ መንግሥትም ጥሩ እያገዘን ነው ያለው፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ አርስዎ የሚመሩት ፌዴሬሽን ግዙፍና በውስጡም በርካታ የሰው ኃይል ያለበት ነው፡፡ ወደፊትም ትላልቅ ብራንድ ያላቸው ሆቴሎች እየመጡ ነው፡፡ እንዲሁም መሰል ተቋማ ኢንዱስትሪውን ሰላማዊ ለማድረግ ወደፊት ምን አስቧል?

አቶ ፍትሕ፡- ይህ እኛ ብቻችንን የምንሠራው ሥራ አይደለም፡፡ የእኛን ጉዳይ ከሚመለከተው ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጀምሮ ባህልና ቱሪዝም የሠራተኛ ኮንፌዴሬሽን በርካታ ከኢንዱስትሪው ጋር የተያያዙ በመተጋገዝ፣ በመተባበር፣ የምንፈጽመው ጉዳይ ነው፡፡ በኛ በኩል እንደ ፌዴሬሽን የሚሠራቸው በርካታ ሥራዎች ይኖራሉ፡፡ የአሠሪውን መብት ክማስጠበቅ ጀምሮ አንዳንድ ሕጎች እንዲሻሻሉና አዳዲስ እንዲወጡ በማድረግ ቀጣይ በኢንዱስትሪው ለመሳተፍ የሚመጣ ማንኛውም አካል ምንም ችግር ሳይገጥመው መሥራት እንዲችል ማድረግ ነው፡፡ ከአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለፈ ሥራውን የሚያሻሽልበትና ደረጃ የሚጠብቅበትንና አገራችንን እንዴት የቱሪዝም መዳረሻ እናድርጋት? ብሎ እንዲያስብ ማስተባበርና ሥልጠና መስጠትም የኛ ሥራ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ ሰሞኑን በተከሰተው ሁከት የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጎድቷል፡፡ አንዳንድ ሆቴሎችም ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ለነዚህ ምን እያደረገ ነው?

አቶ ፍትሕ፡- ችግሩ የተከሰተው እኛ ማኅበራችንን ወደ ፌዴሬሽን ገና እያቋቋምን ባለበት ወቅት ቢሆንም ዝም ብለን ቁጭ አላልንም፡፡ የተጎዱ ሆቴሎችን የጉዳታቸውን መጠን መረጃ እያሰባሰብን ነው ያልነው፡፡ ይህንን በማጠናከር ወደ ባህልና ቱሪዝም በመላክ ከሚመለከተው ጋር ስለወደፊቱና ስላለፈው መነጋገርና የመፍትሔ ሐሳቦችን ማስቀመጥ ነው፡፡

Standard (Image)

‹‹ኢትዮጵያ ሳይንቲስት የሚሆኑ ታዳጊዎች አሏት››

$
0
0

ዶ/ር ኮሎኔል ዓለማየሁ ገ/እግዚአብሔር፣ የእስቴም ሲነርጂ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር

ዶ/ር ኮሎኔል ዓለማየሁ ገ/እግዚአብሔር የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባል ነበሩ፡፡ ከሕንድ በሲስተምስ ኤንድ ኮንትሮልንግ ኢንጅነሪንግ የፒኤችዲ ዲግሪ አላቸው፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ የሠራ ዘመናቸውን በመከላከያ ያሳለፉት ኮሎኔል ዓለማየሁ የመከላከያ ኢንጀነሪንግ ኮሌጅ ሲደራጅ በመምህርነት፣ በዲቪዥን ኃላፊነትና ዲንነት አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም በተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ሆነው ዳርፉር በማቅናት ግዴታቸውን መወጣት ችለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የእስቴም ሲነርጂ (Stem Synergy) አገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ድርጅት ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ እስቴም ሲነርጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎችን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ማቲማቲክስ በማሠልጠን በኢትዮጵያ የሳይንስ ማዕከል ለማቋቋም በማቀድ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበርና የሳይንስ ማዕከላትን በመክፈት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎቹና በሳይንስ ማዕከላቱ ያለውን የተማሪዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት እንቅስቃሴ በተመለከተ ዳዊትቶሎሳከዶ/ር ኮሎኔል ዓለማየሁ ገ/እግዚአብሔር ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ የእስቴም ሲነርጂ የሳይንስ ፕሮግራም እንዴት ተጀመረ?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- የእስቴም ሲነርጂና የድጋፍ አድራጊው ዋና ዓላማ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የሚሠሩ ሥራዎች ለወጣቶች በማስተማር ኢንጂነሮችና ሳይንቲስቶች መፍጠር ነው፡፡ የእስቴም ሲነርጂ ፕሮግራም የጀመረው ሚስተር ማርክ ግልፈንድ የተባለ አሜሪካዊ በሌላ የሥራ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት አጋጣሚ ነው፡፡ በአገሪቷ ውስጥ ያሉትን ወጣቶች የሳይንስ ክህሎት በመመልከት የተለየ ድጋፍ ቢደረግላቸው ከፍተኛ ውጤት ሊመጣ እንደሚችል በማመን ፕሮግራሙ ተጀምሯል፡፡ ቀደም ብሎ ግን መነሻ የነበረው ከጐንደርና ከትግራይ አካባቢ ወደ እስራኤል አምርተው የሚኖሩ ወጣት ልጆች በሳይንስ ላይ ያላቸውን ችሎታ ሲመለከት በኢትዮጵያም ድጋፍ ከተደረገላቸው የተሻለ ነገር መሠራት የሚችሉ ወጣቶች እንደሚገኙ በማመኑ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ መጥቶ የቢሾፍቱ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅን ተመልክቶ ከእኔ ጋር በመወያየት፣ በኢትዮጵያ የሳይንስ ማዕከል መክፈት እንደሚፈልግ ገለጸልኝ፡፡ ከዛም በመከላከያ ኮሌጅ ውስጥ ያሉትን ላብራቶሪዎች ከተመለከተ በኋላ በቢሾፍቱ የሳይንስ ማዕከል ለማቋቋም ወሰነ፡፡ በተጨማሪም ከሌሎች አካላት ጋር በመነጋገር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በቢሾፍቱ ከተማ የፎቃ የሳይንስ ትምህርት ማዕከል እንዲመሠረት አደረገ፡፡

ሪፖርተር፡- ማዕከሉ ከተመሠረተ በኋላ በሥሩ የሚሠለጥኑ ተማሪዎችን ለማስተማር መምህራን እንዴት ማግኘት ተቻለ? የናንተስ ድጋፍ ምን ይመስል ነበር?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- ከዚህ ቀደም በመከላከያ ኮሌጅ ለረጅም ዓመታት ልምድ ያላቸው ግን የጡረታ ጊዜያቸው የደረሰ አስተማሪዎች ነበሩ፡፡ እነሱን ቀጥታ ወደ ሥራው ማስገባት ተቻለ፡፡ እኔም በሐሳብ ደረጃ ድጋፍ ሳደርግ ነበር፡፡ የላብራቶሪ መምህር የሆኑትም እንዲሁ በሌሎችም የሳይንስ ማዕከላት የነበሩ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የእስቴም ሲነርጂ የሳይንስ ማዕከላትንና ችሎታ ያላቸውን ወጣት ተማሪዎችን ከማፍራት አንጻር ከቢሾፍቱ ውጪ በሌሎች ክልሎች ለማስፋፋት የተከናወነ እንቅስቃሴ አለ?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- ቢሾፍቱ ከሚገኘው የፎቃ የሳይንስ ማዕከል በተጨማሪ በተለያዩ ክልሎች መስፋፋት አለበት በሚል መነሻ ቁጥራቸው 13 ማድረስ ተችሏል፡፡ ባህርዳር፣ አክሱም፣ ሐዋሳ፣ ጐንደርና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚዎች ሲሆኑ፣ በወለጋ፣ ሰመራ ጅግጅጋና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎችም በሰፊው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ በዩኒቨርሲቲዎቹ አማካይነት ክረምት ላይ በፊዚክስ፣ ሒሳብ፣ አይቲ፣ ኬሚስትሪና በባዮሎጂ የአንደኛ ደረጃና ከዛ በላይ ያሉ ተማሪዎችን በመቀበልና የዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪዎችንና መምህራንን በመጠቀም ወጣቶች እንዲሠለጥኑ ይደረጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡና ከፍተኛ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎች በየአካባቢው በየደረጃቸው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች የመማር ዕድሉን እኩል እንዲያገኙ ምን ዓይነት ዘዴ ነው የተቀመጠው?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- ቀደም ብሎ ታቅዶ የነበረው አካባቢያቸው ባለው የሳይንስ ክበብ ላይ የተደራጁ ልጆችን መርጦ መውሰድ ነበር፡፡ ከዛ በኋላ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር ተወያይተን የተለያዩ ድጋፎች ማለትም የመኝታ፣ የምግብ እንዲሁም የአይቲ አቅርቦት ከተሟላላቸው ለምን በተወሰኑ ክልሎች ብቻ ይሰጣል? በሚል ሐሳብ ከትግራይና ከአፋር እንዲሁም ከሌሎች ክልሎች ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ተማሪዎችን መልምለው ቦታው ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ዕድሉን እንዲያገኙ ተደረገ፡፡

ሪፖርተር፡- በሳይንስ ማዕከሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ከማስተማር ባሻገር በተጨማሪ የተሠራ ነገር አለ?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- ከሳይንስ ማዕከላቱ በተጨማሪ የሳይንስ ሙዚየሞችን መክፈት ሌላኛው ዕቅድ ነው፡፡ ለዚህም በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው ሙዚየም አንዱ ተጠቃሽ ነው፡፡ በቀጣይ ግን ከዕርዳታ አድራጊው አካል ጋር በመሆን ወደፊት ለማስፋፋት ታስቧል፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎች ተምረው ብቻ ራሳቸውን የሚመዝኑበት ዕድል ሊፈጠርላቸው ይገባል፡፡ ለዚህም መንግሥት ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በኢትዮጵያ የሳይንስ ማዕከል እንዲስፋፋ ዕርዳታ እያደረገ የሚገኘው ሚስተር ማርክ ገልፋንድ፣ የተለያዩ ገንዘቦችን በማሰባሰብ ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ ሙዚየሞችን ለማስፋፋት እየሠራ ይገኛል፡፡

ሪፖርተር፡- ያሉትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከላት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በቀጣይ የታሰቡ ነገሮች አሉ?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- ባለፉት ስድስት ዓመታት ለተማሪዎቹ የተለያዩ መንገዶች ተመቻችቶላቸው በተወሰነ ደረጃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ የሳይንስ፣ የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪና የሒሳብ ሕጎችን እንዲቀስሙ ተደርገዋል፡፡ በተቃራኒው ግን ምንም እንኳ የሳይንስ ማዕከሎች ቢስፋፉም፣ እነዛን በአግባቡ ያልተጠቀሙ አሉ፡፡ አንዳንድ ቦታዎች እንዲያውም በመገልገያ ዕቃዎቹ ላይ ሲቆለፍባቸው ተስተውሏል፡፡ የተሻለ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ እንደ ቢሾፍቱ፣ ሐዋሳ፣ ባህርዳርና መቐለ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ቀሪዎቹ ግን መሥራት ያለባቸውን ያክል ሲሠሩ አይስተዋልም፡፡

ለዚህም መፍትሔ ይሆን ዘንድ የእስራኤልና ሩሲያ ልምድ በመቀመር የሳይንስ ተማሪዎችን ብቻ መልምለን ማስተማር የሚለው ሐሳብ ላይ ደርሰናል፡፡ የሳይንስ ማዕከል ካላቸውና በጥሩ ላብራቶሪና መምህር ማስተማርና በመካከላቸው ፉክክር እንዲፈጠር በማድረግ ውድድር ማዘጋጀት አንደኛው መንገድ ነው፡፡

ሁለተኛ መፍትሔ ደግሞ ከሩሲያ የወሰድነው በኮምፒተር የላቀ ደረጃ የደረሱ ልጆችን በመምረጥ በዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ዕውቀት ባላቸው መምህራን ማስተማር ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከትምህርት ቢሮና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገርና ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመተባበር በ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ (Science Sherd Campus) በሚል ስያሜ ተማሪዎችን በመሰብሰብ በወንድይራድ ትምህርት ቤትና ኮተቤ እንዲማሩ እየተደረገ ነው፡፡ ይህም በማርክ ግልፈንድ ለላብራቶሪና ለመምህራን ወጪ የሚሆን የ65 ሺሕ ዶላር ድጋፍ በማድረግ ተጀምሯል፡፡ በመጀመሪያ ዓመትም ብዙ ተማሪዎች ለመማር ተመዝግበው 90 ያህሉ ሥልጠናቸውን ጀምረዋል፡፡

ሪፖርተር፡- እስካሁን በተጓዛችሁበት መንገድ ውስጥ እንደ ችግር የሚነሳው ምንድነው?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- ምንም እንኳ የእስቴም ሲነርጂ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መሥረት ቢጀምርም የተለያዩ ክፍተቶች አሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎቹ ትኩረት በመስጠትና ተማሪዎችን በውጤታቸው መዝኖ በአግባቡ ሥልጠና ያለመስጠት አንዱ ክፍተት ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ከታች ካሉት ትምህርት ቤቶች ጋር ተቆራኝተው ያለመሥራት ችግርም አለ፡፡ በትምህርት ቢሮዎችም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም በአሠራር ግን መደገፍ አለበት፡፡ ምክንያቱም አንድ ዩኒቨርሲቲ በአግባቡ ከሠራ ሌላውም በዛው መንገድ መጓዝ አለበት፡፡ ቢያንስ ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ኮተቤው ትኩረት በመስጠት የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ዓይነት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እንዲሁም የሥርዓተ ትምህርቱ (ካሪኩለም) ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም የሳይንስ ትምህርት አሰጣጥ በሁሉም ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ያላችሁ ግንኙነት እምን ድረስ ነው?

ዶ/ር፡- ቀደም ብለን ስለሥራችን ነግረናቸው ነበር፡፡ እስቴም ሲነርጂ ራሱ በሳይንስ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሥር እንዲሆን ጥያቄም ብናቀርብም አልተሳካም፡፡ ሚኒስቴሩ በቀጣይ ተማሪዎች የሚማሩበትና ሙዚየምም ለመገንባት እንዳቀደ ሰምተናል፡፡ ቀደም ብሎ ባደረግነው ውድድርም 54 ላፕቶፖችን ለሽልማት አቅርቦልናል፡፡

ሪፖርተር፡- በቅርቡ ከሳይንስ ማዕከላትና ከተለያዩ ሥፍራዎች የተወጣጡ ወጣቶችን ያሳተፈ ውድድር አካሂዳችሁ ነበር፡፡ ምን ይመስል ነበር?

ዶ/ር ዓለማየሁ፡- ውድድሩ በአብዛኛው ከእስቴም ማዕከላትና ከሁሉም ክልሎች በተውጣጡ መካከል ሲደረግ ከ60 በላይ ፈጠራ ይዘው ቀርበውበታል፡፡ ይዘው ከቀረቡት ፕሮጄክቶች አንጻር ሁሉም መሸለም ይገባቸው የነበረ ቢሆንም ካሳዩት ብቃት አኳያ 15 ልጆችን ብቻ 15 ላፕቶፕ መሸለም ችለናል፡፡ ግን ዋናው በዚህ ትንሽ ድጋፍ 60 የፈጠራ ልጆችን ማግኘት ከተቻለ፣ የበለጠ መሠረት እንደሚቻል ያሳየን ውድድር ነው ማለት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ ሳይንቲስት የሚሆኑ ታዳጊዎች አሏት ማለትም ይቻላል፡፡    

Standard (Image)

‹‹አካል ጉዳተኞችን በልማት ለማካተት በመንግሥት መዋቅር መሄዱ ሥራዎችን ቀጣይ ያደርጋቸዋል››

$
0
0

አቶ ጌታቸው አበራ፣ የላይት ፎር ዘ ወርልድ ከፍተኛ ፕሮግራም ኦፊሰር

ላይት ፎር ዘ ወርልድ የሰባት አገሮች ማለትም የኦስትሪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ቤልጂየም፣ ኔዘርላንድስ፣ ጀርመንና ዩናይትድ ኪንግደም ስብስብ ሲሆን፣ ዋና ቢሮው ቬና ኦስትሪያ ይገኛል፡፡ አሜሪካ ደግሞ የላይት ፎር ዘ ወርልድ አባል ለመሆን በሒደት ላይ ትገኛለች፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በእስያና ምሥራቅ አውሮፓ ውስጥ በሚገኙ 15 አገሮች በአካል ጉዳተኝነትና በልማት ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው፡፡ ከ15ቱ አገሮች ኢትዮጵያ የፕሮግራም ቅድሚያ የተሰጣት አገር ስትሆን፣ ድርጅቱ ከሚሠራባቸው አገሮች ለ2016 ብቻ ከሰባት ሚሊዮን ዩሮ በላይ ዕርዳታ በማግኘት ከቀዳሚዎቹ ትመደባለች፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ፣ በሞዛምቢክ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በቡርኪናፋሶ ቢሮ ከፍቶ የሚሠራ ሲሆን፣ በኡጋንዳ በከፊል ይንቀሳቀሳል፡፡ ከትራኮማ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ዓይነ ስውርነትን በመከላከልና አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ትምህርት ለማዳረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራም ይገኛል፡፡ አቶ ጌታቸው አበራ የላይት ፎር ዘ ወርልድ የኢትዮጵያ ቢሮ ከፍተኛ ፕሮግራም ኦፊሰር ናቸው፡፡ በድርጅቱ ሥራዎች ዙሪያምሕረት ሞገስ አነጋግራቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡- ድርጅቱ ላይት ፎር ዘ ወርልድ የሚለውን ስም ይዞ ከመምጣቱ በፊት በኦስትሪያ ክሮቶፎር (ክርስቲያን) ብላይንድ ሚሽን (ሲቢኤም) በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ በወቅቱ ድርጅቱ ይሠራ ከነበረው የአሁኑ ላይት ፎር ዘ ወርልድ በምን ይለያል?

አቶ ጌታቸው፡-እ.ኤ.አ. በ1984 ሲቢኤም ኦስትሪያ ሲቋቋም የሚሠራው በቀጥታ ሳይሆን የሲቢኤም ዓለም አቀፍ ኔትወርክ አባል ሆኖ ነበር፡፡ በጀርመን ቤንሳይን የሚገኘው ዋና ቢሮ ዕርዳታ አሰባስቦ የዓይን ጤና ላይ ለሚሠሩ ፕሮጀክቶች እንዲውል ለሲቢኤም ዓለም አቀፍ ቢሮ በማስተላለፍ ይደግፉ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ፕሮጀክቶችን በአካል ተገኝቶ ለመገምገም እንዲሁም ከውጭ ዕርዳታ ለሚያደርጉ ፋውንዴሽኖችም ሆነ ግለሰቦች ወይም ሌሎች ገንዘባችሁ የዋለው እዚህ ነው ብሎ ለማሳየት አይቻልም ነበር፡፡ በመሆኑም ሲቢኤም ኦስትሪያ ባደረገው ጉባኤ ስም ለመቀየርና ራስን ችሎ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ከስምምነት በመደረሱ፣ እ.ኤ.አ. በ2004 ላይ ላይት ፎር ዘ ወርልድ ኦስትሪያ ተብሎ ተቋቋመ፡፡ ስያሜው ላይት ፎር ዘ ወርልድ ቢሆንም፣ የክርስቶፈር ብላይንድ ሚሽንን ፊሎሶፊ በመከተል ሥራው ይከናወናል፡፡ ክርቶፈል የዓይን ሐኪም ሲሆን፣ እንደሚሽነሪም በኢኮኖሚ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች እየተዘዋወረ ዓይነ ስውርነትን ለመከላከል ይሠራ ነበር፡፡ ላይት ፎር ዘ ወርልድም ከ2004 ጀምሮ ኦስትሪያ ቬና ላይ ሆኖ ፕሮጀቶክችን ይረዳ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የዕርዳታው መጠን እያደገ፣ ፕሮጀክቶችም እየበዙ ሲመጡ፣ ከርቀት ከመርዳትና ሥራዎችን ከመከታተል ይልቅ፣ በኢትዮጵያ ቢሮ ቢቋቋም የተሻለ ውጤት ማምጣት ይቻላል በሚል እ.ኤ.አ. በ2010፣ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ቢሮ ከፍቷል፡፡

ሪፖርተር፡- እርስዎ ቢሮውን በኢትዮጵያ ለመክፈት ከማማከር ጀምሮ እስካሁን በድርጀቱ ይሠራሉ፡፡ ምን ዓይነት ፕሮጀክቶችን ይዛችሁ ነው ሥራውን የጀመራችሁት?

አቶ ጌታቸው፡- በወቅቱ የዓይን ጤና፣ የማኅበረሰብ አቀፍ መልሶ ማቋቋም በተለይ አካል ጉዳተኝነትን ቀድሞ መከላከልና አካል ጉዳተኞችን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ስድስት ያህል ፕሮጀክቶች ነበሩን፡፡

ሪፖርተር፡- አሁን ምን ያህል ፕሮጀክቶች አሉ?

አቶ ጌታቸው፡-አሁን ላይ ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆኑ ፕሮግራሞችም አሉን፡፡ 32 ያህል የዓይን ጤና፣ ማኅበረሰብ አቀፍ መልሶ ማቋቋም እንዲሁም የአካቶ ልማት ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኒግሌክትድ ትሮፒካል ዲሲዝ (ኤንቲዲ) ላይ ሙሉ የትግራይ ክልልን እንዲሁም ምዕራብ ኦሮሚያን የሚሸፍን ፕሮግራም አለ፡፡ በዚህ ውስጥ ከጤና ቢሮ ጋር ተፈራርመን የምንሠራቸው ፕሮጀክቶች አሉ፡፡ ኤንቲዲ በ2014 ላይ ነው የተጀመረው፡፡ በ2016 ደግሞ የአካቶ ትምህርት ተጀምሯል፡፡ የአካቶ ትምህርት “One Class for all” ማለትም በአንድ ክፍል ሁሉንም ዓይነት ተማሪዎች ለማስተማር የሚያስችል አሠራር ለማስፈን እየተሠራ ነው፡፡ ይህ ትምህርት ለሁሉም ልጆች ማዳረስ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ አንድ ሕፃን የአካል ጉዳት ካለበት የትምህርት ዕድል ማጣት የለበትም፡፡ በኢትዮጵያ ከአሥር አካል ጉዳተኛ ሕፃናት ዘጠኙ አካላዊ ብቃታቸው ትምህርት ቤት ለመድረስ፣ ከደረሱ በኋላም ግቢው ለመግባትና በግቢው ያሉ መሠረተ ልማቶትን ለመጠቀም ባለመቻላቸው፣ በአካባቢያቸው ላይ ባለ አሉታዊ አመለካከት፣ በመምህሩ የሥልጠና ብቃት፣ በአቅም ማነስና በሌሎች ምክያቶች ከትምሀርት ቤት ይቀራሉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአካል ጉዳት ያለበት ሰው ከ15 እስከ 17 በመቶ ይደርሳል፡፡ ከዚህ ውስጥ ዋናውን ድርሻ የሚይዙት በመማር ዕድሜ ክልል ያሉ ናቸው፡፡ ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት በዓለም የአካል ጉዳተኝነትን 15 በመቶ ሲያደርገው፣ በኢትዮጵያ 17 በመቶ እንደሆነ አስፍሯል፡፡ ብዙውም በመማር ዕድሜ ክልል ላይ ያለ ከመሆኑ አንፃር፣ የተለያየ ዓይነት የአካል ጉዳት ያለባቸውን አካቶ ማስተማር ግድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ትምህርትን ለሁሉም ለማዳረስ ባላት ፖሊሲ መሠረት፣ አካል ጉዳተኞችን ካላካተትን ፖሊስውንም ሆነ ሁለተኛውን የሚሊኒየም ልማት ግብ ማሳካት አይቻልም፡፡ በመሆኑም አካቶ ትምህርት በአገሪቱ እንዲተገበር ከመንግሥት ጋር በመተባበር የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እናደርጋለን፡፡ የአካል ጉዳተኛውን አላካተትንም ማለት ኢኮኖሚውን ከመጉዳት ባለፈ የጉዳተኞቹም ሕይወት ያልተሻለ እንዲሆን መተው ነው፡፡ በአንድ ክፍል ሁሉንም ማስተማር የሚለውን የምንሠራው በአማራ ክልል፣ አዲስ አበባንና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የአካቶ ትምህርትን በምን ዓይነት መልኩ ነው የምትተገብሩት?

አቶ ጌታቸው፡- ላይት ፎር ዘ ወርልድ በራሱ ፕሮግራም አይተገብርም፡፡ ለአጋሮቻችን የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እንሰጣለን፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጽያ ቢሮ ስላለውም የፕሮጀክትና የፕሮግራም ትግበራን ሞኒተር እናደርጋለን፡፡ የአካቶ ትምህርትን ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር ስንሠራ፣ ያነጣጠርነው ሦስት ክልል ላይ ቢሆንም፣ በተግባር የጀመርነው በአማራና በደቡብ ክልሎች ነው፡፡ ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ስምምነት ተፈራርመን የክልሉን ትምህርት ቢሮ የሚደግፉ ባለሙያዎች ቀጥረናል፡፡ የመምህራን ሥልጠናንም እንደግፋለን፡፡ ከመምህራን ማሠልጠኛ ተቋማት ጋር ውል ተፈራርመን የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተሠራ ነው፡፡ ምክንያቱም አካቶ ትምህርት ልዩ ክህሎት ይፈልጋል፡፡ በምልክት፣ በብሬልና በሌሎችም አጠቃላይ ግንዛቤው እንዲኖር በኮሌጅ ደረጃ የመምህራን ሥልጠና አካል ሆኖ እንዲሰጥ ሥርዓተ ትምህርቱን በጋራ ለማሻሻል ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተደርጓል፡፡ የዚህ ፕሮግራም ባለቤትም ትምህርት ሚኒስቴር በመሆኑ እኛ ድጋፍ እናደርጋለን፡፡ የመምህራን ሥልጠናው የተጀመረ ሲሆን፣ ይህንን ቀጣይ ለማድረግ ሥርዓተ ትምህርቱ ላይ ወደፊት የምንሄድበት ነው፡፡ ከትምህርት ቤቶች ጋር በትምህርት ቢሮ አማካይነት ለመምህሩ የትምህርት ሥርዓቱ ሳይስተጓጎል የሥራ ላይ ሥልጠና መስጠትም የድጋፋችን አካል ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በመምህሩና በሥርዓተ ትምህርቱ በኩል ያሉ ክፍተቶችን በሥልጠናና በሙያ ስታግዙ፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው ልጆችን የሚያስተናግድ የትምህርት ቤት መሠረተ ልማቶች እንዲኖሩ የምታደርጉት እገዛ ምን ይመስላል?

አቶ ጌታቸው፡- የአካል ጉዳተኞች ትምህርት ክፍል፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቢሮዎች፣ መፀዳጃ ቤት መግባት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ መረማመጃዎች መገንባት አለባቸው፡፡ የአካል ጉዳተኞችን የሚያካትቱ የትምህርት ቤት መሠረተ ልማት ጅምር ያለባቸው ሥፍራዎች ላይ እያገዝን ነው፡፡ አጠቃላይ የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግም በሚሠሩ ሥራዎች ላይ እናግዛለን፡፡ የትምህርትና የሥልጠና መርጃ መሣሪያዎች ማቅረብና የመሳሰሉትን በማስፋፋት በአጠቃላይ አካቶውን ለማጎልበት በተለይ መንግሥታዊ ተቋማትን እያገዝን ነው፡፡ በዚህ የአካል ጉዳት ያለበት ልጅ ትምህርት ቤት እንዲገባ እየሠራን ነው፡፡ የዓይን፣ የመስማት፣ የመናገር፣ የመስማትና መናገር፣ የመራመድ ችግር ያለባቸውን፤ ሙሉ አካል አላቸው ከሚባሉት ጋር አካቶ ለማስተማር የመምህሩ ክህሎት ላይ ያተኮረ ሥልጠናንም እንደግፋለን፡፡

ሪፖርተር፡- ሙሉ አካል ያላቸውንና ሁሉንም ዓይነት የአካል ጉዳት ያለባቸውን አብሮ ለማስተማር የማስተማር ዘዴው ይለያያል፡፡ እዚህ ላይ ለመምህሩ የሚሰጠው ሥልጠና እንዴት ነው?

አቶ ጌታቸው፡- አንድ መምህር በክፍል ውስጥ የተለያየ ፍላጎትን ማስተናገድ አለበት ብለን እናምናለን፡፡ አሁን ላይ ያለው ልምድ የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች አራተኛ ክፍል እስከሚደርሱ  የተለየ ክፍል ተዘጋጅቶላቸው ማስተማር ነው፡፡ አምስተኛ ሲደርሱ ከሌሎች ጋር ይቀላቀላሉ፡፡ እስካሁን የአካል ጉዳት ያለባቸው ላለው የትምህርት አሠራር ነበር ራሳቸውን ሲያዘጋጁ የነበሩት፡፡ የአካቶ ምልከታ ደግሞ አሠራሩ አካል ጉዳተኞችን ያካት የሚል ነው፡፡ ይህ የትምህርት ሚኒስቴር ፖሊሲም ነው፡፡ ፈታኝ ሊሆን ይችላል ብለንም አንፈራም፡፡ ደቡብ ላይ የአርባምንጭ ተሃድሶ ማዕከል አለ፡፡ ቀድሞ በአገር ውስጥ ግብረሰናይ ድርጅት ይመራ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን የክልሉ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ መደበኛ በጀት መድቦለት እየሠራ ነው፡፡ ላይት ፎር ዘ ወርልድም ገንዘብ እየረዳን ከመንግሥት ጋር እየተባበረ ጋሞጎፋ ዞንና ወላይታ ሶዶ ዞን ላይ በስፋት እየሠራ ነው፡፡ እዚህ ያለው ፕሮጀክት የአካቶ ፅንሰ ሐሳብ ስላለው፣ ሁሉም ዓይነት የአካል ጉዳት ያለባቸው ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩበት ላይ እየተሠራ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ሁሉም ዓይነት የአካል ጉዳት ያለባቸውን ከሌለባቸው ጋር በአንድ ላይ በማስተማሩ ለውጥ እያያችሁ ነው? የምትሰጡት የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ከመሆኑ አንፃርስ መሬት ላይ የተሠራውን እንዴት ትገመግሙታላችሁ?

አቶ ጌታቸው፡-ለውጦች አሉ፡፡ ድጋፉን በተመለከተ ፕሮግራሞቹ ስለሰፉ ብዙ ባለሙያዎች አሉን፡፡ ፕሮጀክት መተግበሩን በየጊዜው እንከታተላለን፡፡ ታች ወርደንም ተጠቃሚውን ጭምር እናነጋግራለን፡፡ ከቀበሌ አስተዳደር ጀምሮ እስከ ላይ ደርሰን እናያለን፣ እንገመግማለን፡፡ ከእኛ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ በየሦስት ዓመቱ ሲታደስ የውጭ ገምጋሚዎች የፕሮጀክቱን ተፈጻሚነት ያያሉ፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ቢሮ የከፈተውም ሥራውን ለመከታተል ነው፡፡ ከጡረታቸው የሚለግሱ ግለሰቦችን ጨምሮ ትላልቅ ተቋማት ድርጅቱን በገንዘብ ስለሚደግፉ ለእነሱ የደረስንበትን ማሳወቅ ግድ ነው፡፡ ከተለያየ ቦታ ተለምኖ የሚመጣው ገንዘብ ለተጠቃሚው መዋሉን ማረጋገጥ አለብን፡፡ በሥራችን ዙሪያ ዋና አጋሮቻችን የመንግሥት ተቋማት ናቸው፡፡ በአካቶ ትምህርቱም ሆነ በጤናው ከመንግሥት ተቋማት ጋር በብዛት እንሠራለን፡፡ የሥራውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በመንግሥት መዋቅር ከተሄደ፣ መንግሥት ቀስ በቀስ ወደ ፕሮግራሙ አስገብቶትና መደበኛ በጀት መድቦለት ያስቀጥለዋል፡፡ ምክንያቱም የእኛ ድርጅት በፈንድ የሚንቀሳቀስ ስለሆነ፣ ይህ ሲታጣ ፕሮግራሙ ይቋረጣል፡፡ በያዝነው የገንዘብ አቅም ከመንግሥት ጋር በመጣመር ቀጣይነት ያለው ሥራ መሥራት እንችላለን፡፡

ሪፖርተር፡- ከአካቶ ትምህርት ድጋፍ በተጨማሪ የዓይን ጤና ላይ ትሠራላችሁ፡፡ የዓይን ጤና እክል በተለይ ከትራኮማ ጋር የተያያዘ ዓይነ ስውርነትን እንዴት ይገልጹታል?

አቶ ጌታቸው፡-የዓይን ሕመም ችግር ከፍተኛ ነው፡፡ በቀደሙት ዓመታት ያለው የዓይን ሐኪምም በጣት የሚቆጠር ነበር፡፡ በዘርፉ የሚሠሩ ዓለም አቀፍ አጋሮችም ኦርቢስና ሲቢኤም ብቻ ነበሩ፡፡ ስለዚህም ችግሩን ለመቅረፍ ድጋፍ ያስፈልግ ነበር፡፡ አሁን ላይ ያለው የዓይን ሐኪም ከቀድሞ ሲነፃፀር እየጨመረ ነው፡፡ ሆኖም በቂ ስላልሆነ እኛ የሰው ኃይሉን መገንባት አለብን ብለን እየሠራን ነው፡፡ የግሎባል ትራኮማ ማፒንግ ፕሮጀክት ወይም ሰርቬይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ2013 ሲሠራ፣ ኢትዮጵያ (ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር) በተሳካ መልኩ ሰርቬይ አስረክባለች፡፡ ይህም ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ወደ ኢትዮጵያ እንዲዞር ዕድል ፈጥሯል፡፡ እኛም ዕድሉን ተጠቅመን ትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉና በምዕራብ ኦሮሚያ በትራኮማ የሚከሰት ዓይነ ስውርነትን ለማጥፋት እያገዝን ነው፡፡ ዝሆኔ በሽታን ለማጥፋት የሚሠራውን ሥራም እንደግፋለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት እየሰጠ በመምጣቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እየተባበሩ ነው፡፡ ላይት ፎር ዘ ወርልድ በኦሮሚያ ትራኮማን ለመከላከል የመድኃኒት ስርጭት ላይ ሲሠራ፣ በክልሉ ችግሩን ለመቅረፍ እንዲተባበር ሥራው የተሰጠው ፍሬድ ሆሎውስ ፋውንዴሽን ድርጅት ቀሪዎቹን ያከናውናል፡፡ የእኛ ድርጅት መድኃኒቱን ሲደግፍ፣ ሥልጠናውን፣ ቀዶ ሕክምናውንና ሌሎች ድጋፎችን ፍሬድ ሆሎውስ ይዞታል፡፡ በዚህም ድርጅቱ ከእኛ ጋር በመተባበር በሌላው ክልል የሚሰጠውን ሙሉ ፓኬጅ በኦሮሚያም ይተገበራል፡፡ የተለያዩ ድርጅቶች ፕሮግራሞች እንዳይደራረቡም  ድርጅቶች ተናበው እንዲሠሩ እየተደረገ ነው፡፡ ይህም አቅምን አቀናብሮና ተባብሮ ችግርን ለመፍታት ያስችላል፡፡ 

Standard (Image)

‹‹ያለው አሠራር ዕድል አይሰጥም›› አቶ ፍቅሬ ዘውዴ፣ የዲጂታል ኦፖርቹኒቲ ትረስት በኢትዮጵያ ዳይሬክተር

$
0
0

አቶ ፍቅዘውዴ ይባላሉ፡፡ የዲጂታል ኦፖርቹኒቲ ትረስት በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ድርጅቱ የተቋቋመው በ1994 ዓ.ም. ካናዳ ውስጥ ነው፡፡ በወጣቶች የሊደርሺፕ ክህሎትና በሥራ ፈጠራ ዙሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች አምስት የአፍሪካ አገሮች ይሠራል፡፡ የተቋቋመው የወጣቶችን ሥራ አጥነት ለመቀነስ እንዲሁም ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶችን ለሥራ ብቁ የሚያደርጉ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት ተፈላጊውን የሰው ኃይል ለማብቃት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከተቋቋመ ሰባት ዓመታትን ቢያስቆጥርም በደንብ መስራት የጀመረው ከ 3 አመታት ወዲህ ነው፡፡ ድርጅቱ ባለፈው ሣምንት በራስ አምባ ሆቴል በሥራ ፈጠራ ሥኬት ያስመዘገቡ ሰዎች ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዕለቱ ከተገኙ ወጣቶች በቀላሉ ውጤት ሊያስገኙ የሚችሉ የቢዝነስ ሐሳቦችን የማፍለቅ ውድድርም ተካሂዶ ነበር፡፡ የድርጅቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሻሂዳ ሁሴንዳይሬክተሩ አቶ ፍቅሬ ዘውዴን አነጋግራቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡- ድርጅቱ የሚያተኩረው በምን በምን ጉዳዮች ላይ ነው?

አቶ ፍቅሬ፡- ወጣቶች ተቀጥሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የተለያዩ ሥልጠናዎች እንሰጣለን፡፡ ቢዝነስ የመፍጠር፣ ቢዝነስን የማሳደግ፣ ቢዝነስን ከደንበኞች ጋር የተዋሃደ እንዲሆን የሚያስችሉ የተለያዩ ሥልጠናዎች እንሰጣለን፡፡ በቀላል አገላለፅ ቢቻል ተቀጥረው አለዚያ የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ክህሎት በሥልጠና እንዲያዳብሩት እናደርጋለን፡፡ በተለይ የተማሩ ወጣቶች ላይ ስንሠራ አይሲቲን ለቢዝነሳቸው እንዲጠቀሙ ተጨማሪ የአይሲቲ ሥልጠና እንሰጣቸዋለን፡፡

ሪፖርተር፡- በሴቶች ላይ በተለየ የምትሠሯቸው ፕሮግራሞች አሉ? እስቲ በሴቶች ዙሪያ ስለምትሠሯቸው ሥራዎች ይንገሩን?

አቶ ፍቅሬ፡- የምንሰጣቸውን ሥልጠናዎችና የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት አገልግሎቶች በተቻለ መጠን ሴቶች ባሉበት ሆነው እንዲደርሳቸው የምናደርግበት አሠራር አለን፡፡  የሥልጠናዎችን ተደራሽነት በተመለከተ ሴቶች በመደበኛ የሥልጠና ፕሮግራም ላይ ለመገኘት በተለያዩ አጋጣሚዎች ላይመቻቸው ይችላል፡፡ ስለዚህም እነሱ ባሉበት አካባቢ፣ በሚመቻቸው ሰዓት ሥልጠናውን በግሩፕ የሚያገኙበትን ሁኔታ እናመቻችላቸዋለን፡፡ በተጨማሪም ምን ዓይነት ሥልጠና ብንሰጣቸው የተሻለ እንደሚሆን ከእነሱ መረጃ በመሰብሰብ ሥልጠና የሚሰጥበትን መንገድ በመቀየስ የበለጠ የተመቸ እንዲሆን እናደርጋለን፡፡ ሴቶች እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ፣ ሥኬታማ ከሆኑ ሴቶች ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የምናደርግበትንና ጠቃሚ ሆነው ያገኘናቸው አሠራሮችም አሉን፡፡ የተለያዩ ፕሮግራሞቻችንን የምናደርሰው ኢንተርኖቻችንን በመጠቀም ነው፡፡ የሴቶች ሴቶችን መርዳትን ታሳቢ በማድረግም ቢያንስ 50 በመቶ የሚሆኑ ኢንተርኖቻችን ሴቶች እንዲሆኑ የምናደርግበት ሁኔታም አለ፡፡

ሪፖርተር፡- ኢንተርን ሆነው በድርጅታችሁ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን እንዴት ነው የምትመለምሉት?

አቶ ፍቅሬ፡-ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የወጡ ወጣቶችን ነው የምንወስደው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ነገር ግን ወደ ሥራው ዓለም ያልገቡ ናቸው፡፡ ካለን ውስን አቅም አንፃር በየዓመቱ የምንቀበለው 122 እስክ 130 ወጣቶችን ነው፡፡ ለአንድ ወር ያህል ተከታታይ የአሠልጣኞች ሥልጠና እንሰጣለን፡፡ ከዚያም ለአንድ ዓመት ያህል ከእኛ ጋር እንዲሠሩ እናደርጋለን፡፡ ከእኛ ጋር በሚቆዩበት የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም ከሥር ከሥር በአመራርና በአይሲቲ ላይ ያላቸውን ዕውቀት እንገነባለን፡፡ የአንድ ዓመት ጊዜያቸውን በሚያጠናቀቁበት ወቅት በተለያዩ ሥራዎች ለመሠማራት ብቁ ይሆናሉ፡፡ ከእኛ ጋር ተመርቀው በመውጣት ገበያውን ይቀላቀላሉ፡፡ ተፈላጊው ክህሎት ስላላቸውም በቀላሉ ሥኬታማ ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶቹ ኢንተርኖቻችን ገና ሳይመረቁ በተለያዩ ተቋማት ይቀጠራሉም፡፡ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶችን እንዲማሩ የሚነሳሱበትና የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን የሚቀጥሉም አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ከአዲስ አበባ ውጭ በተለያዩ የክልል ከተሞች ትሠራላችሁ? የምትሠሩ ከሆነ አካባቢዎቹን የምትመርጡበት መሥፈርቶች ምን ምን ናቸው?

አቶ ፍቅሬ፡-ምንሠራው የወጣት ሥራ አጦች፣ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰት በሚበዙባቸው በአዲስ አበባ፣ በመቀሌ፣ በባህር ዳር፣ በአዋሳና በአርባምንጭ ከተሞች ነው፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ከተቋቋመና መሥራት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ25,000 የሚበልጡ ወጣት ሴቶችና ወንዶችን መድረስ ችለናል፡፡ሥልጠናውን ለማዳረስ የምንሞክርበት ሁኔታ ፒር ቲቺንግ (የአቻ ለአቻ ሥልጠና) በመሆኑ ግን ውጤታማ ነው፡፡ ከአንድ አካባቢ ወስደን የምናሰለጥነው አንድ ኢንተርንም በአካባቢው ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የሚፈጥርበት ዕድል መኖሩም የተሻለ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

ሪፖርተር፡- በሥራ ፈጠራ ዙሪያ ያሉ ችግሮች ምንድን ናቸው?

አቶ ፍቅሬ፡-በጣም ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ዋናው ሥራ የሚሠራበት ቦታ አለማግኘት ነው፡፡ ጥሩ የቢዝነስ ሐሳብ ኖሯቸው ወደ ተግባር ለመለወጥ መሥሪያ ቦታ በማጣት ብዙ የሚቸገሩ አሉ፡፡ ቦታ ቢያገኙም በአገሪቱ ባለው አመቺ ያልሆነ የአከራይ ተከራይ  ግንኙነት ለመሥራት የሚቸገሩ ብዙ ናቸው፡፡ የኪራይ ዋጋ እስከ 40 በመቶ በአንዴ የሚጨምሩ አሉ፡፡ ይኼ የገበያ ሁኔታውን ለመገመት አዳጋች ከማድረጉ ባለፈ የትርፍ ህዳጋቸው በጣም እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ ቢሮክራሲም ሌላው ችግር ነው፡፡ አንድ ጉዳይ ለማስፈጸም ከምዝገባ ጀምሮ ብዙ ውጣ ውረዶች አሉ፡፡ የሚጠየቁ ሰነዶችም ብዙ ናቸው ገደብ የላቸውም፡፡ አንድ ሰው አንድ የቢዝነስ ሐሳብ ይዞ ሲነሳ ሐሳቡን እስካልተገበረው ድረስ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆን ለማወቅ አይችልም፡፡ ለዚህም አንድ ዓመት ወይም ስድስት ወር የመሞከሪያ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን ያለው አሠራር ዕድል አይሰጥም፡፡ ገና ከመጀመርያው ሕንፃ ይኑርህ፣ ቤት ይኑርህ፣ ይህን ክፍል የሚባል ነገር አለ፡፡ እነዚህ በጣም ተስፋ የሚያስቆርጡ ናቸው፡፡ ፋይናንስም ሌላው መሠረታዊ ችግር ነው፡፡ የኛ ዒላማ ወጣቱ ነው፡፡ ወጣቱ ደግሞ ገንዘብ ሲበደር የሚያስይዘው ኮላትራል (ማስያዣ ንብረት) የለውም፡፡ ለዚህም መነሻ ገንዘብ በማጣት ስራውን ከጅምሩ ይተዉታል፡፡ እንዲህ ያሉ ችግሮችን ይፈታሉ ተብለው የተቋቋሙ  የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እንኳን ያለ ኮላተራል ብድር አይሰጡም፡፡ እንዲያውም ባንኮች ከሚጠይቁት ማስያዣ የበለጠ የሚጠይቁበት አጋጣሚ አለ፡፡ ወጣቶች የሚያመጡትን አዲስ የቢዝነስ ሐሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥ ድጋፍ የማድረግ ነገርም ዝቅተኛ ነው፡፡ ለዚህም በማኅበረሰቡ ሌላ ትልቅ ለውጥ መፍጠር የሚችለውን ሐሳብ ወደ ጎን ብሎ ተቀጣሪ ሆኖ የመሥራት ነገር አለ፡፡ እነዚህ ትልቅ ነገሮች ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- ድርጅቱ የቴክኒክ ድጋፎችን ከማድረግ ባለፈ ወጣቶቹን በገንዘብ የሚደግፍበት አሠራር አለ?

አቶ ፍቅሬ፡- እኛ በመሠረቱ የገንዘብ ድጋፍ አንሰጥም፡፡ ነገር ግን ይህን አገልግሎት ከሚሠጡ ከተለያዩ ተቋማት ጋር አብረን በመሥራት የሚሰጡት የፋይናንስ ድጋፍ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ሥልጠናና ክትትል እናደርጋለን፡፡

ሪፖርተር፡- በአገሪቱ የሚሰጡ የኢንተርፕሩነርሺፕ ሠልጣኞች በወኔ ተሞልተው አንድን ሥራ እንዲጀምሩ የሚያነሳሳ እንጂ በሥራው ላይ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ችግሮችም እንዳሉና እንዴት መወጣት እንዳለባቸው ጭምር የሚያሠለጥኑ አይደሉም የሚሉ አሉ፡፡ በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምን ይመስላል?

አቶ ፍቅሬ፡- እንዲህ ዓይነት ነገር የሚፈጠረው የሚሰጡ ሥልጠናዎች የፅንሰ ሐሳብ ብቻ ሲሆኑ ነው፡፡ እኛ ግን ዝም ብለን ሌክቸር አንሰጥም፡፡ እኔ ኢንተርፕሩነር መሆን እችላለሁ ወይ ብሎ ራስን እንዲጠይቅ የሚያስችል ሥልጠና እንሰጣለን፡፡ በሥልጠናዎች ላይ ሥኬታማ የሆኑ ሥራ ፈጣሪዎች ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን፡፡ ይህ ምን ምን ዓይነት ችግሮች መኖራቸውን እንዲገነዘቡ እንዴትስ ማለፍ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ያስችላል፡፡

ሪፖርተር፡- ለምን ያህል ጊዜ ነው ሥልጠና የምትሰጡት?

አቶ ፍቅሬ፡- ሥልጠናዎች የተለያዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ለመጀመርያ ጊዜ ሠልጣኞች ከሦስት እስከ አራት ሳምንት እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡ ከዚያ በኋላ ለአንድ ወር ያህል ክትትል እናደርግላቸዋለን፡፡ ሌሎቹ ግን ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት የሚሰጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ብቻ በቂ ባለመሆናቸው በሚፈልጉት መጠን ድጋፍ የሚያገኙበት አሠራርም አለን፡፡ እነሱ ፍላጎት ኖሯቸው እስከመጡ  ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወራት ድረስ አስፈላጊውን አገልግሎት እንሰጣቸዋለን፡፡

 

ሪፖርተር፡- ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ምሩቆችን ለስራ ብቁ ለማድረግ የምትሰሩትስ ካለ?

አቶ ፍቅ፡- ብዙ ጊዜ ከኮሌጆች፣ ከዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች ለሥራ ብቁ የሚያደርጋቸውን ዕውቀት ጨብጠው አይወጡም፡፡ በተለይም የኮሙኒኬሽን፣ የኔት ዎርኪንግ፣ ደንበኛ አያያዝ የመሳሰሉት ክህሎቶች ላይ ደካማ ናቸው፡፡ ቀጣሪዎቹ የሚፈልጉት ያህል ዕውቀት የላቸውም፡፡ ቀጣሪዎች የሚፈልጉት ሌላ፣ የትምህርት ተቋማት የሚያዘጋጁት የሰው ኃይል ሌላ ነው፡፡ ይኼንን እንደ አንድ ክፍተት ተመልክተን እየሠራንበት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- አለ ለሚሉት ችግር ማለትም የትምህርት ተቋማት የሰው ኃይል ከማፍራት አኳያ ያለባቸው ከፍተት እንዴት ተፈጠረ? ቀጣሪዎችስ ሠራኞች ምን ዓይነት ክህሎት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ?

አቶ ፍቅ፡- የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተለያየ ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ይፈልጋሉ፡፡ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ጨርቃጨርቅ ላይ ቴክኒካል ክህሎት ያለው ሰው ይፈልጋል፡፡ ሌሎችም እንደዚሁ፡፡ ሁሉም ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከሠራተኞች የሚፈልጉት አንድ ዓይነት መስፈርት አለ፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ የኮሙኒኬሽን ክህሎት ነው፡፡ ሠራተኛው እንዴት ነው ደንበኞችን የሚያስተናግደው? እንዴት ነው ራሱን የሚገልጸው? የሚለው ጉዳይ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ለወጣቶች የሕይወት ክህሎት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የተለያዩ ችግሮች ሲገጥማቸው እንዴት መወጣት ይችላሉ? እነዚህ እነዚህ ሁሉ አብረው የሚሄዱ ዕውቀቶች ናቸው፡፡ እኛም በዚህ ረገድ የሚኖረውን ክፍተት ለወጣቶች ሥልጠና በመስጠት ለመሙላት እንጥራለን፡፡ ከዚህም ሌላ ቴክኒካል የሆኑ የኢንተርፕሩነር ሥልጠናዎችን እንሰጣለን፡፡ የትምህርት ሥርዓቱ ላይ ችግር አለ፡፡ በሁሉም ቦታዎች ላይ ያለው የትምህርት ጥራቱ ደካማ እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው፡፡ እያደገ ከሚሄደው የኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ጋር የተጣጣመ የትምህርት አሰጣጥም የለም፡፡ ተማሪዎች የሚማሩበት መንገድም የተግባር ትምህርትን ያላካተተ የፅንሰ ሐሳብ ትምህርት ብቻ መሆኑም ትልቅ ችግር ነው፡፡ የፅንሰ ሐሳብ ትምህርቶች ከተግባር ጋር አያይዘው ስለማይማሩ ወደ ሥራው ዓለም በሚገቡበት ወቅት በትምህርት ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር ለመለወጥ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የትምህርት ጥራቱ ጉዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዴት ነው?

አቶ ፍቅሬ፡- እኛ ካጤንነው ጊዜ ጀምሮ የትምህርት ጥራቱ እየደከመ እየደከመ ነው የመጣው፡፡ በተለይም ደግሞ ብዛት ላይ ትኩረት ተደርጎ መሠራት ከተጀመረ በኋላ የትምህርት ጥራቱ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡ ብዛት ላይ ማተኮሩ የመምህራን ቁጥርና የተማሪዎች ቁጥር እንዳይጣጣምም አድርጓል፡፡

ሪፖርተር፡- በአገሪቱ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

አቶ ፍቅሬ፡- የተለያዩ ስትራቴጂዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ዋናው የትምህርት ሥርዓቱን ከጥራት፣ ከይዘትና ከተደራሽነት አኳያ መለወጥ ያስፈልጋል፡፡ አሁን በብዛት እየተሠራ ያለው ተደራሽነት ላይ ነው፡፡ ተደራሽነትን ደግሞ ከሌሎች ነገሮች ጋር ሚዛናዊ አድርጎ ማስኬድ ካልተቻለ አደገኛ ነው፡፡ የዚህ ጥቅሙና ጉዳቱ የሚታየው ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ ከዓመታት በኋላ አደገኛ ነገር ከማየት አሁኑኑ ነገሮችን በጥሞና አስቦ መሥራት ግድ ነው፡፡ መምህር ሳይኖር 30 ዩኒቨርሲቲ ቢከፈት ምንድነው ጥቅሙ? በአሁኑ ወቅት በደንብ ያልሠለጠኑ መምህራን እንዲያስተምሩ ሲደረግም ይታያል፡፡ ያለው የተጠያቂነት ሥሜትም በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ክፍል ገብቶ ሳያስተምር ሁለትና ሦስት ወር ሌላ ቦታ ቆይቶ ቅዳሜና እሑድ ገብቶ የአንድ ሴሚስተር ኮርስ ጨርሶ መሄድም ተለምዷል፡፡

ሪፖርተር፡- ለመፍጠር ያሰባችሁትን ያህል ለውጥ  መፍጠር ችለናል ይላሉ?

አቶ ፍቅሬ፡- እኛ የምንፈልገው ፈጣንና በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች ሥራ መፍጠር የሚችሉ ወጣቶችን ማፍራት ነው፡፡ ይኼንን ማሳካት የአንድ ድርጅት  ሥራ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡     

 

 

Standard (Image)

‹‹ሕገወጦችን ቁጥጥርና ክትትል ከሌለ በመሥፈርት ብቻ መከላከል ያስቸግራል››

$
0
0

አቶ ኃይለልዑል ኦላና፣ የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ

ለዓመታት በውጭ ኩባንያዎች ተይዞ የቆየው ነዳጅንና የተለያዩ ዘይቶችን ወደ አገር ውስጥ የማስመጣት እንቅስቃሴን ኢትዮጵያውያን ከተቀላቀሉ ሰነባብተዋል፡፡ በዚህ ረገድ እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ተመሥርቶ ሥራውን የጀመረው የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማኅበር የመጀመርያ ነው፡፡ ኩባንያው በ21 ኢትዮጵያውያን አማካይነት በ13 ሚሊዮን ብር ተቋቁሞ በበጀት ዓመቱ የተከፈለ ካፒታል 163.5 ሚሊዮን መድረሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው አቶ ኃይለ ልዑል ኦላና ይናገራሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም 269 ባለድርሻዎች አሉት፡፡ ከ1,100 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ጭምር አቶ ኃይለ ልዑል ያስረዳሉ፡፡ የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም፣ የቢፒ ኩባንያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያመርታቸው የካስትሮል ዘይትን በኢትዮጵያ በማስተዋወቅና አገልግሎት ላይ በማዋል በብቸኝነት ተጠቃሽ ሆኗል፡፡ ይሁንና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ባልጠበቁ የዘይት ምርቶች፣ እንዲሁም በአገሪቱ ያለው የትርፍ ህዳግ በጣም ትንሽ በመሆኑ ምክንያት ናፍጣ፣ ቤንዚንና ነጭ ጋዝ እየተቀላቀሉ ለአገልግሎት መዋላቸው በተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ ያሳስባቸዋል፡፡ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርግ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም አጥጋቢ መልስ ሊገኝ አለመቻሉን ጭምር ይናገራሉ፡፡ ሌሎችም በርካታ ተግዳሮቶች በገበያው እንዳሉ የሚናሩ አቶ ኃይለ ልዑልን ደረጀ ጠገናውአገነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም እንዴት ተመሠረተ?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ኩባንያው እንዲመሠረትም ምክንያት የሆነው በአገሪቱ የነበሩት አራቱ ኩባንያዎች (አጅፕ፣ ሼልና ቶታልና ሞቢል) የደርግ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ  በመኪኖች ላይ ለምን አትሠሩም የሚል ጥያቄ ይቀርብ ስለነበርና ይህንኑ ተከትሎ ለመንግሥት በቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው፡፡ ሥራው በሞኖፖል ተይዞ የቆየበት ጊዜ ማብቃቱ በሚመለከተው የመንግሥት አካልም ስለተገለጸልን በጥቂት ቁርጠኛ የአገር ውስጥ ባለመብቶች 13 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ነው የተመሠረተው፡፡ መሥራች አባላቱም 21 ነበሩ፡፡ ኩባንያው ሥራውን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በመጠኑም ቢሆን ምንም ዓይነት ኪሳራ ሳያጋጥመው ሲሠራ ቆይቶ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የተከፈለ ካፒታል 163.5 ሚሊዮን ደርሷል፡፡ ዕቅዱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ 300 ሚሊዮን ማድረስ ነው፡፡ 200 ሚሊዮን ያህሉን በዚህ በጀት ዓመት እንዘጋለን ብለን አቅደን እየሠራን እንገኛለን፡፡

ሪፖርተር፡- የኩባንያው ባለቤቶች ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናችሁ፡፡ በዚህ ሥራ ላይ ደግሞ የረዥም ዓመታት ልምድ ኖሯቸው ሲሠሩ የቆዩት የውጭ ኩባንያዎች ከመሆናቸው አኳያ ይህ በገበያው የተፎካካሪነት አቅማችሁ ላይ የፈጠረው የለም?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- በዋናነት በዘርፉ ውስጥ አቅሙም ብቃቱም ያላቸው ባለሙያዎችና በአገልግሎታቸው ዓለም ላይ ተቀባይነትን ያተረፉ ዘይቶችን ይዘን ወደ ሥራው መግባት በመቻላችን ኢትዮጵያውያን በመሆናችን ብቻ አልተቸገርንም፡፡ በመንግሥት በኩል ጥሩ እገዛ ስለተደረገልንም ቀጥለንበት ተሳክቶልናል፡፡ አሁንም በአጭር ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደርሳለን የሚል እምነት አለኝ፡፡ እርግጥ ነው በሥራው የዓመታት ዕድሜ ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች እንደመኖራቸው አስቸጋሪ ነገሮች ሊገጥሙ እንደሚችሉ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በዋናነት ኢትዮጵያዊያን የዚህ ሥራ ባለቤት በመሆን ለመሥራት እንችላለን የሚለውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከቢሮ ቢሮ የነበረው ውጣ ውረድ ከባድ ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ ኩባንያው አሁን ለሚገኝበት ደረጃ እንዲበቃ ከእኛ በፊት የነበሩት አንጋፋ ባለሙያዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር፡፡ ሌላው ኩባንያው ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያውያን በመሆኑ የሥራ ቋንቋውም የራሳችን ነው፡፡ ምክንያቱም ኩባንያችን ስለሚያቀርበው ምርት በአማርኛ የቀረበ ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ለዚህም የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም ሥራውን ሲጀምር የኩባንያውን ሎጎና ተዛማጅ ሥራዎችን በራሳችን ቋንቋ አሠርተን ነው ወደ ገበያ የገባነው፡፡ ይኼ በራሱ ሒደት ነበረው፡፡ አንድ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት አገር በራስ ቋንቋ አዘጋጅቶ ኩባንያውን በይፋ ያስተዋወቀ የተባበሩት ፔትሮሊየም የመጀመርያው ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በገበያው ያላችሁ ተደራሽነትስ?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ውድድሩ ጠንካራ ቢሆንም ተወዳድሮ ወደ ስኬት መምጣት መቻሉ ነው ትልቁ ነገር፡፡ በዚህ ደረጃ ኩባንያችን ተሳክቶለታል ብለን እናምናለን፡፡ ቀደም ብለው የነበሩት አራቱ ድንበር ዘለል ኩባንያዎች በነበረው ሁኔታ መቀጠል ያልቻሉበት አጋጣሚም አለ፡፡ ከአራቱ ድንበር ዘለል ኩባንያዎች በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ብቻ ናቸው ያሉት፡፡ ሆኖም ያሉትም ቢሆኑ በነበራቸው ቆይታ ምክንያት በገበያው ውስጥ ያላቸው ድርሻ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ብዙ ተጠቃሚም አላቸው፡፡ በተቻለ መጠን ከጨረታው ጀምሮ እየተሳተፍን እንገኛለን፡፡ ለዚህ በዋናነት በተለይ ከአዲስ አበባ ውጭ ተደራሽ ባልሆኑ ቦታዎች ትኩረት አድርገን ብዙ ቦታዎች ላይ ማደያዎችን ሠርተን አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን፡፡ የኢትዮጵያዊነቱ ዋናው ዓላማና ግቡም የአገሪቱ ሕዝብ በሚኖርበት አካባቢ ምንም ዓይነት ውጣ ውረድ ሳይኖርበት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ይህን የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አሳክቷል፣ ይቀጥልበታል፡፡ አዲስ አበባ የራሱ የሆነ ፉክክር አለ፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው ያሉት ማደያዎች የቤንዚን ናቸው፡፡ ክፍለ አገር ደግሞ በአብዛኛው ናፍጣና ኬሮሲን የ(ነጭ ጋዝ) ገበያ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ በተለይ ነጭ ጋዝ ለክፍለ አገር ሕዝብ በአብዛኛው በማገዶነትም ትልቅ ጥቅም ስላለው ናፍጣ ደግሞ ለትልልቅ መኪኖች ስለሚውል ያንን ታሳቢ ያደረገ አገልግሎት እየሰጠን ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- ከማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ጋር ተያይዞ እንቅስቃሴያችሁ ምን ይመስላል?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ፕሮጀክቶቹ አሉን፡፡ ወደፊትም በስፋት ለመቀጠል እንፈልጋለን፡፡ በአሁኑ ወቅት 110 ማደያዎች አሉን፡፡

ሪፖርተር፡- ማደያዎችን በማስፋፋት ሒደት መመዘኛ የምታደርጓቸው ነገሮች ምንድናቸው?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ማደያዎቹ የሚገኙባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ቦታው ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጫነት ይመቻል፤ አይመችም በሚል የገበያ ጥናት ከተደረገ በኋላ የወደፊቱ ግምት ውስጥ ገብቶ ፕሮጀክቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

ሪፖርተር፡- የኩባንያው የተፎካካሪነት አቅም እየጎለበተ መሆኑ የሚሳዩ ምልክቶች አሉ፡፡ የባለአክሲዮኖች ድርሻስ እንዴት ነው? እስካሁን በ21 መሥራቾች እጅ እንደተያዘ ነው?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ኢትዮጵያውያን በገበያው ውስጥ ያለንን አቅም አልተጠቀምንበትም የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምክንያቱም  ከ20 በላይ ትላልቅ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ኩባንያዎች በባለአክሲዮንነት አሉበት፡፡ ወደ 300 መኪና የያዘ የፍሳሽ ትራንስፖርትም አለ፡፡ እነዚህ በሙሉ የእኛን የሚጠቀሙ ቢሆን፣  ከዚህ ውጭ ገበያው ባላስፈለገን ነበር፡፡ ለዚህ የራሱ ምክንያቶችም አሉት፣ የአቅም ውስንነት አንዱና ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡ በመሆኑም ይህ የሚያሳየው የራሳችንን አቅም ሙሉ በሙሉ ያልተጠቀምንበት መሆኑን ነው፡፡ አሁን በደረስንበት ደረጃ ግን ከበቂ በላይ ክምችት አለን፡፡ የምንይዛቸው ምርጥ ዘይቶች ናቸው፡፡ ምክንያቱም  ዘይቶቹን ስናመጣቸው ገበያውን ብለን ብቻ ሳይሆን ለራሳችን አባላት ብለን የምናመጣቸው ናቸውና፡፡ ጥራቱ ላይ የምንሠራው ተጠንቅቀን ነው፡፡ ለዚህ በኩባንያው ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ዋናውና ትልቁ ኃላፊነታቸው ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት በአጭር ጊዜ ገበያው በተሻለና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ጎላ ብለን የምንታይበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን አምናለሁ፡፡   

ሪፖርተር፡- ዘይቶቻችሁ ከሌላው የሚለያቸው ምንድነው?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ለልዩነቱ አንዱና ዋናው ነገር የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም የሚያስመጣቸው ዘይቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ የተሽከርካሪና የፋብሪካ አምራቾች ደረጃዎች ምዘናን ያለፉ መሆናቸው ናቸው፡፡ በዚህ ደረጃ ዓለም ላይ ያሉ ትልልቅ ኩባንያዎች ሦስት ናቸው፡፡ ትልቁ በነዳጅም በዘይትም ኤክስኤል ሞቢል ሲሆን፣ ቀጥሎ ሼልና እኛ የምናመጣው ቢፒ ካስትሮል ናቸው፡፡ ስለሆነም እነዚህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማንኛውም መኪና አምራችም ሆነ ኢንዱስትሪዎች የሚስማሙባቸው (እንዲጠቀሟቸው የሚመክሯቸው) ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃም ቢሆን ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ትልልቅ ኩባንያዎች ማሽነሪዎቻቸውን ይዘው ሲገቡ የካስትሮል ምርቶችን ነው እንዲጠቀሙ የሚመከሩት፡፡ ከመኪና አምራቾች መርሰዲስ፣ ቢኤምደብሊው፣ ቮልስዋገንና የመሳሰሉት ትልልቅ ኩባንያዎች እነዚህን ምርቶች እንዲጠቀሙ ነው የሚመክሩት፡፡ እኛም ስናመጣው ይህንኑ ታሳቢ አድርገን ነው፡፡ ዋጋውም ከፍ ያለ ነው፡፡ ይኼ ከጥራቱ ጋር አብሮ የሚታይ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህም ነው ለዋጋ ብቻ በሚል የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ አናስገባም የምንለው፡፡ ምክንያቱም በአገሪቱ የዘይት ምርቶችን ለመቆጣጠር ብቃት ያለው ተቋም የለም፡፡ ማንም ሰው የፈለገውን ዘይት አስመጥቶ መሸጥ ይችላል፡፡ የተባበሩት ይህንን ተሞክሮ አይጠቀምም፡፡ ምክንያቱም በውጭ ምንዛሪ የመጡ ተሽከርካሪዎችና ማሸነሪዎች በምንም ዓይነት የጥራ ደረጃ በጎደላቸው ዘይቶች ተጠቅመው የአገልግሎት ጊዜያቸው እንዲያጥር አይፈልግም፡፡ በዚህ የተነሳም በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸው የተረጋገጠላቸው የቢፒና የካስትሮል ቅባቶችን አስመጥተን ነው የምንሸጠው፡፡ እዚህ ላይ አንዳንድ ሰዎች ሁሉም ዘይት ዘይት ነው ብለው የሚያስቡ አሉ፡፡ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ በየአምስት ሺሕ ኪሎ ሜትር የሚቀየር የዘይት ዓይነት አለ፡፡ አሥርና እስከ 20 ሺሕ ኪሎ ሜትር ማገልገል የሚችል የዘይት ዓይነትም አለ፡፡ አንዳንዶቹ 3,000 ኪሎ ሜትር ከሄዱ በኋላ የሚቀይሩም አሉ፡፡ የኛ ከአሥር እስከ 20 ሺሕ ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡ ይኼ በዋጋው አንፃርም ሲታይ እጅግ የተሻለ ነው የሚሆነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከአካባቢ የአየር ብክለት ጋር ተያይዞ የእናንተ ዘይቶች እንዴት ይታያል?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም የሚያስመጣቸው ዘይቶች በአብዛኛው አካባቢያዊ ብክለትን የሚከላከሉ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አልፈው የመጡ እንደመሆናቸው ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እንዲወጣ የማድረግ ብቃት ያላቸው ናቸው፡፡ ለአካባቢ ጥበቃም የምናበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም፡፡ ለዚህም ከደንበኞቻችን የሚመጡልን ግብረ መልሶች እጅግ አበረታች ናቸው፡፡ ከደንበኞቻችን ዳንጎቴ ሲሚንቶ አንዱ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የተባበሩት የሚያስመጣቸው ዘይቶች ዋጋ በንፅፅር ከፍ ያለ መሆኑ ተፅዕኖ አልፈጠረባችሁም?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ፈጥሯል፣ በዚህ ረገድ አንዳንድ ሰዎች አሥር ብርና ከዚያ በላይ ተጨማሪ ክፍያ ላለመክፈል እርካሽ የሆኑ ዘይቶችን የሚጠቀሙ አሉ፡፡ እነዚያን ሰዎች ለማስተማር እየሞከርን ነው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ዛሬ የሚከፍሉትን ብቻ አስበው ትልቁን ነገር እንዳይዘነጉት ስለምንፈልግ ነው፡፡ 100 እና 200 ብር ተጨማሪ ላለመክፈል ብለው እስክ 50,000 ብር ወጪ የሚዳርጉ አጋጣሚዎች በጣም ብዙ ናቸው፡፡ በዚህ ነገር ላይ መካኒኮችን በማሠልጠን ጭምር ሰዎች ግንዛቤው ኖሯቸው ጥራት ባለው ዘይት እንዲጠቀሙ ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነው፡፡ አገራችን ለቴክኖሎጂው ቅርብ እንድትሆን እንፈልጋለን፡፡ የምንገዛቸው ዕቃዎች ከመግዛታችን በፊት የጥራት ደረጃቸው እስከምን ድረስ ነው? የሚለውን መለየትና ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ሌላው ደግሞ ተቆጣጣሪ አካል በዚህ ነገር ላይ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ እንፈልጋለን፡፡ ይኽ ካልሆነ የጥራት ደረጃቸውን ባልጠበቁ ዘይቶች ለከፋ ጉዳት የሚደርስባቸው ንብረቶች ይኖራሉ፡፡ በሌሎች አገሮች እንደዚህ ዓይነት ምርቶች በላብራቶሪ ይፈተሻሉ በእኛ አገር ግን የለም፡፡

ሪፖርተር፡- ከነዳጅ ጋር ተያይዞ ቀላቅለው ለገበያ የሚያቀርቡ ኩባንያዎች እንዳሉ ይነገራል፡፡ የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም በዚህ ረገድ የሚለው ይኖራል?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- በዚህ ጉዳይ በአገሪቱ ውስጥ ትልቅ ችግር እየተጋፈጥን ነው፡፡  ናፍጣ ወይም ቤንዚን ውስጥ ነጭ ጋዝ የሚጨምሩ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ በእኛ በኩል ከእነዚህ ችግሮች ነፃ መሆናችንን ለማረጋገጥ በማደያዎቻችን ነዳጅ በሚራገፍበት ጊዜ ታይቶና ተረጋግጦ ነው እንዲራገፍ የምናደርገው፡፡ በሁሉም ማደያዎቻችን ድንገተኛ የቁጥጥር ሥራዎችን እንሠራለን፡፡ ነዳጅ የሚጭኑልን ተሽከርካሪዎችም ይህንኑ የኩባንያውን አቋም ስለሚያውቁ ይጠነቀቃሉ፡፡ በእኛ ደረጃ ቁጥጥር ተደርጎ ብቻ መፍትሔ አያመጣም፡፡ ምክንያቱም በናፍጣ፣ በቤንዚንና ነጭ ጋዝ መካከል ያለው የዋጋ ልዩነት እስካልተስተካከል ድረስ ችግሩ መቀጠሉ አይቀርምና ጉዳዩን ለሚመለከተው የመንግሥት አካል በተለይ በዋጋው ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርበናል፡፡ በተለይ ነጭ ጋዝ የሚለይበት ቀለም ይኑረው ብለን ጠይቀናል፡፡ እስካሁን ሰሚ ባናገኝም ጩኸታችን ግን ይቀጥላል፡፡ ችግሩ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ብቻ ሳይሆን ለአየር ንብረት ብክለትም ምክንያት መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ ረገድ አሁንም ትልቁን ድርሻ መውሰድና መንቀሳቀስ ያለበት መንግሥት ነው፡፡ መንግሥት ዕርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ በተለይ በንብረት ላይ በርካታ ጉዳቶች እየታዩ ነው፡፡ ይኼ ወደፊት ማስተካከያ ካልተደረገ ተባብሶ መቀጠሉ ስለማይቀር ጉዳቱም በዚያው መጠን ነው እየጨመረ የሚሄደው፡፡ ጉዳቱ ለአገር ኢኮኖሚ ከባድ ነው፡፡ የሕዝብ ሀብት እየወደመ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- እንደነዚህ የመሰሉ ኩባንያዎች ሊያሟላቸው የሚገቡ መሥፈርቶች የሉም? ምክንያቱም መሥፈርቶቹ ሕገወጥ አሠራሮችን መቆጣጠር ያስችላል?

አቶ ኃይለ ልዑል፡- ኩባንያዎቹ ሲቋቋሙ ደረጃቸውን የጠበቁ መሥፈርቶች ይኖሯቸዋል፡፡ ከመሥፈርቶቹ አንዱና ዋናው ዲፖ ነው፡፡ የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም መሥፈርቶቹን አሟልቶ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ሕገወጦችን ቁጥጥርና ክትትል ከሌለ በመሥፈርት ብቻ መከላከል ያስቸግራል፡፡ ሌላው የችግሩ መንስዔ የምንለው በናፍጣና በቤንዚን መካከል ያለው የትርፍ መጠን (ህዳግ) አነስተኛ መሆኑ ነው፡፡ ሕገወጦች መቀየጥን እንዲለምዱ የሚያስገድዳቸው ከልዩነቱ ጥቅም ለማግኘት ነው፡፡ ነዳጅ መቀየጥና መሸጥ ያለ ቢሆንም፣ መጠኑ ላይ ግን ተገቢ ትኩረት እየተሰጠ አይደለም፡፡ ለዚህ ቀደም ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው የትርፉን መጠን በማሻሻል በዋጋው ልዩነት ላይ የማቀራረብ ሥራ ቢሠራ ችግሩን ማቃለል ይቻላል ብለን እናምናለን፡፡  ለዚህ የኬሮሲን ቅየጣ ዋናው ምክንያት በአገራችን የትርፍ መጠኑ (ህዳጉ) በጣም ትንሽ በመሆኑ ነው፡፡ የሚገርመው የእኛን ዓይነት የትርፍ ህዳግ ያለው አገር የለም፡፡ በአገራችን አሁን ያለው የትርፍ ህዳግ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከነበረው በመቶ ሲቀመጥ ተመሳሳይ ነው፡፡ በዚህ ነገር ላይ መንግሥትም ሊያስብበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለው የትርፍ መጠን (ህዳግ) ከ30 ዓመት በፊት አንድ ቦቴ 30,000 ብር ሲራገፍ በነበረበት ያለ ነው፡፡ ይኼ ማለት እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እስከዚህ ባለው ጊዜ ውስጥ አንድ ቦቴ ለማራገፍ አንድ ሚሊዮን ብር ይጠየቃል፡፡ ባለፈው ዓመት ሦስት ሳንቲም ጭማሪ ተደርጓል፡፡ ለሕገወጥ አሠራር በመንስዔነት እነዚህ ነገሮች የራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡ አሁንም መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የጨመረው የሦስት ሳንቲም ጭማሪ ሥራውን ለማከናወን ከሚፈለገው ወረት ጋር አይመጣጠንም፡፡ በጣም ያንሳል፡፡ ለመንግሥት አማራጮችን አሳውቀናል፡፡ እንቀጥልበታለን፡፡ ተሽከርካሪዎች በሚቀየጡ ነዳጆችና ጥራታቸውን ባልጠበቁ ዘይቶች ምክንያት ለውድመት እየተዳረጉ መሆኑ አሁንም ሊታሰብበት እንደሚገባ የፀና እምነት አለን፡፡ በተለይ ደግሞ ሁለት ማደያ የከፈተ ሰው ኩባንያ ሆኖ ሊፈቀድለት ይገባል የሚባለው ትኩረት የሚሻ መስሎ ይሰማናል፡፡ መንግሥት በእነዚህ ነገሮች ላይ ያለው ሚና ጠብቅ ያለ ቢሆን እንመርጣለን፡፡

 

Standard (Image)

‹‹በየቀኑ ከተማ የሚገባው ሰው በርካታ ከመሆኑ የተነሳ የአዲስ አበባን ጤና ችግር መፍታት ያዳግታል››

$
0
0

አቶ ግርማ አሸናፊ፣ ተሰናባቹ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፊል ሹም ሽሩን ታኅሣሥ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲያካሂድ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ግርማ አሸናፊ በዶ/ር ጀማል ኡመር የተተኩ ሲሆን፣ ይህን ቃለመጠይቅ ያደረግነው፣ የቀድሞው የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማል፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ሆነው ከመሾማቸው አስቀድሞ ነው፡፡ አቶ ግርማ አሸናፊ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ላለፉት ሦስት ዓመታት መርተዋል፡፡ አዲስ አበባ ብዙ ነዋሪዎች ተጨናንቀው የሚኖሩባትና የሁሉም መናኸሪያ ከመሆኗ አንፃር ለተለያዩ የጤና እክሎች ስትጋለጥ ትስተዋላለች፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ቢሮው ምን እየሠራ ነው? በሚለው ዙሪያ ምሕረት ሞገስአቶ ግርማን አነጋግራቸዋለች፡፡   

ሪፖርተር፡- አዲስ አበባ ከሌሎች ክልሎች አንፃር፣ በጤና ሁኔታ ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ስትሆን ትታያለች፡፡ የተጋላጭነቷን ስፋት ቢያብራሩልን?

አቶ ግርማ፡- ከሌሎች ክልሎች አንፃር አዲስ አበባ ስትታይ ለየት የሚያደርጓት ባህሪያት አሉ፡፡ አዲስ አበባ ባህሪዋ ሙሉ ለሙሉ ከተማ ነው፡፡ ስለሆነም በርካታ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውስብስብ ጉዳዮች አሉባት፡፡ ከአጠቃላይ ኅብረተሰቡ ሁኔታ ስትታይ በገቢም ቢሆን ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ኅብረተሰብ የሚኖርባት ናት፡፡ በአኗኗር ዘይቤም ሲታይ በርካታ ጉዳዮችን የምንቋደስባት ናት፡፡ የምንኖርባቸው አካባቢዎች ለሰው ልጆች ምቹ መሆን አለባቸው፡፡ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ሲኖርም ጤናማ ኅብረተሰብ ይኖረናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ብዙው ኅብረተሰብ በጣም ተጠጋግቶ ይኖራል፡፡ ብዙ ነገር በጋራ ይጠቀማል፡፡ በጋራ የምንኖርበትን አካባቢ በጋራ የማናፀዳ ከሆነና የጋራ ግንዛቤ ከሌለ አካባቢውን ሊበክሉ የሚችሉ በርካታ ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ የኅብረተሰቡ የአኗኗር ደረጃ፣ የገቢ ሁኔታ፣ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ለኅብረተሰቡ ጤና መጓደል ወይም መቃናት የራሱ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ከገጠር ለየት የሚያደርገው በርካታ ምክንያቶች ሲኖሩ፣ በከተማ መኖር ለሕክምና አገልግሎት በቀላሉ ተደራሽ መሆኑ መልካም ነው፡፡ ተደራሽነቱ ከገጠር ለየት ያለ ቢሆንም፣ በከተማ ውስጥ በጋራ ተጨናንቆ ትራንስፖርት መጠቀም፣ የምግብ አዘገጃጀትና አቀራረብና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው በሙሉ ለኅብረተሰቡ ጤና መጓደል በቀላሉ ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ይህንን ስናይ በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ በሆስፒታሎች የማስፋፊያ ሥራ ሲከናወን ጤና ጣቢያዎችም ወደ 96 ደርሰዋል፡፡ በቀደመው ጊዜ ከሞላ ጎደል ስናየው በአዲስ አበባ ከአገራችን የተሻለ የጤና አገልግሎት አለ ቢባልም፣ የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡት ግን የተወሰኑት ነበሩ፡፡ አንዳንዶቹ አንድ አንድ በሽታ ብቻ የሚያክሙ ነበሩ፡፡ ቁጥራቸውም ጥቂት ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- ሆስፒታሎቹ ጥቂት ቢሆኑም የሕዝቡም ቁጥር በኢትዮጵያ ደረጃ አሁን ካለው በግማሽ ያህል ያንስ ነበር፡፡ አሁን የሚሠሩት ይህንን የሕዝብ ቁጥር አማክለው አይደል?

አቶ ግርማ፡- አዎ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 83 ዓ.ም. ላይ ከነበረበት በእጥፍ አካባቢ አድጓል፡፡ በተለይ ከየክልሉ ለሥራ ፍለጋና በኢኮኖሚ ችግር ወደ እየፈለሰ ከተማ የሚገባው የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዚህ የተነሳ የጤና አገልግሎት ፍላጎቱ አዲስ አበባ ውስጥ ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ከተማ ውስጥ ያሉት ሆስፒታሎች የሚያገለግሉት የከተማውን ሕዝብ ብቻ አይደለም፡፡ የክልል ሕዝቦችም አዲሰ አበባ እየመጡ የጤና አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ አለ፡፡ በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ የጤና አገልግሎት ፍላጎቱ እያደገ በመምጣቱ በጥቂት ሆስፒታሎች ብቻ የነበሩ አገልግሎቶች በሁሉም ተደራሽ እንደሆኑ ለማድረግ ጥረት አድርጓል፡፡ ሁሉም ሆስፒታሎች የማስፋፊያ ግንባታዎች ተደርጎላቸዋል፡፡ በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ወደ 500 ሚሊዮን ብር በመመደብ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ የነበሩት አገልግሎቶች በሁሉም ሆስፒታሎች ተደራሽ ለማድረግ ተሠርቷል፡፡   

ሪፖርተር፡- በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተጨማሪ የሆስፒታል ግንባታዎች ታስበዋል፡፡ የመሠረት ድንጋይ የተቀጠላቸውም አሉ፡፡ ይህን ቢያብራሩልን?

አቶ ግርማ፡- በርካታ ሕዝብ በሚኖርባቸው ሦስት ክፍለ ከተሞች ሦስት ሆስፒታሎች ለመሥራት የዲዛይን ሥራው ከአንድ ዓመት በላይ ፈጅቶብናል፡፡ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በላፍቶ ንፋስ ስልክና በቦሌ ክፍለ ከተሞች እጅግ ዘመናዊ ሆስፒታሎች ለማስገንባት ከአማካሪው ጋር እየተሠራ ነው፡፡ ዘመኑ የደረሰበትን የሆስፒታል ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ለመገንባት በማቀዳችን ባሰብንበት ጊዜ ግንባታውን አልጀመርነውም፡፡ በቅርቡ ለመጀመር የሚያስችሉንን ቅድመ ዝግጅቶች ስላጠናቀቅን በቅርቡ እንጀምራለን፡፡

ሪፖርተር፡- የዳግማዊ ምኒልክ ማስፋፊያ አዲሱ ሆስፒታል ዘመናዊ ኦክስጅን ማስተላለፊያን ጨምሮ የተለያዩ ፋሲሊቲዎች ያሉት ነው፡፡ የአሁኑ ግንባታ ከዚህ የተለየ ይሆናል?

አቶ ግርማ፡- ምኒልክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከርነው ቢሆንም ፈተና ገጥሞናል፡፡ እስካሁን ኦክስጅኑ እየሠራ አይደለም፡፡ ኦክስጅኑ ሲገጠም የሚከታተሉት ባለሙያዎች በዘርፉ ዕውቀት ስላልነበራቸው ፈተና ገጥሞናል፡፡ ኦክስጅን የሚመረትበት ያስፈልጋል፣ የተመረተው ኦክስጅን ለእያንዳንዱ በሽተኛ ሊደርስ ይገባል፡፡ የአገራችን መሐንዲሶች ሌሎች ሕንፃዎችና በርካታ ግንባታዎች ሠርተው ሊሆን ይችላል፡፡ የሆስፒታል ግንባታ ግን የተለየ ነው፡፡ ምሕንድስናው ላይ የሕክምና ባለሙያዎችን ማሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ የሆስፒታል ግንባታም ከሌላው የተለየ ነው፡፡ አዲስ የምንሠራቸው ሆስፒታሎች ላይ ይህ እንዳይገጥመን ከዲዛይን ጀምሮ ክለሳ አድርገናል፡፡ ለዚህም ነው ግንባታው የዘገየው፡፡   

ሪፖርተር፡- የጤና ፖሊሲው በሽታን ቀድሞ መከላከል ላይ ያጠነጠነ ቢሆንም ከ60 – 80 በመቶ ለሚሆኑ በሽታዎች መንስኤ የሆነው የቆሻሻ አወጋገድ እንዲሁም የአካባቢና የግል ንፅህና ጉድለት አዲስ አበባን እየፈተናት ነው፡፡ እንደ ጤና ቢሮ ከምትሠሩት በተጨማሪ ቆሻሻን ከሚያስወግደው መንግሥታዊ አካል ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ይመስላል?

አቶ ግርማ፡- የከተማችን የአካባቢ ጥበቃ ላይ ብዙ ሥራዎች ይጠብቁናል፡፡ ጤና ቢሮ በሽታን በመከላከል የሰው ልጆችን ንቃተ ህሊና ለማዳበርና ከዚህ በዘለለ በጤና ተቋማት እንዲታከሙ በሽታ የመከላከሉን ይሠራል፡፡ ፖሊሲያችን መሠረት ያደረገው ተላላፊውንም ተላላፊ ያልሆነውንም መከላከል ይቻላል በሚለው ላይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ትልቁ የጤና ችግር የአካባቢ ብክለት ነው፡፡ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ከተማ ውስጥ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ኅብረተሰቡ እንዴት ቆሻሻ ማስወገድ እንዳለበት እያስተማረ ነው፡፡ ቤተሰብ ቆሻሻውን ከቤት ሲያወጣ ይህንን የሚያስወግድ አካል አለ፡፡ ፍሳሹንም እንዲሁ፡፡ በርካታ የዘርፍ መሥሪያ ቤቶች ነን በየዘርፉ የምንሠራው፡፡ በጋራ ባለመሥራታችን ብዙ ችግር እየገጠመን ነው፡፡ ለበርካታ ተላላፊ በሽታዎች ሊያጋልጡ የሚችሉ ጉዳዮች አሉ፡፡ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን የምንከተል ቢሆንም፣ ከተማው ውስጥ ከአየር ብክለት ጋር በተያያዘ ከየመኪናው የሚወጣው ጭስ ከመብዛቱ የተነሳ፣ የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀቱ የመተንፈሻ አካል ችግሮች እያስከተለ መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ አስም ከዚሁ ጐን ለጐን በየሆስፒታሉና በጤና ተቋማት የሚታከሙ ሕመምተኞች ምን ምን በሽታዎች አሉባቸው የሚለው በዩኒቨርሲቲዎች ይጠናል፡፡ እነዚህ ጥናቶች የሚያሳዩት ተላላፊ ከሆኑት ባላነሰ ሁኔታ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችም እንዳሉ ነው፡፡   

ሪፖርተር፡- ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተላላፊ ከሆኑት ባልተናነሰ ሁኔታ እየተስተዋሉ ከሆነ፣ የጤና ሥርዓቱ ለዚህ በሚያመች ሁኔታ የተዘረጋ ነው?

አቶ ግርማ፡- በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ይህንን ታሳቢ አድርገናል፡፡ ሆስፒታል ስንገነባ በሽታን ቀድሞ መከላከል እንጂ ሆስፒታል መገንባት ምን ያደርጋል የሚሉን አሉ፡፡ ነገር ግን ሆስፒታሎች በሽታን የመከላከል ሥራን ነው የሚሠሩት፡፡ ለምሳሌ የሳንባ በሽታን ማከም፣ መከላከልም ነው፡፡ ስለዚህ በሽታን መከላከል ያለ ጤና ተቋም አይቻልም፡፡ በመሆኑም በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ምርመራዎችን ማድረግ የሚችሉ ተርሸሪ አገልግሎቶች መኖር አለባቸው፡፡ የሠለጠኑ የጤና ባለሙያዎችም ያስፈልጋሉ፡፡ ሆኖም በመሠረታዊነት በሽታን መከላከል ያለብን ሰው ታሞ ሳይሆን ሳይታመም ነው፡፡ ተላላፊ ያልሆኑትን በሽታዎች በአመጋገብ ሥርዓት፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ የተመጣጠነ ምግብና የአልኮል መጠጥ ሥርዓት ላይ ኅብረተሰቡን በማስተማር መከላከል ይቻላል፡፡ ለካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ነገሮች ኅብረተሰቡ እንዲቆጠብ በማድረግ መቀነስ ይቻላል፡፡ ተላላፊ የሆኑትንም ሆነ ያልሆኑትን በሽታዎች ሙሉ ለሙሉ መከላከል ባይቻልም መቀነስ ይቻላል፡፡ አገራችን ውስጥ የማህፀን በርና የጡት ካንሰር ከፍተኛ ችግር እየሆነ ነው፡፡ ችግሩ ሳይባባስ በየወቅቱ ምርመራ የሚደረግበት ሁኔታ ቢመቻች በቀላሉ በሽታውን ማቆም እንችላለን፡፡ በሽታን የመከላከልና ጤናን የማበልፀግ ሥራን ይዘን በከተማዋ 98 ጤና ጣቢያዎችና የፌዴራሎችን ጨምሮ 11 ሆስፒታሎች አሉ፡፡ ሆስፒታሎቹ በሙሉ በሥራቸው ያሉትን ጤና ጣቢያዎች እንዲደግፉ እናደርጋለን፡፡ ጤና ጣቢያዎች ደግሞ በሥራቸው ያለውን የወረዳ ሕዝብ በጤና ኤክስቴንሽን አማካይነት በመግባት፣ ሕክምና የሚፈልጉትን በቀጠናና በቤት በመለየት እየተሠራ ነው፡፡ ይህ ያስፈለገው የታመመ ሁሉ ወደ ጤና ጣቢያ ላይመጣ ስለሚችል እንዳደጉት አገሮች የግል ሐኪምና የግል ነርስ ባይኖርም፣ ሐኪም ነርስና ሌሎች የሕክምና ባለሙያዎች ያሉበት ቡድን ወደ ቤተሰብ እየሄደና በቤተሰብ ደረጃ ያለውን የጤና ችግር እየለየ ወደ ሕክምና ተቋም እንዲመጡ፣ እዚያው ቤታቸው መታከም የሚችሉትም እንዲታከሙ ከጤና ኤክስቴንሽን በዘለለ እየተሠራ ነው፡፡ በቤተሰብ ጤና ቡድን ኅብረተሰቡን ቤት ለቤት ለማከም በተለይ ተላላፊ ያልሆኑት ላይ ትኩረት ለመስጠት እየተሠራ ነው፡፡     

ሪፖርተር፡- በቤተሰብ ጤና ቡድን ወደ ቤተሰብ ገብቶ የማከሙ ሥራ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ወረዳዎች ተጀምሯል፡፡ ሙሉ ለሙሉ በከተማዋ የሚጀመረው መቼ ነው? ምን ዓይነት አካባቢዎች ቅድሚያ ያገኛሉ?

አቶ ግርማ፡- ገጠር ላይ በአብዛኛው ወጥ የሆነ አኗኗር አለ፡፡ በሀብትም ብዙም ልዩነት የለም፡፡ አኗኗሩ እንደ ከተማ የተፋፈገ ባለመሆኑ እንደ ከተማ ዓይነት የጤና ችግር የለም፡፡ በአዲስ አበባ በዓለም ከሚወዳደሩ ሀብታሞች ጀምሮ ጎዳና ላይ እስከሚያድረው ደሃ አለ፡፡ ስለሆነም ለዚህ የሚስማማ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ወደፊት መተግበር አለበት ብለን የተለያዩ የአሠራር ሥርዓቶች ዘርግተናል፡፡ ከስድስት ወራት በፊት በጉለሌ፣ በየካና በቦሌ ክፍለ ከተሞች የቤተሰብ ጤና ቡድን አገልግሎት መስጠት ጀምረናል፡፡ በዚህ ሁሉንም ቤተሰብ ለመድረስ የሚያስችል አመርቂ ውጤት አይተናል፡፡ በጣም በዝቅተኛ ደረጃ የሚኖሩትንና የጤናው ችግር በዚያው ልክ የጎላባቸውን፣ መካከለኛ ገቢ ኖሮት የከፋ የጤና ችግር የሌለበት ግን ተጋላጭ የሆነውን፣ ባለው ከፍተኛ ኢኮኖሚ የራሱን ሕክምና ድጋፍ የሚያደርግ ግን ምክር የሚፈልግ ስላለ የጤና ሥርዓቱ ይህንን መሠረት አድርጎ እንዲተገበር ይፈለጋል፡፡ አገልግሎቱን ለማስፋትና በዚህ ዓመት ከሦስት ክፍለ ከተሞች ወደ ሁሉም ለማካተት ወካይ ጥናት አድርገን ለመሥራት አቅደናል፡፡      

ሪፖርተር፡- የጤና ጣቢያዎች ቁጥር በከተማዋ ቢጨምርም ሆስፒታሎች ውስጥ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሉም፡፡ ለጤና ጣቢያዎቹ በሙሉ የሚመጥን ባለሙያ አለ? አንዳንዶቹ ጤና ጣቢያዎች ብዙም ሰው ሳያስተናግዱ ሲውሉ አንዳንዶቹ ተጨናንቀው ይታያሉ፡፡ ጠቅላላ ሆስፒታል ከተደረጉትም የጴጥሮስ ሆስፒታል ቢታይ ተገልጋይ ብዙም የለውም፡፡ ይህ ከምን የመነጨ ነው?

አቶ ግርማ፡- አዲስ አበባ ውስጥ በፊት ጊዜ አንዳንድ ሆስፒታሎች አንድ በሽታ ብቻ የሚያክሙበት ሁኔታ ነበር፡፡ ሕዝቡ አሁንም ያንን ነው የሚያውቀው፡፡ ለምሳሌ ጴጥሮስ ሆስፒታል የሳንባ በሽታን  ብቻ ያክም ነበር፡፡ አሁን በርካታ ግንባታ ተካሂዶ ጠቅላላ ሆስፒታል ሆኗል፡፡ ግን የማስተዋወቅ ሥራ ባለመሥራታችን ብዙ ሕዝብ እየተጠቀመበት አይደለም፡፡ ነገር ግን ዘመናዊና ከተማዋ ውስጥ ካሉ ሆስፒታሎች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚችል ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አማኑኤል ወይም ጋንዲ ካልሆኑ በስተቀር ሁሉም ሆስፒታሎች ጠቅላላ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ የአማኑኤልና የጋንዲ ሆስፒታሎችንም እያስፋፋን ስለሆነ ወደፊት ጠቅላላ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ከተማዋ ውስጥ ያሉት ሆስፒታሎች ውስን በመሆናቸው የሚሰጡት አገልግሎት ከአቅማቸው በላይ ነው፡፡ ስለሆነም ሆስፒታሎች ጤና ጣቢያዎችን እንዲደግፉ እየተሠራ ነው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ሆስፒታሎች የቀዶ ሕክምና መሥሪያቸውን ጤና ጣቢያ ላይ እንዲያደርጉ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ ጳውሎስ ሚሊኑየም ሜዲካል ኮሌጅ ይህንን ጀምሯል፡፡ ይህንን አሠራር ሆስፒታሎች በራሳቸው ጀምረውታል፡፡ የከተማ አስተዳደሩም የጤና ጣቢያዎችን ደረጃ በማሻሻልና በቂ የሠለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት በጤና ዘርፍ ውስጥ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት በዕቅዱ ተቀምጧል፡፡ መተግበሩ አለመተግበሩ የእኛ አቅም ቢሆንም፣ ጤና ጣቢያዎችም ልክ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲሰጡ ታስቧል፡፡ በማህፀን መውለድ የተቸገሩ በቀዶ ሕክምና እንዲወልዱ፣ መለስተኛ ቀዶ ሕክምና እንዲሠሩ፣ አስተኝተው እንዲያክሙ፣ የዓይን፣ የጆሮ፣ የጥርስና የአእምሮ ሕክምና እንዲሰጡ አደረጃጀቱን ቀይረናል፡፡ ነገር ግን ጤና ጣቢያዎችን ሆስፒታሎች ካልደገፉዋቸው ሁሉን በሽታ ለማከም የአቅም ውስንነት ይኖራል፡፡ ጤና ጣቢያዎች መሠረታዊ አገልግሎት በብዛት የሚሰጡት የእናቶች ጤና ላይ አትኩረው ነበር፡፡ የነፍሰጡር ክትትል፣ የቤተሰብ ዕቅድ፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን የሚያክሙ ጤና መኮንኖችና ነርሶች አሉ፡፡ ወደፊት እነዚህን በሁለተኛ ዲግሪ ለማሠልጠንና ሌሎች ሐኪሞችንም በጤና ጣቢያዎች ለመመደብ ታቅዷል፡፡  

ሪፖርተር፡- የካንሰር ሕክምና አገልግሎት በመንግሥት ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውጭ አለመኖር ሌላው ችግር ነው፡፡ የካንሰር ሕክምናን እንደ ከተማ ተደራሽ ለማድረግ ምን ተጀምሯል?

አቶ ግርማ፡- ጳውሎስና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም በ18 ጤና ጣቢያዎች በተለይ የካንሰር ቅድመ ምርመራው ላይ ትኩረት እንዲደረግ፣ ለሕክምናው ደግሞ በመንግሥት በኩል ጥቁር አንበሳ ብቻ ስለማይበቃ አስተዳደሩ ለካንሰር ሕክምና ብቻ አንድ ጤና ጣቢያ መድቧል፡፡ 20 ጤና ጣቢያዎች ተመርጠው አስፈላጊ ቅድመ ካንሰር መመርመሪያ መሣሪያዎች አሟልተናል፣ ባለሙያዎችም አሠልጥነናል፡፡ በዘላቂነት ከጥቁር አንበሳ ጋር በመሆን በመሠረታዊነት ሁሉም ጤና ጣቢያዎች ቅድመ የካንሰር ምርመራ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እየሠራን ነው፡፡ እንደ ከተማም ሕክምናውን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብቻ መስጠቱ ቅሬታ እያስነሳ ነው፡፡ ከካንሰር በተጨማሪም ከፍተኛ በጀት ተመድቦም ከዘውዲቱና ከጳውሎስ ሆስፒታሎች በተጨማሪ በምኒልክ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ለመጀመር እየተሠራ ነው፡፡   

ሪፖርተር፡- አዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ወይም ተቆጣጥራቸው የጠፉ እንደ ዝሆኔ፣ ከቅማል ጋር የተያያዙ ተላላፊና ሌሎች በሽታዎች ዳግም እየታዩባት ነው፡፡ ይህ ከምን የመነጨ ነው? ከተማዋስ ለእነዚህም ምላሽ የሚሰጥ የጤና ሥርዓት ዘርግታለች?

አቶ ግርማ፡- ቁጥጥሩ አለ፡፡ ዋና ዋና የኅብረተሰብ ጤና አደጋ የሆኑትን የምንቆጣጠርበት የበሽታ ቅኝት ሥርዓት አለን፡፡ በእያንዳንዱ ወረዳም ሙያተኞች መድበናል፡፡ ለኅብረተሰብ ጤና አደጋ ከሆኑት ዋና ዋናዎቹ 20 በሽታዎች ተለይተው የምንከታተልበት ሥርዓት አለን፡፡ በመሆኑም የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች በየዕለቱ ሪፖርት የሚደረጉበት አሠራር አለ፡፡ ያልተለመደ በሽታ ሲከሰት ለምሳሌ አተት ሲከሰት ወዲያው ታውቋል፡፡ እኛም የምንከታተልበት ሥርዓትም አለ፣ ችግሩም በየጊዜው ይከሰታል፡፡ የአኗኗር ዘይቤያችን በጣም አስቸጋሪ በሆነበት፣ ሦስት በአራት በማይሞላ በአንድ ክፍል ውስጥ እስከ 40 ሰው የሚያድርበት፣ በትንሽ ክፍያ ተጨናንቀው አድረው ወደ ክልል ወይም እዚሁ ለሥራ የሚወጡ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ተላላፊ በሽታዎች ይኖራሉ፡፡ በተለይ ከቅማል ጋር ተያይዞ የትኩሳት ግርሻ ብዙ ጊዜ ይከሰታል፡፡ ታይፎይድም በከፍተኛ ሁኔታ እየተከሰተ ነው፡፡ አዲስ ከተማ፣ አራዳ ላይ ይከሰታል፡፡ ቀድሞ መከላከል ዋናው ቢሆንም፣ የእኛ ባለሙያዎች ደርሰው የሚያክሙት ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ይህንን የሚከላከል ሥርዓት የለንም?

አቶ ግርማ፡- መደበኛውን ኅብረተሰብ ቤት ለቤት በመሄድ በማስተማር የግልና አካባቢ ንፅህናውን እንዲጠብቅ በመድረስ ቀድሞ በሽታን እንዲከላከል ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከተማ ውስጥ ከአቅም በላይ የሆነብን ችግር ለተለያየ ሥራ ከተማ ውስጥ በጎዳናና ባልተስተካከለ የኑሮ ሁኔታ የሚኖሩትን መድረስ ነው፡፡ በከተማዋ በርካታ ሰዎች በየሥርቻውና በሕገወጥ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ታዝበናል፡፡ ይህ ለበርካታ በሽታ መንስኤም ነው፡፡ በጎዳና የሚኖሩትንም፣ ደረጃውን ባልጠበቀ ቤት ውስጥ ያሉትንም ከማስተማር የዘለለ ብዙም አቅም የለንም፡፡ ውኃና መፀዳጃ እንዲኖራቸው ከሚመለከተው አካል ጋር መሥራት ነው፡፡ በአጠቃላይ የከተማው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ሲቀየር ብቻ ነው ለውጥ ማምጣት የሚቻለው፡፡ ከጎዳና ጀምሮ ሰዎች ሲታመሙ ግን ነፃ ሕክምና እንዲያገኙ እየሠራን ነው፡፡ በጎዳና የሚኖሩ በርካቶች እንዲታከሙ፣ ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ፣ ሥራ መሥራት የሚችሉት እንዲሠሩ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን በየቀኑ ከተማ ውስጥ የሚገባ ሰው በርካታ ከመሆኑ የተነሳ የአዲስ አበባን የጤና ችግር ለመፍታት በጣም ከባድ ነው፡፡ በሁሉም የከተማዋ አካባቢ የግልና የአካባቢ ንፅህናን ካላስጠበቅን፣ ውኃና መፀዳጃ ካልገባ፣ የፍሳሽ ማስወገጃዎች ሥርዓት ካልያዙ፣ ውኃና መፀዳጃ በማያገኙ አካባቢዎች መሠረታዊ ኑሮን መቀየር ካልቻልን ጤና የሚባል ነገር አይረጋገጥም፡፡     

Standard (Image)

‹‹ብዙ ወላጆች ሳያውቁ ያጠፉ ይመስለኛል›› ወ/ሮ ናርዶስ ማሞ ደስታ፣ ሳይኮቴራፒስት

$
0
0

ወ/ሮ ናርዶስ ማሞ ደስታ ትባላለች፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በሶሻል ወርክ በአሜሪካ ካንሳስ ዩኒቨርሲቲ፤ ሁለተኛ ዲግሪዋንም የአእምሮ ጤና ላይ በማተኮር በሶሻል ወርክ ሠርታለች፡፡ ከዚያም በሳይኮ ቴራፒስትነት ዕውቅና አግኝታ መንቀሳቀስ ጀመረች፡፡ በአሁኑ ወቅት በቡድንና በግለሰብ ደረጃ አእምሮ ጤና ላይ የምክር አገልግሎት በሚሰጠው ማይንድሴት (mindset) ክሊኒካል ዳይሬክተር ሆና በመሥራት ላይ ትገኛለች፡፡ በተቋሙ ከምክር አገልግሎት ጋር የሚያያዙ ሥራዎችን ትመራለች እንደ ባለሙያነቷም የምክር አገልግሎት ትሰጣለች፡፡ ከአእምሮ ጤና ችግር ጋር በተያያዘ የተገልጋዮች የአእምሮ ችግሮችን በመረዳት የምክር አገልግሎት መሻትን በሚመለከት የሚስተዋሉ እውነታዎችን እንዲሁም በተቋሙ የምክር አገልግሎት ምን እንደሚመስል ምሕረት አስቻለውከወ/ሮ ናርዶስ ማሞ ደስታ ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች፡፡

ሪፖርተር፡- የምክር አገልግሎት የምትሰጡት ለማን ነው?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- የአእምሮ ጤና መዛባት ችግር ላለባቸው ብቻም ሳይሆን ለቤተሰብ እንዲሁም የአእምሮ ችግር ያለባቸውን ለሚንከባከቡ ነው፡፡ ተቋሙ በዚህ መልኩ የምክር አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከሞላ ጎደል አንድ ዓመት ሊሆን ነው፡፡ የምናየው በተለያየ መንገድ የአእምሮ መዛባትና የሥነ ልቦና ችግር ያጋጠማቸውን ነው፡፡ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ሱስና ሌሎችም ችግሮችን እናያለን፡፡ ከዕድሜ አንፃር ደግሞ ከሕፃናት እስከ አዋቂዎች እንመለከታለን፡፡ እኔበተለይ ሕፃናት ላይ እሠራለሁኝ፡፡ እስካሁን ከአምስት ከስድስት ዓመት ሕፃናት ጀምሮ እስከ ስልሳ ዓመት ዕድሜ ያላቸውን አይቻለሁኝ፡፡ ወጣቶችና ታዳጊ ወጣቶች ላይ በተይም ከሱስ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ሰጥቻለሁ፡፡  

ሪፖርተር፡- በኅብረተሰቡ ዘንድ የአእምሮ ችግሮችን የማወቅና የመረዳት ችግር አለ፡፡ በሌላ በኩል መፍትሔ ለመፈለግ የሚኬድበት አቅጣጫም የተሳሳተ ሲሆን፣ በስፋት ይስተዋላል፡፡ በዚህና በመሰል ሁኔታዎች ውስጥ ወደ እናንተ አገልግሎት ሽቶ የመምጣት ነገር እንዴት ይታያል?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- መጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ያጋጠመኝ ነገር ችግሩ በንግግር ይድናል ብሎ አለማሰብና አለማመን ነው፡፡ እዚህ ቢሮ ገብቼ የአእምሮ ጤና ላይ ከሥነ ልቦና አንፃር መሥራት እችላለሁ ማለት አልቻልኩም ነበር፡፡ የተለያዩ ሰዎችና ተቋማትን አናግሬአለሁኝ የነበረው ነገር ከተማ ተመሥርቶ መንገድ የሌለው ያህል ነበር፡፡ ችግር ያለባቸው ሔዱ ከተባለ የሚሔዱት የሥነ አእምሮ (Psychatrist) ባለሙያ ጋር እንጂ ከእሱ ቀጥሎ የሥነ ልቦና ባለሙያ ማማከርን አያስቡትም፡፡ አገልግሎት የጀመርኩት ሌላ ቦታ ነበር፡፡ ለማማከር የሚመጣ ሰው አልነበረም፡፡ ከመጣሁኝ ሦስት ዓመት ሆኖኛል ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት እዚህ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊ ሳይኮ ቴራፒስቶችን መፈለግ ጀመርኩ ሳልመጣ አጠያይቄ አንድ ሰው መኖሩን አውቄ ነበር እዚህ ስመጣ ደግሞ ሁለት ሦስት ብቻ እንደነበሩ ተረዳሁኝ፡፡   

ሪፖርተር፡- ታዲያ እንዴት ወደ ሥራ ልትገቢ ቻልሽ?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- አንድ የግል ክሊኒክ ውስጥ ራሴ ሜዲካል ዳይሬክተሩን አናግሬ የሕክምና ክፍሉ እንዲከፈት አደረግን፡፡ በመጀመሪያዎቹ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብዬ አንድ ሁለት ሰው ብቻ ነበር የማናግረው፡፡ ነገር ግን የሕክምና ባለሙያዎችም ተገልጋዩም አገልግሎቱ መኖሩን ሲያውቁና ጥቅሙን ሲረዱ ነገሮች እየተለወጡ ይመጣሉ፡፡ አሁን በጣም ጊዜ የለኝም ማለት እችላለሁኝ፡፡ አገልግሎቱ መኖሩን አለማወቅ እንጂ አገልግሎቱ መኖሩን ካወቀ ኅብረተሰቡ ፍገለጎት እንዳለው የሚያሳዩ ነገሮች አሉ፡፡ አገልግሎቱን ፈልገው የሚመጡ ገቢያቸው ጥሩ የሆነ ያልሆነም ናቸው፡፡ በፊት ከነበረው አንፃር ብዙ ለውጦችና መሻሻል አለ፡፡   

ሪፖርተር፡- ዛሬ በቂ መረዳት ወይም ግንዛቤ አለ ማለት እንችላለን?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- ይህን ማለት እንኳ አይቻልም፡፡ ለምሳሌ ለሳይኮ ቴራፒስት አገልግሎት የሚከፍሉት ለሳይካትሪስትና ለማንኛውም ዓይነት ሀኪም ከሚፈፍሉት በንፅፅር ከፍ ያለ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሳይኮ ቴራፒስቱ ጋር የሚያጠፉት ጊዜም በአሥር እጥፍ የሚጨምር ነውና፡፡ ከዚህና ከሌሎችም ነገሮች አንፃር ዋጋው ለምን ከፍ አለ የሚሉ አሉ፡፡ ቢሆንም ግን ብዙዎች ተጠቅመውበት ሲመለከቱ ያምናሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ከዋጋው ባሻገር የግንዛቤ ችግሮችስ?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- በቂ ነው ባልልም ግንዛቤውም ከድሮው የተሻለ ነው፡፡ በመጀመሪያ ይህ ነገር የአእምሮ ጤና መዛባት እንዳይሆን ብሎ ነገሮችን የመከታተልና የማየት ነገር የለም፡፡ የአእምሮ ጤና ችግርን በአንድ የመጠቅለል ነገር ነው ያለው፡፡ ድብርት ነው ወይስ ጭንቀት ብሎ የመለየት ነገር የለም፡፡ በሌላ በኩል የአእምሮ ጤና መዛባትን ከሀይማኖትና ከባህል ጋር የማያያዝ ነገር አለ፡፡ ችግሩ ሀኪም ማማከር ያስፈልገዋል ወይ? ችግሩ ያጋጠመውን ሀኪም ጋር ልውሰደው አልውሰደው የሚለውን ለማማከር ወደ እኛ ከሚመጣው የማይመጣው ይበልጣል፡፡ በጊዜ መታከም ሲችል ረዥም ጊዜ የወሰደበት ሰውም ብዙ ነው፡፡ ሱስ የአእምሮ ጤና ችግር መካከል እንደሆነ አለማወቅም ሌላው ነገር ነው፡፡ ቢሆንም እያየን ያለነው ለውጥ አበረታች ነው፡፡ በእምነት አባቶች ከፀበል ወደ ሀኪም የተላኩ መኖራቸውን ማየት ተስፋ አለን ያሰኛል፡፡   

ሪፖርተር፡- ለውጦች ቢኖሩም በማኅበረሰቡ ከአእምሮ ጤና ጋር የተያያዘው ችግር ሰፊ ነው፡፡ የተሻለ ግንዛቤ እንዴት መፍጠር ይቻላል?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- ከተለያዩ ሰዎች ጋር ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ እሠራለሁኝ፡፡ ሥራው ከታች መጀመር አለበት እላለሁኝ፡፡ ብዙዎቹ የአእምሮ ጤና መጓደሎች በሀያዎቹ መጀመሪያ ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ቤተሰብ ውስጥ፣ ትምህርት ቤት ሥራውን መጀመር ይገባል፡፡ ልጆች ያለባቸው የጤና ችግር የእነሱ ጥፋት እንዳልሆነ፤ መፍትሔም እንዳለው ሊነገራቸው ይገባል፡፡ የአእምሮ ጤና መጓደል በቀላሉ በመድሃኒት ወይም በመመካከር ሊታከሙ እንደሚችሉ ለተማሪዎች፣ ወጣቶችና ወላጆች መንገር ትልቅ ነገር ነው እላለሁኝ፡፡ ስለዚህ ውይይቱ ከታች መጀመር አለበት በዚህ ብዙዎች መረዳት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ መገናኛ ብዙኃንም እዚህ ላይ ሚናቸው ከፍተኛ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የአእምሮ ጤና መጓደልን በፊልሞች የማንፀባረቅ ሙከራዎች በተለያዩ የአገራችን ፊልሞች ታይተዋል፡፡ እዚህ ላይ ምን አስተያየት አለሽ?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- የአእምሮ ጤና ችግሮችን በአንድ ጠቅልለው ያስቀምጣሉ፡፡ በተሳሳተ መልኩ መጓደሎቹን የማስቀመጥ ነገርም ጭምር አለ፡፡ ብዙ ሰው የሚማረው ከፊልም፣ ከድራማ ከመሆኑ አንፃር በመገናኛ ብዙኃን በድራማና በፊልም የአእምሮ ጤና መጓደሎች የተለያዩ መሆናቸው እያንዳንዳቸውም በትክክል መሳል ሲችሉ ግንዛቤ መፍጠር ይቻላል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውጤቱ በተቃራኒው ይሆናል፡፡ ለዚህ ከባለሙያ ጋር መሥራት አስፈላጊ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የማኅበረሰቡ ኑሮ ሩጫ የበዛበት በመሆኑ የአኗኗር ዘዬ ግለኝነት እያመዘነበት አንዱ ለአንዱ ድጋፍ መሆን የማይችልበት ጊዜ ነው፡፡ በሌላ በኩል የኑሮ ሸክም ከባድ በመሆኑ ሰዎች ሁለት ሦስት ሥራ በመሥራት ውጥረት ውስጥ የገቡበት ወቅትም ነው፡፡ ከዚህ ከዚህ አንፃር ወደ እናንተ ብዙ የሚመጡ ኬዞች እንዴት ያሉ ናቸው?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- ማይንድ ሴት የምክር አገልግሎት ማዕከል እንደመሆኑ የከፋ የአእምሮ ችግር፣ ተኝተው መታከም ያለባቸው መድሃኒት የሚያስፈልጋቸውም ወደ እኛ አይመጡም፡፡ ስለዚህ እኛ ጋር የሚመጡት የሥነ ልቦና ሳይኮ ቴራፒ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ እነዚህ መድሃኒት እየወሰዱ ጎን ለጎን ሳይኮ ቴራፒ የሚያስፈልጋቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ድብርት፣ ጭንቀት፣ ሱስ ችግር ያለባቸው በብዛት ይመጣሉ፡፡ እውነት ነው በፊት ለዕርዳታ ይዘረጉ የነበሩ እጆች ሰሚ ጆሮዎች ዛሬ የሉም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ጠንካራ ስሜቶችን ከእኛ ጋር መጥተው ያወጣሉ፡፡ 

ሪፖርተር፡- የታዳጊ ወጣቶች በሱስ መጠመድ የብዙ ወላጆች እራስ ምታት ሆኗል፡፡ ልጆቻቸውን ትልልቅ ትምህርት ቤት፤ የሕዝብም የላኩ ወላጆች ችግር ውስጥ ናቸው፡፡ አንዳንድ ልጆች ያሉበት ሁኔታ ወላጆቹ ልጆቻችንን አናውቃቸውም እስከማለትና አለማመን ይደርሳል፡፡ በዚህ መልኩ አንቺ ጋር የመጡ ስንቶች ናቸው?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- በጣም ብዙ፡፡ የምረዳቸው ብዙ ተማሪዎችና ወጣቶች አሉ፡፡ የሚታየው ነገር አገራችን ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች ያሳያል ምክንያቱም ሱስ ሆ ተብሎ የተጀመረ ነገር ሆኗል፡፡ በጣም ጥሩ፣ መንፈሳዊ የሚባለው የትኛውም ትምህርት ቤት ከዚህ ችግር ውጭ አይደለም፡፡ የሚያስፈራ ነገር ነው፡፡ ይህ ችግር በአንድ ለአንድ ምክክር የሚፈታ ሳይሆን ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር የሚጠይቅ ነው፡፡ ልጆች መመራት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስለዚህ ከአስተማሪዎችና ከትምህርት ቤቶች ጋር ትልቅ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡  

ሪፖርተር፡- በተለያየ መንገድ ሮጠው እየለፉ ልጆቻቸው የጠየቁትን ሁሉ የሚያሟሉ ነገር ግን የልጆቻቸውን ትክክለኛ ባህሪና አዋዋል ለመረዳት ጊዜ የሌላቸው ወላጆች ብዙ ናቸው?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- ብዙ ወላጆች ሳያውቁ ያጠፉ ይመስለኛል፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የማያውቁ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከውጭ አገር ባህል ስንወስድ ጥሩ ጥሩውን የልጅ አስተዳደግ አልወሰድንም የተማሩ ወላጆች የኑሮ ዘዬ ፊልም ላይ እንደምናየው አይደለም፡፡ የድሮ ወላጆች መግረፍ ልጅ የሚለውን መስማት አለመፈለግ ትክክል አልነበረም እኔ እንደ እናት አባቴ አላሳድግም ያለ ወላጅ በተለያየ አጋጣሚ ውጭ ሲሔድ ፊልም ላይ ይቃርምና ያን ይከተላል፡፡ በእርግጥ ባለሙያም ቢሆን ልጅ ሲያሳድግ ሁሉን አያውቅም እየሞከረ እያየ ነው፡፡ ነገር ግን ወላጆች ማድረግ ያለባቸው ቆም ብለው የአስተዳደጋቸውን ተፅዕኖ መገምገም ነው፡፡ ለዚህ ብዙ መጽሐፍ ማንበብ ይቻላል ከኢንተርኔትም ብዙ ይገኛል የዚህን ዓመት ሕፃን እንዴት ሥነ ሥርዓት ማስተማር እችላለሁ በሚለው ቢፈለግ ብዙ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ችግሩ ቆም ብለን አናይም፡፡ የሥነ ልቦና ባለሙያም ልጄ እንዲህ እንዲህ እየሆነ ነው ምን ልጠርጥር ምን ልፍራ ብሎ ማማከርም ይቻላል፡፡ ልጆችን ማዳመጥ፣ ለልጆች ትኩረት መስጠት፣ አስጠኚ መቅጠር ጥሩ ትምህርት ቤት መምረጥ ወላጆች ላይ የሚታይ ጥሩ ነገር ነው፡፡ በተቃራኒው ልጆችን እንደፈለጋችሁ ሁኑ ማለት የፈለጉትን ሁሉ መስጠት ትክክል አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- ለልጆች የፈለጉትን ሁሉ መስጠት ምን ማለት ነው?

ወ/ሮ ናርዶስ፡- ለልጆች የፈለጉትንና የጠየቁትን ሁሉ መስጠት ደስታቸውን መንፈግ ነው፡፡ አንድ መጫወቻ የተገዛለትና አሥር የተገዛለት እኩል በመጫወቻዎቹ አይደሰቱም፡፡ አንድ የተሰጠው ያን አንድ ያከብረዋል፣ ለረዥም ጊዜ ይጫወትበታል አያያዙም ጥሩ ይሆናል፡፡ በጣም ብዙ ያለው ግን ይሰለቸዋል፡፡ ሌላም ሌላም ይፈልጋል፡፡ ልጆች ሥሥትን ይወቁ ባይባልም የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ ዋጋ ሳይከፍሉበት ማግኘት ለእውነተኛው ዓለምም አያዘጋጃቸውም፡፡ ምክንያቱም ከፈለግክ ታገኛለህ ነው እንጂ ከፈለግክ ትሠራለህ ታገኛለህን አይደለም የሚያውቁት፡፡  

Standard (Image)

‹‹የከተማ ጤና ራሱን ችሎ እንደ አንድ አጀንዳ ሊሠራበት ይገባል››

$
0
0

አቶ ኅብረት ዓለሙ፣ በጄኤስአይ የከተማ ጤና  ማጠናከሪያ ፕሮግራም ፕሮጀክት ኃላፊ

ጆን ስኖው ኢንኮርፖሬትድ ጄኤስአይ የተቋቋመው ከ20 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ቦስተን ከተማ ነው፡፡ የጤና ፕሮግራሞችን ቀርጾ በመተግበር ይታወቃል፡፡ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ከአሜሪካ የዕርዳታ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ነው፡፡ በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ አገሮችና የዓለም ክፍሎችም ይሠራል፡፡ ፕሮግራሙ በአገሪቱ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አራት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ አቶ ኅብረት ዓለሙ ጄኤስአይ ከሚያስፈጽማቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የከተማ ጤና ማጠናሪያ ፕሮግራም ፕሮጀክት ኃላፊ ናቸው፡፡ አብዛኛውን ሥራዎቹን የሚሠራው ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከጤና ቢሮዎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በአገሪቱ ምን ዓይነት ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ፣ እንዲሁም በከተማ ጤና ዙሪያ ባሉ ጉዳዮች ላይ ሻሂዳ ሁሴንአነጋግራቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡-  ጄኤስአይ በአገሪቱ መስራት የጀመረው በምን ዓይነት ፕሮግራም ነበር? በየትኞቹ የአገሪቱ ክፍሎችስ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ያደርጋል?

አቶ ኅብረት፡- በደቡብ ክልል መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ለኢትዮጵያ የሚል ፕሮጀክት ይዞ ነበር በአገሪቱ መሥራት የጀመረው፡፡ በወቅቱ የተሠራው ሥራ ጥሩ የሚባል ውጤት በማስመዝገቡ የፕሮጀክቱ ሁለተኛው ክፍል ደቡብን ጨምሮ በኦሮሚያና በአማራ ክልል መተግበር ጀመረ፡፡ የሕፃናትን ጤና ማሻሻል፣ የጤና ዘርፉን የገንዘብ አሰባሰብና አጠቃቀም ማሻሻል፣ ማኅበረሰቡ ከጤና ዘርፉ ጋር ተቆራኝቶ መሥራት እንዲችል ለማድረግ የማኅበረሰብ ንቅናቄ ሥራዎችን መሥራት በፕሮጀክቱ  ሲተገበሩ የነበሩ ሥራዎች ናቸው፡፡ ድርጅቱ ከሚተገብራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች መካከል የከተማ ጤና ፕሮግራም አንዱ ነው፡፡

ሪፖርተር፡‑ ፕሮጀክቱ ከከተማ ጤና ጋር በተያያዘ ምን ይሠራል?

አቶ ኅብረት፡‑ በአገሪቱ የተለያዩ ሴክተሮች እያደጉ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከተሜነት ዋናው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ባለው መረጃ መሠረት ከ18 እስከ 20 ሚሊዮን የሚሆነው የአገሪቱ ሕዝብ የሚኖረው በከተሞች ነው፡፡ አገሪቱ የያዘቻቸው የኢኮኖሚ ስትራቴጂዎች ከተሜነትን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ ስለዚህም አገሪቱ በያዘችው የዕድገት አቅጣጫ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሊሄድ ይችላል፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄ ከተማ ውስጥ የሚኖረው ሰው ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ለዚያ የሚመጥን የጤና ሥርዓት አለን ወይ? አሁን በከተማ ውስጥ ያለው የጤና አሰጣጥ ያንን መቋቋም ይችላል ወይ? የማይችል ከሆነ ደግሞ እንዴት ነው ከወዲሁ መዘጋጀት የምንችለው? የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ካልተዘጋጀን ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ከሆኑ በኋላ መመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡ ከሌሎች አገሮችም የምንማረው ይህንኑ ነው፡፡ አገሪቱ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ትሰለፋለች ይባላል፡፡ ለዚያ የሚሆን መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በከተሞች እንዲኖር የመንግሥትን ጥረት የመደገፍ ሥራ እንሠራለን፡፡ እኛ ጥገኝነትን መፍጠርም ሆነ ሁሉን ነገር እኛ እያቀረብን በእኛ ላይ ብቻ እንዲቆም አንፈልግም፡፡ ቀዳሚ ተግባራችንም የጤና አሰጣጥ ሥርዓቱ ያሉበትን ጥቃቅን ክፍተቶች በመሙላት ቀጣይነት እንዲኖረው ማስቻል ነው፡፡ ሥራችንንም የምንሠራው በከተማ ጤና ሥርዓቱ ላይ ያሉ ክፍተቶችን እያጠናን ነው፡፡

እገዛ የምናደርገውም በአራት በተለያዩ የጤና ዘርፎች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽነት ማሻሻል ነው፡፡ በዚህ ረገድ የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች መስጠት የሚገባቸውን አገልግሎት ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሰጡ፣ ሥልጠና በመስጠትና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ስራቸውን በተገቢው መልኩ እንዲያከናውኑ እገዛ እናደርጋለን፡፡

ማኅበረሰቡን በማስተማርና የተለያዩ መገናኛ አውታሮችን በመጠቀም መረጃ በመስጠት ሕዝቡን የምናነቃበት ሥራም አለን፡፡ በጤናው ሴክተር ያለውን የሰው ኃይል የአስተዳደርና የመሪነት ሥልጠና በመስጠት የአቅም ግንባታ ሥራ የመሥራት፣ መረጃ ማሰባሰብና መረጃውን ተንተርሶ ክፍተቶችን የመሙላት እንዲሁም በጤናው ላይ ያሉ ጉዳዮችን  ባለድርሻ አካላት በየጊዜው እየተገናኙ እንዲወያዩ፣ ችግሮችን ለይተው መፍትሔ እንዲሰጡ፣ የከተማን የጤና ሥርዓት የማደራጀትና የማጠናከር ሥራም እንሠራለን፡፡

ሪፖርተር፡‑ የከተማ ጤና ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው በየትኞቹ የአገሪቱ ክፍሎች ነው?

አቶ ኅብረት፡‑ ፕሮጀክቱ የተጀመረው ለ49 ከተሞች ድጋፍ እንዲያደርግ ነው፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታትም 47 ከተሞችን ስንደግፍ ቆይተናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁለት ከተሞችን ጨምረን የከተሞቹን ቁጥር 49 አድርሰናል፡፡ ጋምቤላ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ሲቀሩ በሌሎቹ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች እንሠራለን፡፡ ትላልቅ ከተሞች በፕሮግራሙ ታቅፈዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የጤና ችግር ባለባቸው አምስት ክፍለ ከተሞች ላይ እንሠራለን፡፡ አዲስ አበባ የተለያየ ማኅብረሰብ ክፍል የሚኖርባት ከተማ ነች፡፡ የተሟላ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ የራሳቸው ሐኪም ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ በጣም አስቸጋሪ በሆነ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖሩ የተወሳሰበ የጤና ችግር ያለባቸውና ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ለመታከም እንኳን የሚፈሩ ሰዎች አሉ፡፡ እኛም ትኩረታችንን አድርገን የምንሠራው በእነዚህ ሰዎች ላይ ነው፡፡

ሪፖርተር፡‑ በዋናነት የምትሠሩት በየትኞቹ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ ነው?

አቶ ኅብረት፡‑ የከተማ የጤና ችግር ብዙ ቢሆንም የእኛ አብዛኛው ትኩረታችን የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ የሥነ ምግብ ጉዳዮች፣ የቤተሰብ ምጣኔ፣ ኤችአይቪና ቲቢ ላይ ነው፡፡ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እየበዙ መምጣታቸውን እናውቃለን፡፡ ግን የእኛ ፕሮግራም ዓላማ በእነዚህ ላይ ብቻ ነው፡፡

ሪፖርተር፡‑ ከምትሠሩባቸው ከተሞች መካከል ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር ያለበት የትኛው ነው?

አቶ ኅብረት፡‑ የእኛን ከተሞች በሦስት መድበን ልናያቸው እንችላለን፡፡ አዲስ አበባ የክልል ከተሞችና የወረዳ ከተሞች አሉ፡፡ እነዚህ እንደየደረጃቸው ያሉባቸው ችግሮች ይለያያሉ፡፡ ለእኔ አዲስ አበባ የተለየ ከተማ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ችግርና የሌሎች የክልል ከተሞች ችግር የተለያየ ነው፡፡ አዲስ አበባ እንደ ሌሎቹ የክልል ከተሞች ወጥ የሆነ ባህል የላትም፡፡ የህዝቡ ብዛትም ከሌሎቹ የተለየ ነው፡፡ ከተማው ከተለያዩ አካባቢዎችና ክልሎች የሚመጡ ሰዎች የሚኖሩበት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች አዲስ አበባ ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት ውስብስብ ያደርጉታል፡፡ ለምሳሌ ከፅዳት፣ ከቆሻሻ ማስወገድ ጋር ተያይዞ ያለው ችግር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በቅርቡ ተከስቶ የነበረው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ክስተትም ያሳየን ይህንኑ ነው፡፡ በከተማይቱ ያለው ቆሻሻ የማስወገድ ሥራ ገና ብዙ ልፋት ይጠይቃል፡፡ ሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ችግር ቢኖርባቸውም አስፈላጊ የሚባሉ ሴክተሮችን አንድ ላይ አገናኝቶ ሥልጠና መሰጠት ካለበትም ሰጥቶ ማሠራት ይቻላል፡፡ ብዙ አይከብድም፡፡ አዲስ አበባ ላይ ግን ቀላል አይደለም፡፡ አስቸጋሪነቱ እንደ አዲስ አበባ አይደለም፡፡ ትንንሾቹ የወረዳ ከተሞች ላይ ደግሞ ያንን ያህል ከባድ አይደለም፡፡ የከተማ ጤና ፕሮግራሙም ወደፊት አዲስ አበባን፣ ባህርዳርን፣ ሐዋሳን እንደሚያክሉ ታሳቢ በማድረግ ትኩረቱን በእነሱ ላይ አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ ሪፖርተር፡‑ ድርጅታችሁ በኤችአይቪ ዙሪያ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ ለመሆኑ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው የኤችአይቪ ሥርጭት ምን ይመስላል?

አቶ ኅብረት፡‑ አሁንም ድረስ ኤችአይቪ በተወሰኑ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ላይ በስፋት ይታያል፡፡ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ቤት ለቤት እየሄዱ ለኤችአይቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን እንዲመረመሩ ያስተምራሉ፡፡ ጤና ጣቢያ ሄደው መመርመር ባይፈልጉ እንኳን እዚያው ቤታቸው ውስጥ ሆነው በጤና ኤክስቴንሽን ሠራኞች እንዲመረመሩ እናደርጋለን፡፡ በአጠቃላይ ግን ኢትዮጵያ የኤችአይቪ ሥርጭትን መቆጣጠር ችላለች፡፡ ከፍተኛ የሆነ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል፡፡ መከላከል ላይ አተኩሮ መሠራቱም ጥሩ የሚባል ለውጥ እንዲታይ ዕድል ሰጥቷል፡፡ በአገሪቱ የነበረውን የኤችአይቪ ሥርጭትም ወደ 1.14 በመቶ ማውረድ ተችሏል፡፡ በገጠር ያለው የሥርጭት መጠን 0.6 በመቶ ሲሆን በከተማ ደግሞ 4.2 በመቶ ነው፡፡ነገር ግን አሁን ነገሮች ጥሩ ሆነዋል በሚል መዘናጋት እንዳይፈጠር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ችግሩም ወዲያው የሚታይ ሳይሆን ከጊዜ በኋላ ነው፡፡ ተገቢው ጥንቃቄ ሳይደረግ ቀርቶ አገሪቱ  በኤችአይቪ ወረርሽኝ ዳግም እንዳትመታ ህዝቡን የመቀስቀስና የማስተማሩ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የምንሠራው ሥራም ይህንኑ ነው፡፡ ለኤችአይቪ ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰቡ ክፍሎች በተለይም ሴተኛ አዳሪዎች ኮንዶም የሚያገኙበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡ የወጣት ማዕከላት ላይም እየተገኙ ስለ ሥነ ተዋልዶ ጤናና ስለኤችአይቪ እንዲያስተምሩ እናደርጋለን፡፡ ትምህርት ቤቶች ላይም ያስተምራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከአምስትና ከስድስት ዓመታት በፊት የነበረውን ንቅናቄ አሁን ላናይ እንችላለን፡፡ ኤችአይቪ በከተሞች ላይ ትልቅ ችግር ነው፡፡ መዘናጋት አያስፈልግም፡፡

ሪፖርተር፡‑ ከሥነ ምግብ ጋር በተያያዘ በአገሪቱ ትልቅ ችግር እንዳለ ይነገራል፡፡ የችግሩ መጠን ምን ያህል ነው? እናንተስ በዚህ ረገድ ምን ትሠራላችሁ?

አቶኅብረት፡‑ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የአመጋገብ ሁኔታን በሦስት መንገዶች እንለካለን፡፡ ሕፃኑ ለዕድሜውና ለቁመቱ የሚመጥን ክብደት እንዲሁም ለዕድሜው የሚስተካከል ቁመት አለው ወይ? የሚሉትን እናያለን፡፡ በዚህ መሰረት በተሰራ ጥናት በአገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ የማግኘት ችግር መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ በአገሪቱ ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ ሕፃናት መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት የተመጣጠነ ምግብ ባለማግኘታቸው የቀነጨሩ ናቸው፡፡ 8.7 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከቁመታቸው ጋር የማይመጣጠን ክብደት ያላቸው ናቸው፡፡ 13.4 በመቶዎቹ ከመደበኛው ክብደት በታች ናቸው፡፡ ገጠር ላይ  ፕሮዳክቲቭ ሴፍቲኔት የሚባል የመንግሥት ፕሮግራም አለ፡፡ በዚህ ፕሮግራም በምግብ ራሳቸውን ያልቻሉ አርሶ አደሮች በሴፍቲኔት ታቅፈው ሥራ ይሠራሉ፡፡ ለሠሩበት ሥራ በምግብ ይከፈላቸዋል፡፡ የተወሰኑ ከተሞችም የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡ በዚህ ላይ እኛ የሚኖረን ዋናው ሚና ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሕፃን ከተወለደ እስከ ስድስት ወር ድረስ ጡት ብቻ ነው መጥባት ያለበት፡፡ ነገር ግን ከተማ ላይ ያለው ኅብረተሰብ ይህንን ያምናል ወይ የሚለው ነገር አጠያያቂ ነው፡፡ ይህንን በጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች አማካይነት ኅብረተሰቡን እናስተምራለን፡፡ ሠራተኞቹ እናትየው በወለደች በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲጎበኟት፣ ድጋፍ እንዲያደርጉላት እናደርጋለን፡፡ ሕፃኑ ከእናት ጡት በተጨማሪ ምግቦችን መመገብ በሚያስፈልገው ጊዜም ምን ዓይነት ምግብ መመገብ አለበት የሚለውን እንዲያስተምሯቸው ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ዕርዳታ ያደርጉላቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- በሥራችሁ ላይ ምን ዓይነት ችግሮች ያጋጥሟችኋል?

አቶ ኅብረት፡- እኛ የምንደግፋቸው ወደ 2,200 የሚሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አሉ፡፡ በሥራ ላይ የሚያስቸግሯቸው ነገሮች እንዳሉ ጠይቀናቸው ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ በሚሰሩበት ጊዜ  ፀሐይ እንደሚያስቸግራቸው ነግረውን ለሁሉም ጃንጥላ ገዝተን አከፋፍለናል፡፡ ዕቃ መያዣ ቦርሳዎችም ጠይቀውን በፈለጉት ዲዛይን ቦርሳ ከአሜሪካ ተሠርቶ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ የክብደት መለኪያ፣ ቴርሞ ሜትር፣ የደም ግፊት መለኪያ መሣሪያም ለማቅረብ ግዥ በመፈጸም ላይ ነን፡፡ እንደዚህ ያሉ ቁሳቁሶቹን በበቂ የሚያቀርብ ድርጅት ባለመኖሩ እንቸገራለን፡፡ ቁሳቁሶቹን አገር ውስጥ የሚያቀርቡ ድርጅቶች የሚይዙት ውስን በመሆኑ የምንፈልገውን ያህል መጠን ለማግኘት እንቸገራለን፡፡ የሕክምና ቁሳቁሶችን ለማግኘት ያለው ውጣ ውረድ ደግሞ በጣም ከባድ ነው፡፡ የሕክምና ቁሳቁሶችን ከውጭ ለማስገባት ፈቃድ ሊኖረን ይገባል፡፡ ፈቃዱን ለማግኘት ያለው ሒደት ደግሞ እንደኛ ላለ ድርጅት ቀላል አይደለም፡፡ ስለዚህም ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች እንድንገዛ እንገደዳለን፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ጉዳዮች በአገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች አቅርቦት እኛ በምንፈልገው መጠን አይደለም፡፡ ስለዚህም ገበያው ላይ የተገኘውን እየገዛን በሒደት የተፈለገውን ያህል ለማቅረብ አስበናል፡፡ ቦርሳውንም በምንፈልገው መጠን ሠርቶ የሚያቀርብልን ድርጅት ባለመኖሩ ወደ ውጭ ገበያ ለመሄድ ተገደናል፡፡ እንደዚህ ያሉ ችግሮች በሥራችን ላይ እንቅፋት እየሆኑብን ይገኛሉ፡፡

ሪፖርተር፡‑ ፕሮግራሙ ቀጣይነት ይኖረዋል ወይስ በቅርቡ የሚዘጋበት ሁኔታ አለ?

አቶ ኅብረት፡‑ እኛ የምንሠራው ዩኤስኤአይዲ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በሚኖረው የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ተመሥርትን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የእኛን ሥራ ለሁለት ዓመታት ያህል አጠናክረን እንሠራለን፡፡ ከከተሞች መስፋፋትና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ለመቋቋም የጤናው ሴክተርም መጠናከር አለበት፡፡ በቀጣይ አመታት የከተማ ጤና ራሱን ችሎ እንደ አንድ አጀንዳ ሊሠራበት ይገባል፡፡   

  

              

Standard (Image)

​‹‹እስላማዊ ቅርሶች ቀርቅበው የያዟቸውን ባለማየታችን አያሌ የታሪክ መረጃዎች ተደብቀው እንዲቀሩ ፈርደንባቸዋል›› ዶ/ር ሐሰን ሰዒድ፣ የቅድመ ዘመን አርኪዮሎጂስት

$
0
0

ዶ/ር ሐሰን ሰዒድ የቅድመ ዘመን አርኪዮሎጂስት ናቸው፡፡ ላለፉት 15 ዓመታት በሙዚየም ኃላፊነት እያገለገሉ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአርኪዮሎጂና ቅርስ አስተዳደር ክፍለ ትምህርት የሙዚየም ሳይንስን ያስተምራሉ፡፡ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋምም የሙዚየም በኩሬተርት ያገለግላሉ፡፡ የኢትዮጵያ አርኪዮሎጂ ባለሙያዎች ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልም ናቸው፡፡ የከፋውን የቡና ሙዚየም በማቋቋም ይጠቀሳሉ፡፡ ብሔራዊ የቤተ መንግሥት ወደ ሙዚየም እንዲቀየር እየተደረገ ባለው ጥረት በግብረ ኃይሉ ውስጥ ሠርተዋል፡፡ በሙዚየምና ቅርስ ዙሪያ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ዶ/ር ሐሰን ቀደም ሲል የአርኪዮሎጂ እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት ያዘጋጁ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ ‹‹እስላማዊ ቅርሶች ዓይነትና ስርጭት ከሰሜን ሸዋ እስከ ደቡብ ወሎ›› በሚል ርዕስ ከአቶ ሐሰን ሙሐመድ ጋር አዘጋጅተው ለኅትመት አብቅተዋል፡፡ በመጽሐፉና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሔኖክ ያሬድ ዶ/ር ሐሰንን አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡‑ ቅርሶችን የተመለከተው መጽሐፍ የማዘጋጀት መነሻችሁ ምንድን ነው?

ዶ/ር ሐሰን፡‑ በኢትዮጵያ ሚሌኒየም ብሔራዊ ሴክሬታሪያት ውስጥ ቅርስን እንወክል በተባለበትና በምክትል ዳይሬክተርነት ተመድቤ በምሠራበት ጊዜ በአገራችን የቅርስ አፈላለግ፣ አስተዳደርና ልማት ላይ ፍንትው ብለው የሚታዩ ክፍተቶች ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያን ብዝኃነት ባማከለ ሁኔታ የሚሠራ ሳይሆን ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ነበር፡፡ አገር በቀል የእምነት ሥርዓትን አንሰበስብም፣ የቤተ እስራኤልን፣ የሙስሊሙን ቅርሶች አንሰበስብም ለልማት የምናደርገው ጥረት ደካማ ነበር፡፡ በቱሪዝም ረገድ የሰሜን መስመር ከሚባለው በስተቀር ወደ ምሥራቅ፣ ወደ ደቡብ አልሄደ፣ ይኼ ክፍተት ትንሽ ጠገነንና ምን አስተዋጽኦ እናድርግ ብለን ተነሳን፡፡ ለኢትዮጵያ ሚሌኒየም የምንቆየው አንድ ዓመት ተኩል ቢሆንም ክፍተቱንም ማሳየት አንድ ነገር ነው ብለን አንድ ፕሮጀክት ቀርጸን፣ ፕሮጀክቱን አማራጭ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማመላከት አልንና በሰሜን ሸዋና በደቡብ ወሎ ያሉትን ነገሮች መረጥን፡፡ አመራረጣችንም ለአዲስ አበባ ቅርበት ያላቸውና በውሎ ገባ መመለስ የሚቻልበት አጋጣሚ ስላላቸው ነው፡፡ ሁለተኛ የሰሜን ሸዋ ከደቡብ ወሎ አካባቢ በጥንት ጊዜ ወደ ቀይ ባሕር የሚሄደው የምሥራቅ የንግድ መስመር አንኮበር፣ አልዩ አምባ ጫፍ ይዞ ይገኛል፡፡ በብሔረሰቦች ደረጃም ኦሮሞ፣ አማራ፣ አርጎባ፣ አፋር በአንድነት በገበያ፣ በበዓል፣ በጋብቻ የሚገናኙበት ትልቅ ማዕከል ነው፡፡ ከሃይማኖት አኳያም የቤተ እስራኤል ትልቁ ክንፍ ያለው በሰሜን ሸዋ ነው፡፡ ክርስትናና እስልምና ያሉበት እንዲያውም ለ200 ዓመት የእስልምና ሱልጣኔት አስተዳደር ያለበት ነበር፡፡

እነዚህ አንኳር ነጥቦች ምክንያት ሆነው ደረጃውን የጠበቀ ሰነድ እንሥራ ብለን መነሳታችን ይህ መጽሐፍ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህ በኩል ያለውን ክፍተት ይሞላል፡፡ ጥናቱና ስነዳው ስምንት ዓመት ወስዷል፡፡ የኅትመት ገንዘብ አጥተን የቆየ ቢሆንም አሁን ግን የአርጎባ ልዩ ወረዳ አስተዳደር፣ አብዛኛው መጽሐፉ ውስጥ ያሉት ቅርሶች የሚያስተዋውቁት፣ አካባቢዬን ነው በማለት በአጋርነት (ስፖንሰርነት) እንዲታተም አድርጎታል፡፡

ሪፖርተር፡‑ የመጽሐፉ ይዘት ምንድን ነው?

ዶ/ር ሐሰን፡‑ በመጽሐፉ ውስጥ ለማሳየት የፈለግነው አንዱ የእስላማዊ ቅርስ ምንነት ነው፡፡ አንዳንዱ እስላማዊ ቅርስ ምን ማለት ነው? ብሎ ይጠይቃል፤ ለምንስ የእስላም የክርስቲያን ይባላል፡፡ ቅርስ ቅርስ ነው እንጂ ይላል፡፡ የበለጠ ቀርበን እንድናጠናው፣ እንድናውቀውና እንድንጠብቀው ለይተን እናጠናለን፡፡ ለምሳሌ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ባይብል ከለር አርኪዮሎጂ የሚባል አለ፡፡ ዓላማው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተተረኩት ታሪኮች እውን ነበሩ? ተብሎ የሚጠናበት ነው፡፡ ኢያሪኮን በከተማነት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ተቸነከረበት የተባለውን ምስማር፣ እንጨት ማግኘት፣ ወዘተ የሚመረምር መጽሐፍ ቅዱሳዊ አርኪዮሎጂ ተፈጥሯል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም እስላማዊ አርኪዮሎጂ ተፈጥሯል፡፡ ይህን ወደ አገራችን ስናመጣ እስላማዊ አርኪዮሎጂ፣ ቅርስ ለማለት ሰው የሚፈራው አገራዊ አይደለም ወይ በማለት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተግባር ላይ ያሉ 44 ሙዚየሞች አሉ፡፡ ይዘታቸውም ከቤተክርስቲያን ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የአገር ቅርስም ናቸው፡፡ እንዲሁም በእስላማዊ ቅርስ ረገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሰባተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በነበረው ሒደት ምን ቅርስ አፍርቷል? ከሥነ ሕንፃ፣ ከሥነ ጽሑፍ፣ ከአዋቂዎች (ኡላማዎች) አንፃር እነማን ተነስተዋል የሚለውን ጉዳይ ለማሳየት መጽሐፉ ይሞክራል፡፡ መጽሐፉ በውስን መልክአ ምድር ሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ ላይ ያተኩራል፡፡ የእስላማዊ ቅርሶች ብያኔን ከማስፈር ባለፈ፣ በየዘርፉ መድበናል፡፡ እስላማዊ መንደሮች የሚመሠረቱበትን መልክ ከሌሎች ጋር በማነፃፀር ሠርተናል፡፡

እስልምና ከእምነት ባለፈ የሕይወት የአኗኗር ስልት ዘይቤ ነው፡፡ ሃይማኖቱ በሚፈቅደው መልክ መኖር ማለት ነው፡፡ በአርኪዮሎጂ የቤቶችን ክብነት ወይም ሌላው ዓይነት እናገኛለን፡፡ በመንደር፣ በመስጊድ፣ በእስላማዊ ሥነ ጽሑፍ በአጀቢ ጽሕፈት (ቋንቋው አማርኛና ሌላ የአገር ቋንቋ ሆኖ ፊደሉ ዐረቢኛ ሆኖ ሥነ ፈለክ፣ ቁጥር፣ ሕክምና፣ ወዘተ ይዘት ያላቸው የያዘ)፣ የዑላማዎች አስተዋጽኦ (በእግራቸው በሱዳን በኩል ግብፅና የመን ሄደው ተምረው የተመለሱ፣ በቃልና በኪታብ ሲያስተምሩ የኖሩት) ይህ ሁሉ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡

መሠረታዊ የሚባሉትን የእስላማዊ ቅርሶችን በየዘርፉ የተሰነደበት መጽሐፍ ነው፡፡ እስላማዊ ሥነ ጽሑፎች፣ ግጥሞች፣ መንዙማዎችና ውዳሴዎች ባለመፈለጋቸው፣ ባለመሰብሰባቸውና ባለመጠናታቸው ስንኳን ስለሀገር ሥነ ጥበብ ያበረከቱትን ለመለየት ቀርቶ ለዛና ጣዕማቸውን ለማጣጣም አልታደልንም፡፡ ከዚህ ሌላ እስላማዊ ቅርሶች በውስጣቸው ቀርቅበው የያዟቸውን ቁም ነገሮች ባለማየታችን አያሌ የታሪክ መረጃዎች ተደብቀው እንዲቀሩ ፈርደንባቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡‑ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ሦስተኛውን የማይዳሰስ ቅርሷን የገዳ ሥርዓት አስመዝግባለች፡፡ ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች አኳያ ለማስመዝገብ ብዙ ሥራ እንዳልተሠራ ይነገራል፡፡

ዶ/ር ሐሰን፡‑ በአገሪቱ በቤተእስራኤልም፣ በክርስትናም፣ በእስልምናም ብዙ መንፈሳዊ ቅርሶች አሉ፡፡ የመውሊድ በዓል ገታ ላይ የሚከበረው ዠማ ንጉሥ ሳምንት ድረስ የሚዘልቀው ልዩ ነው፡፡ በመርካቶ 24 ሰዓት ሳምቡሳ እየተበላ ጫትም ኖሮ የበዓሉ መገለጫ መንዙማው ልዩ ድባብ አለው፡፡ በዓለም ቅርስነት ማስመዝገቡ ቆይቶ በአገር ደረጃ ለምን እንዲሰነድ አይደረግም? ሁሉንም የሚወክል የቅርስ አሰባሰብ ያስፈልጋል፡፡ ሙዚየሙ የተቋቋመለትን ዓላማ ግቡን ይመታ ዘንድ በቅርስ አሰባሰብ ላይ ፖሊሲ ሊኖር ይገባል፡፡ ውክልናውን ማስጠበቀ ይገባል፡፡ የሁሉንም ማቀፍ አለበት፡፡

ሪፖርተር፡‑ ቅርስ ባለሥልጣን የቅርስ ማስመዝገብ ጥያቄ ሲቀርብለት ነው የሚንቀሳቀሰው ይባላል?

ዶ/ር ሐሰን፡‑ አሠራሩ ጥያቄ ሲቀርብለት ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ብሔራዊ ተቋሙ በወካይነት ሊቀመጡ የሚችሉ ቅርሶችን አስቦና ተጨንቆ የመመዝገብ የማስተባበር ሥራ መሥራት አለበት፡፡ ለሙስሊሙ ዓለም ልናበረክት የምንችለው ነጋሽ ላይ ቅርስ አለ፡፡ ድሬ ሼህ ሁሴን ለዩኔስኮ የዕጩነት (ኖሚኔሽን) ፋይል ቀርቦ እንዴት ስምንት ዓመት ይፈጃል፡፡ ዛሬ ስለርሱ የሚያነሳ የለም፡፡ ወረዳም ሆነ ዞን ተነስቶ ቅርስ አስመዘግባለሁ ይላል፡፡ ማነው የሚያደርገው? አገር ነው የሚጠይቀው አገር ሲጠይቅ ግን ተዘጋጅቶ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ሊያስተዋውቁ ብዝኃነቷን ሊያሳዩ የሚችሉ ቅርሶች ማስመዝገብ ያለበት ይኼ ተቋም ነው፡፡

በሌላ በኩል በዩኔስኮ ቅርስን ማስመዝገብ ተጨማሪ ኃላፊነትን መውሰድ ማለት ነው፡፡ አክሱምን ተመልከት ባለው አያያዝ በአደጋ ላይ ያለ ቅርስ ወደሚባለው መዝገብ ውስጥ ሊገባ ነው፡፡ ተቋማዊ ብቃትን ሳናጠናክር ሕጋዊ መስመርን ሳናሲዝ ማስመዝገብ ጥያቄ ውስጥ ያስገባል፡፡

ሪፖርተር፡‑ ከእስላማዊ ቅርሶች ጋር የተያያዘ ዕውቀት ያለው ባለሙያ አለ?

ዶ/ር ሐሰን፡‑ በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትም (ወመዘክር) ሆነ በቅርስ ተቋም እንደሌለ ነው የማውቀው፡፡ በዓረቢኛ የተጻፉት የክርስትና ይሁን የእስልምና ጽሑፎች መሆናቸውን የሚለይ የለም፡፡ ስለዚህ ይህ ብሔራዊ ተቋም እስላማዊ ቅርሶችን መሰብሰብ ግዴታዬ ነው እንዲህ ዓይነት ባለሙያ ላፍራ ማለት የለበትም?!

ሪፖርተር፡‑ የአገሪቱን ምልዐተ ቅርሶች በስፋት እንዲታወቁ እንዲጠበቁ ለማድረግ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሥር የተቋቋመው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ኃላፊነት እምን ድረስ ነው?

ዶ/ር ሐሰን፡‑ ተቋሙ ባደረጃጀት ችግሮች ያሉበት ነው፡፡ የመጀመሪያው የቅርስ ተቋም በ1936 ዓ.ም. የተቋቋመው ብሔራዊ ሙዚየም ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ብሔራዊ ሙዚየሙን አፈረሰው፡፡ ከዚህ ቀደም ከአሠርታት በፊት ሙዚየም እንዲያድግ አይፈለግም ነበር፡፡ ለምን ሌሎች ዲፓርትመንቶች ሙዚየሙ ገኖ ከወጣ ዝቅ ይላሉ፡፡ ያ ገጽታ (ስታተስ) እንዳይኖር ሙዚየሙ ከነርሱ ጋር እኩል እንዲራመድ ገድበውት ቆዩ፡፡ ይባሱኑም ገደሉት፡፡ በአሁን ጊዜ በሕግ አቋም ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም›› ተብሎ የሚጠራ ተቋም የለም፡፡

እንዲያውም የቅርስ ባለሥልጣኑ የፌዴራል ፖለቲካዊ አደረጃጀቱንኳ ከግምት ያላስገባ ነው፡፡ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ቅርንጫፎች በየክልሉ አሉ እንዴ? ሁለተኛ ባለሥልጣኑ አሁን የሚመራበት አዋጅ መታየት ያለበት ነው፡፡ ይህም የምልበት አንዱ ማሳያ በአዋጁ ቅርስ ጥናትና ጥበቃን የሚመራ የመማክርት ምክር ቤት ይመሠረታል እንጂ ቅርንጫፍ አቋቁሞ ሥራውን ይመራል የሚል የለውም፡፡ ከክልል ጋር የሚሠራው በመግባባት እንጂ የሕግ አስገዳጅ ነገር የለውም፡፡ ስለዚህ ከአደረጃጀትም ከሥልጣንም አንፃር ትልቅ ችግር አለበት፤ ከባጀትም አንፃር ውስን ነው፡፡ አገሪቱ በአሁን ጊዜ ሰፊ መሠረተ ልማት እያከናወነች ግዙፍ ተቋማት በየአካባቢው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ እነዚህም በቅርሶች ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ ይኖራል፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከክልሎች 27 ጥያቄዎች መጥተውለታል፡፡ አብዛኛው ከቤተክርስቲያን ‹‹ጠግንልን›› ብለው ላኩ፡፡ በጀቱና ፍላጎቱ ቢኖረውም ያሉት ባለሙያዎች ሰባት ናቸው፡፡ መሥሪያ ቤቱ መሥራት ያለበት ሬጉላቶሪ የሱፐርቪዥን ሥራ እንጂ ኦፕሬሽን ላይ አይችልም፡፡ ይህ ዝበት ስላለ ነው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ሥራችን የቆመው፡፡

ሁለተኛ ነገር በሌላው አገር ምርምር የሚሠራው መጀመሪያ በራሷ የሰው ኃይል ነው፡፡ ያለውን ዕምቅ ሀብት ማወቅ ይገባል፡፡ ይህ ባለመታወቁ የምርምር አካሄዳችን ተጣርሷል፡፡ ከውጭ ተመራማሪዎች ጋር ተቧድኖ የሚሠራው ምርምር በተወሰነ አካባቢ ሆኗል፡፡ ምርምሩን የሚተልሙት የውጭ አጥኚዎች እንጂ በእኛ ተቋማት አይደለም፡፡

ተቋማዊ ተክለ ሰውነቱ ራሱ ልዩ ነው፡፡ ላቦራቶሪ ለመሆን ቴክኒሻኖች ማፍራት፣ ቴክኖሎጂ ማስገባት አለብህ፡፡ ቢያንስ ቻርኮል እዚህ ዘመኑ መለየት (ዴት) መቻል አለበት፡፡ የብራና መጻሕፍት፣ አይቮሪ፣ ቴክስታይል፣ ወዘተ መጠገን መቻል አለብህ፡፡ አሁን ጽሕፈት ቤትና ግምጃ ቤት (ስቶር) ነው የሆነው፡፡ ስለዚህ አካሄዳችንም አሠራራችንም ትንሽ የጎደለው ነገር አለ፡፡

ሪፖርተር፡‑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካሄድስ?

ዶ/ር ሐሰን፡‑ በኒዮሌቲክ፣ በብረት ዘመን፣ በቅድመ ታሪክ አርኪዮሎጂ ሰው የለንም፡፡ ዩኒቨርሲቲዎቻችን የሚሰጡን ሥርዓተ ትምህርት አንድ ዓይነት ነው፡፡ ዶ/ር ካሳዬ የዛሬ አሥር ዓመት የቀረፀውን ሥርዓተ ትምህርት ፎቶ ኮፒ እያደረግን እንደጨረር በአዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ ያቺኑ ነው የምናስተምረው፡፡ የወጡት ልጆች ግን ሁሉን ነገር ያሟላሉ? ራሳቸውን ችለው የመስክ ምርምር ማድረግ የሚችሉ ናቸው? ስፔሻላይዜሽን እንኳ የለንም፡፡ ሐዋሳ ቅድመ ታሪክ አርኪዮሎጂን ከሚያስብ ኢትኖ አርኪዮሎጂን ለምን አያስተምርም፡፡ የብሔር ብሔረሰቦች አካባቢ ነውና ከ50 በላይ ብሔረሰቦች ይሠራል፡፡ በአፋርስ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለምን ተመሳሳይ ትምህርት ያስተምራል፡፡ ፊዚካል አርኪዮሎጂ እያለለት፡፡ አክሱምስ እንደማንኛውም ቅርስ ማስተማር አለበት? አኩሱሞሎጂ ነው ነጥሮ መውጣት  ያለበት፡፡ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ሌላ ቀርቶ ስፔሻላይዜሽን እንኳን አይሞክሩም፡፡ እስቲ ቆም ብለን እንመልከት፡፡ በአሥር ዓመት ውስጥ እያፈራን ያለነው የአገሪቱ ፍላጎት ላይ ተመሥርተን ነው?

ከዐሥር ዓመት በፊት የቀረፅነው ሥርዓተ ትምህርት ዛሬም ሊያገለግለን ይገባል? ለምን አናሻሽለውም፡፡ ለዚህ ነገር ተነሳሽነቱን መውሰድ ያለበት ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነው፡፡ የሰው ኃይል የሚፈልገው ከዩኒቨርሲቲ በመሆኑ የሚፈልገውን እያገኘ ነው ወይ? ይህን ዞር ብሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡ መወቀስ ካለም ባለሥልጣኑ ብቻ ሳይሆን የአርኪዮሎጂና ሙዚየም ባለሙያዎች ማኅበራትም ጭምር ናቸው፡፡

ማኅበራት ያለውን ክፍተት ለመሙላት ምን ያህል ተንቀሳቅሰዋል? ለመንግሥትም ሆነ ለተቋም ምን ያሳየነው ነገር አለ? አቅጣጫ ለማሳየት በቁርጠኝነት ምን ያህል ሄደናል?

ሪፖርተር፡‑ ምን መደረግ አለበት?

ዶ/ር ሐሰን፡‑ ከአርኪዮሎጂ አንፃር ሥርዓተ ትምህርታችንን መፈተሽ አለብን፡፡ የትኛው ዩኒቨርሲቲ አንፃራዊ ጠቀሜታ አለውና በየትኛው ነገር ስፔሻላይዝ ያድርግ ማለት አለብን፡፡ ሁለተኛ አዳዲስ የሚወጡ ተመራቂዎች መተማመን ኖሯቸው ወደየምርምር ቦታዎች ራሳቸውን ችለው እንዲሄዱ ማድረግ፣ 19 ኢንተርናሽናል የምርምር አካሎች እዚህ ሲንቀሳቀሱ ከእኛ ፈቃድ አግኝተው ነው፡፡ በፈቃዱ ፎርማት ላይ በአጭር በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የአቅም ግንባታ ለተቋሙ ለማድረግ ፈቅደን ፈርመናል ይላል፡፡ ምን ያህል ተጠቅመንበታል፡፡

ወጣቱን ልከን አቅማቸውን የሚያሳድጉበት መንገድ ለምን አንፈጥርም፡፡ የሚመጡ ሰዎች የየዘርፉ ኃላፊዎች በበጀት፣ በሥርዓተ ትምህርት የሚያዙ ናቸው፡፡ አላደረግንም፡፡ ለምንድን ነው ያላደረግነው፡፡ ተቋማዊ ርዕይ ኖሮት የሚመጣ የለም፡፡ ስለዚህ እኛ የፈረንጆች አገልጋይ ሆነን ነው እንጂ የምንመለሰው፣ ራሳችንን ችለን በራስ መተማመን ቦታ እንዲኖረን አያደርግም፡፡ ርግጥ ራሳቸውን ችለው የሚሠሩ አሉ፡፡ ጥቂት እነ ዶ/ር ዘርዐ ሠናይ፣ ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለሥላሴ ዶ/ር ዮናስና ስለሺ አሉ፡፡ ስለዚህ የእኛ ተቋም ርዕይ ሊኖረው ይገባል፡፡ እንግዲህ ሱፐርቪዥን፣ ቁጥጥር፣ አመራር ላይ የሰው ኃይል ሥልጠና ስትራቴጂ ላይ ራሴን ላድርግ ማለት አለበት፡፡ ­

                

Standard (Image)

እንደ ጨው ሀብቷ መሠረተ ልማት ያልሞላላት አፍዴራ

$
0
0

አፍዴራ በነበራት የጨው ክምችት የታወቀችው በኢትዮጵያናበኤርትራመካከልየተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ነው ፡፡ ከቀይባህርይገባየነበረውየምግብጨውአቅርቦትበግጭቱምክንያትመቋረጡአገሪቱበአፍዴራ ያላትንየጨውክምችትመለስብላእንድታይያደረገና ጨው ለመግዛት ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ በእጅጉ ያስቀረ ነበር፡፡በአፍዴራሐይቅ 292 ሚሊዮንቶን የጨውክምችትአለው፡፡ በ1992ዓ.ም. እንደተቆረቆረች የሚነገርላት አፍዴራ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌዎች አሏት፡፡ አቶ ሙሳ መሐመድ የአፍዴራ ወረዳ አስተዳዳሪ ሲሆኑ፣ ሻሂዳ ሁሴንበወረዳዋ የመሠረተ ልማት እንቅስቃሴ ዙሪያ አነጋግራቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡- በወረዳዋ ምን ያህል ሰዎች ይኖራሉ?

አቶ ሙሳ፡- የሕዝብና የቤት ቆጠራ የተደረገው ባለፈው 2004 ዓ.ም. ነው፡፡ በወቅቱ በነበሩት አንዳንድ ሁኔታዎችና የመንገድ ችግር ነዋሪዎቹ ሙሉ በሙሉ አልተቆጠሩም፡፡ በዚህ መልኩ የተቆጠሩ ነዋሪዎች 32,000 ብቻ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- በወረዳዋ ያለው የልማት ሁኔታ ምን ይመስላል?

አቶ ሙሳ፡- የልማት ሥራ የተጀመረው ከሁለት ዓመታት ወዲህ ነው፡፡ በአካባቢው የመጠጥ ውኃ ለማግኘት እንኳን ከፍተኛ ችግር ነበር፡፡ ነዋሪዎቹ የመጠጥ ውኃ የሚያገኙት ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ከሎጊያ ነበር፡፡ አሁን ይኼንን ለማስቀረት ተችሏል፡፡ ነዋሪዎች ቢያንስ ውኃ ፍለጋ ሎጊያ ድረስ እንዳይጓዙ ለማድረግ ተችሏል፡፡ 4,200,000 በሆነ ወጪ የውኃ ማጣሪያ ማሽን ገዝተን ነዋሪው የመጠጥ ውኃ የሚያገኝበትን ሁኔታ አመቻችተናል፡፡ በሌሎችም አራት ቀበሌዎች ላይ የውኃ ቁፋሮ ተደርጓል፡፡ በሌላ አንድ ቀበሌ ላይ ለመቆፈርም በዝግጀት ላይ ነን፡፡ ሁሉም ተጠናቅቀው በዚህ ዓመት አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብለን እንገምታለን፡፡

      ተበታትነው የሚኖሩ ሰዎችን መምራት አስቸጋሪ በመሆኑ በዚህ ዓመት መንደር ማሰባሰብ ጀምረናል፡፡ ሦስት ቀበሌዎችን ለማሰባሰብም አቅደናል፡፡ በመጪው ዓመትም እንደዚሁ ሦስት ቀበሌ እያልን ሕዝቡን ለማሰባሰብ እየሠራን እንገኛለን፡፡ መንደር የማሰባሰብ ሥራ በተከናወነባቸው ሥፍራዎች ላይ እርሻ እየተሞከረም ይገኛል፡፡ በወረዳው ያለውን የጤና ሽፋን ለማስፋፋትም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ በአምስት ቀበሌዎች ላይ የጤና ሽፋን ለማድረስ ተችሏል፡፡ ሁለት ጤና ጣቢያዎች ሲኖሩ የተቀሩት ጤና ኬላዎች ናቸው፡፡ በሌሎቹ ቀበሌዎች ላይ የጤና አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ሞባይል የጤና አገልግሎት በመስጠትና አምቡላንሶች በመጠቀም እየተሠራ ይገኛል፡፡

ሪፖርተር፡- የወረዳዋ ኢኮኖሚ በምን ላይ የተመሠረተ ነው?

አቶ ሙሳ፡- የወረዳዋ ኢኮኖሚ የተመሠረተው በጨው ላይ ነው፡፡ ነዋሪዎቹ ከብት አርቢዎችና ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ በአንድ አካባቢ ተረጋግቶ መኖርን ለማስለመድ በተደረገው ጥረትም በወረዳው የሚገኙ አምስት ቀበሌዎች በአንድ ቦታ ላይ ተረጋግተው እንዲኖሩ አስችሏል፡፡ የተቀሩትን አራት ቀበሌዎችም በመንደር በማሰባሰብ አንድ ቦታ ላይ እንዲኖሩ ለማድረግ እየሠራን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከጨው ምርት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ችግሮች እንዳሉም ይነገራል፤ በዚህ ረገድ ምን ይላሉ?

አቶ ሙሳ፡- በፊት የጋራ ድጋፍ ማኅበር ነበር፡፡ ጨውን አዮዳይዝድ ማድረግ ከተጀመረ በኋላ አሠራሮች ተሻሽለዋል፡፡ ያለ ፋብሪካ ትዕዛዝ ጨው መውጣት እንደማይችልም መንግሥት ወስኗል፡፡ አዮዳይዝድ ያልተደረገ ጨው ወደ ገበያ ያስገባ ሰው ከፍተኛ ቅጣት ስለሚቀጣ ማንም አዮዳይዝድ ያልሆነ ጨው ወደ ገበያ ማስገባት አይችልም፡፡ ከዚህ ቀደም ጨው ላይ ምን ያህል መጠን ያለው አዮዲን መቀላቀል አለበት የሚለውም አይታወቅም ነበር፡፡ አሁን ግን ተስተካክሏል፡፡ በወረዳዋ ከፍተኛ የጨው ክምችት አለ፡፡ አምና ብቻ ወደ ስምንት ሚሊዮን ኩንታል ጨው ምርት ነበር፡፡ ወደ ገበያ ገብቶ በጥቅም ላይ የሚውለው ግን ከሦስትና አራት በመቶ ያነሰ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ወደ ገበያው የተትረፈረፈ ምርት ገብቶ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ችግር እንዳይፈጥር ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በአፍዴራምን ያህል ጨው አምራቾች አሉ?

አቶ ሙሳ፡- 415 ባለሀብቶች ጨው ያመርታሉ፡፡ በተጨማሪም በ20,000 ካሬ ቦታ ላይ  የአካባቢው ተወላጆች ሃያ ሃያ እየሆኑ ይሠራሉ፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ገቢ ዝቅተኛ ነበር፡፡  ለሠራተኛ የሚከፈለውና ነዳጅና ጨው የሚመላለስበት ጋሪ ለመግዛት የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ ስለነበር ከወጪ ገቢ የሚቀረው አነስተኛ ነበር፡፡ በተለይም ለጋሪ የሚወጣው ወጪ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ አንድ አዲስ ጋሪ ከአንድ ጊዜ በላይ ጥቅም አይሰጥም፡፡ ወዲያው ይበላል፡፡ ስለዚህም ጋሪ በየጊዜው ለመግዛት እንገደዳለን፡፡ ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ዓይነት ነበር፡፡ ከጨው ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ለተለያዩ ዕቃዎች መግዣና ለሠራተኛ ክፍያ ይውል ነበር፡፡ ሰውም ለፍቶ የሚያገኘውን ገንዘብ የመቆጠብ ባህል አልነበረውም፡፡ አሁን ግን በወረዳው የባንክ አገልግሎት አለ፡፡ ነዋሪዎቹም መቆጠብ ጀምረዋል፡፡ የጨው ዋጋም ከፍ ብሏል፡፡

ሪፖርተር፡- በወረዳዋ ተዘዋውረን ለማየት ሞክረን ነበር፡፡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አለመኖሩን ታዝበናል፡፡ ነዋሪዎችና በአካባቢው ያሉ የተለያዩ የጨው ፋብሪካዎችም መቸገራቸውን ገልጸውልናል፡፡ በአፍዴራ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች አሉ?

አቶ ሙሳ፡- በዓለም ባንክ ትብብር የኤሌክትሪክ አገልግሎት በአፍዴራ ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ የስቴሽን ቦታም ተመርቷል፡፡ በዚህ ዓመት ለዘጠኙም ቀበሌዎች መድረስ ባይቻልም ቢያንስ ለተወሰኑት እንደሚደርስ እንገምታለን፡፡

ሪፖርተር፡- በአፍዴራ አብዛኛዎቹ መኖሪያ ቤቶች ጊዜያዊና ከሳጠራ፣ ከቆርቆሮና ከላስቲክ የተሠሩ ናቸው፡፡ ይኼ ከምን አንፃር የሆነ ነው? ቋሚ ቤቶችን የመገንባት ሐሳብስ አለ?

አቶ ሙሳ፡- ቤቶቹ የተሠሩት በቀላሉ በእሳት ሊቀጣጠሉ ከሚችሉ ከሳጠራና ፕላስቲክ በመሆኑ ከዚህ ቀደም ሦስት ጊዜ የእሳት አደጋ ተከስቶ የብዙዎች ገንዘብና ንብረት ተቃጥሏል፡፡ ይኼንን ተመልክተን ንግድ ባንክና አንበሳ ባንክ እዚህ አገልግሎት እንዲሰጡ፣ የነዋሪዎችም ገንዘብ በባንክ እንዲቀመጥ አድርገናል፡፡ የከተማው ደረጃና ገጽታ ለማስተካከል ፕላን አውጥተናል፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በፕላኑ መሠረት ቤቶችና ድርጅቶች እየተገነቡ ነው፡፡ ጊዜያዊ ቤቶች እንዳይገነቡም ከልክለናል፡፡ በፕላኑ መሠረት መሥራት የሚችል ሰው ካለ ይሥራ ብለን እየጠበቅን ነው፡፡ አንድ የውጭ ባለሀብትም ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ይህ እንደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የቤት ተመዝጋቢዎች ገንዘብ እየቆጠቡ የሚያገኙት ዕድል ነው፡፡ ጅምሮቹ አፍዴራ አሁን ያላትን ገጽታ እንደሚያሻሽለው እምነት አለን፡፡

ሪፖርተር፡- በአፍዴራ ከፍተኛ የመንገድ ችግር አለ፡፡ ይኼንን ለማስተካከል ምን ታስቧል?

አቶ ሙሳ፡- የመንገድ ግንባታ ጉዳይ የፌዴራል ሥራ ነው፡፡ በቅርቡ 20 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ግንባታ ለማሠራት ጨረታ ወጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ጨረታው ባልታወቀ ምክንያት ተሰርዟል፡፡ ወደ ኤርተአሌ የሚወስደውን መንገድም ለማስገንባት ዕቅድ ተይዟል፡፡ ይሁን እንጂ መቼ ይጀመራል የሚለው ገና አልታወቀም፡፡

ሪፖርተር፡- አካባቢው የተፈጥሯዊ መስህብ መገኛ እንደመሆኑ ከጨው ጎን ለጎን  ቱሪዝም ዋነኛ የገቢ ምንጩ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁንና የጎብኚዎችን  ፍሰት  የሚያበረታቱ ደረጃቸውን የጠበቁ እንደ ሆቴል፣ ምግብና መንገድ ያሉ አገልግሎቶች የተሟሉ አይደሉም፡፡ ይህ ለምን ሆነ?

አቶ ሙሳ፡- ለጎብኚዎች የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች ጭራሽ የሉንም፡፡ ብዙ ጎብኚዎች ይገባሉ፡፡ ነገር ግን ማረፊያ ቦታ ባለመኖሩ ይቸገራሉ፡፡ ለዚህም በዚህ ዓመት ከክልል ቱሪዝም ቢሮ ጋር ተነጋግረን ሆቴል ለመሥራት አስበናል፡፡ ከዚህም ውጪ ያሉ ችግሮችን ከመንግሥት ጋር በመነጋገር መፍትሔ እንሰጣለን፡፡

ሪፖርተር፡- በአፍዴራ የሚመረተው ጨው የአገሪቱን የጨው ፍላጎት የያዘ ሲሆን፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይም ቦታ አለው፡፡ ይሁንና የዚህ ሀብት መገኛ የሆነችው አፍዴራ ገና ድክድክ ማለት እንኳን አልጀመረችም፡፡ ይኼ ከምን አንፃር የሆነ ነው?

አቶ ሙሳ፡- አፋር ክልል በጠቅላላው የልማት ተጠቃሚ አልሆነም ነበር፡፡ በዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ ግን ጥሩ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነው፡፡ እስከአሁን ለነበረው ችግር ምክንያት የአመራር ድክመት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ መንግሥት ዓመትዊ በጀት ይመደባል፡፡ ነገር ግን የተመደበው በጀት ለተባለለት ዓላማ ሲውል ብዙም አይታይም፡፡

ሪፖርተር፡- ከጎሳ መሪዎች ጋር ያላችሁ መስተጋብር ምን ይመስላል? 

አቶ ሙሳ፡- የጎሳ መሪዎች ከመንግሥት ጋር የሚያወዳድራቸው ጉዳይ የለም፡፡ አንዳንድ ጉዳዮች ወደ መንግሥት ሳይደርስ እዚያው ይጨርሳሉ፡፡ መንግሥት የሚመለከተው ጉዳይ ሲሆን ግን ያለነሱ ጣልቃ ገብነት ይሠራል፡፡ የመንግሥት የመንግሥት ነው የኅብረተሰብ ደግሞ የኅብረተሰብ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የወረዳዋን መሠረተ ልማት ከማሟላት አንፃር የታሰቡ ሥራዎች ካሉ ቢነግሩን?

አቶ ሙሳ፡- ሁለት ነገሮችን አስበናል፡፡ በአራት ቀበሌ የሚገኙ ልጆች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ለመክፈት አሊያም ሆስፒታል ለመገንባት አስበናል፡፡ ለዚህ የሚሆን ገንዘብ አስቀምጠናል፡፡ ነገር ግን ያለን አቅም ውስን በመሆኑ ከሁለት አንዱን ማሠራት ብቻ ነው የምንችለው፡፡ የትኛው ቅድሚያ ይሰጠው የሚለውን ነገር ገና ውሳኔ ስላልተሰጠበት በመጠባበቅ ላይ ነን፡፡

 

 

Standard (Image)

‹‹የአካል ጉዳተኛው ጉዳይ ልናስታምመው የሚገባ ፖለቲካ ነው››

$
0
0

አቶ ዮሴፍ ኃይለማርያም፣ የመረጃና ግንዛቤ ስለአካል ጉዳተኞች ማኅበር መሥራችና ፕሬዚዳንት

መረጃና ግንዛቤ ስለአካል ጉዳተኞች ማኅበር፣ የአካል ጉዳተኛውን ችግር ግንዛቤ በመፍጠር ለመቅረፍ የተቋቋመው ከ11 ዓመታት በፊት ነው፡፡ በአምስት አባላት የተመሠረተው ማኅበር ዛሬ ላይ 82 አባላትን አፍርቷል፡፡ የማኅበሩ መሥራችና ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ ዮሴፍ ኃይለ ማርያም ናቸው፡፡ ጋዜጠኛ ዮሴፍ፣ ‹‹ዮሴፍ ምርኩዝ›› በሚል መጠርያ መጣጥፎች በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በቀድሞው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣና ለገዳዲ  ሬዲዮ ላይ ሠርተዋል፡፡ አሁን ላይ በአዲስ አበባ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ይሠራሉ፡፡ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን፣ በሚዲያ ሕግ ማስተርስ ዲግሪያቸውን በኖርዌይና በስዊድን አግኝተዋል፡፡ ቲዎሎጂም ተምረዋል፡፡ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር በመሠረቱት ማኅበር ዙሪያ ምሕረት ሞገስ አነጋግራቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡- ‹‹አካል ጉዳተኞች ከአገሪቱ ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በቀዳሚነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሠራት አለበት›› በሚል በግንዛቤ ዙሪያ የሚሠራ ማኅበር አቋቁማችኋል፡፡ የአካል ጉዳተኛውን ችግር ያባባሰው ምንድነው ይላሉ?

አቶ ዮሴፍ፡- እንደ መረጃና ግንዛቤ ስለ አካል ጉዳተኞች ማኅበር፣ አካል ጉዳተኛውን ከኅብረተሰቡ፣ ከመንግሥትና ከራሱ ጋር እንዲጣላ ያደረገው የመረጃና የግንዛቤ እጥረት ነው፡፡ አንድ ተቋም ወይም ግለሰብ በአካል ጉዳተኛ ዙሪያ መረጃ ከሌለው አብሮ መሥራት አይችልም፡፡ ይህንን መሠረት አድርገን ከ11 ዓመታት በፊት ፕሮጀክት ቀረፅን፡፡ ማኅበሩ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ግንዛቤ ይሰጣል፣ መብት ላይም ይሠራል፡፡ የሕግ ክፍተቶችን ያሳያል፣ ሕጎች ያስተዋውቃል፡፡ የሕክምና፣ የትምህርትና ሌሎችም ዘርፎች ለአካል ጉዳተኞች ያላቸውን ተደራሽነት ችግሮች ነቅሶ በማውጣትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር፣ የአካል ጉዳተኞችን ችግር ግንዛቤ በመፍጠር ለመፍታት ይሠራል፡፡ መጀመሪያ ላይ መጽሔት እናዘጋጅ፣ በራሪ ወረቀትም እንበትን ነበር፡፡ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ ሕግ ጋር ተያይዞ ግን ዕርዳታ ሰጪዎች ወደኋላ ስለተጎተቱብን በሕግ፣ በጋዜጠኝነት በሌሎችም ዘርፎች የተማርነው የማኅበሩ አባላት በበጎ ፈቃደኝነት ‹‹ትኩረት›› የሚል የሬዲዮ ፕሮግራም የመጀመሪያው ኤፍኤም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ሲጀመር ጀምሮ እያስተላለፍን ነው፡፡ በትንሽ ዕርዳታም መሥራት ከባድ ስለሆነ፣ በመንግሥት ሚዲያ ውስጥ ገብተን በአዲስ ቲቪ፣ በኤፍኤም 96.3፣ በአካል ጉዳት ላይ ግንዛቤው እንዲኖር እንሠራለን፡፡ አካል ጉዳተኛውም የሬዲዮ ጣቢያዎች ላይ እየገባ መሥራት ጀምሯል፡፡ ዓባይ፣ ሸገር፣ ዛሚ፣ ብሥራት ላይ የአካል ጉዳተኛውን ችግር ለማስገንዘብና ችግሮችን ለመቅረፍ እየተጋገዝን እንሠራለን፡፡ የጋራ ገቢ ግን የለንም፡፡

ሪፖርተር፡- የተማሩና ገንቢ ሐሳብ ሊያመነጩ የሚችሉ ብዙ አካል ጉዳተኞች ቢኖሩም በየማኅበራቱ ተሳትፈው ለመብታቸው ሲሟገቱ አይስተዋሉም፡፡ ለምን ይመስልዎታል?

አቶ ዮሴፍ፡- የኛ ማኅበር አባላት በገንዘብ ሊተመን የማይችል ዕውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ ኖርዌይ ለትምህርት በቆየሁባቸው ዓመታት የተማርኩት ስለአካል ጉዳተኛ አካል ጉዳተኛ ያልሆነውም ጭምር የሚሟገት መሆኑን ነው፡፡ የአካል ጉዳተኛ ጉዳይ ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አለበት፡፡ ሆኖም በጣም እግሬን ሲያመኝ የሚሰማኝ እኔ ነኝ፡፡ አካል ጉዳተኛው፣ በአካል ጉዳተኛው ጉዳይ አብሮ ቢሠራ ለውጤቱ መልካም ነው፡፡ በተለይ የተማረው አካል ጉዳተኛ ስለአካል ጉዳተኛ አብሮ ካልሠራ አደጋ አለው፡፡ በመከራ ሊሆን ይችላል የተማረው፡፡ ደህና ቤተሰብ የነበረው ደግሞ በር ሳይዘጋበትና ከትምህርት ሳይታገድ ተምሯል፡፡ አሁንም ግን ብዙዎች ከቤት አልወጡም፡፡ አካል ጉዳተኞችን ለመርዳት የተማረው አካል ጉዳተኛ የግድ ዋጋ መክፈል አለበት፡፡ ሰው የመሆን ትርጉሙም ለሌሎች መኖር ነው፡፡ በነበረው የዘመን አስተሳሰብ ተገልለው የነበሩ አካል ጉዳተኞች ዛሬ ድረስ ተፅዕኖ አለባቸው፡፡ የሥጋ ደዌ፣ የአዕምሮ ውስንነት፣ ዓይነ ስውራንና ሌሎች ሰባት የሚደርሱ የአካል ጉዳት ያለባቸውን መርዳት የልብ ሸክምን ማዳመጥ ማለት ነው፡፡ የተማረው አካል ጉዳተኛ ያልተማረውን፣ ተምሮም ሥራ ማግኘት ያልቻለውን ቀድሞ ካልረዳ ማን ሊረዳ ነው? መንግሥት አካል ጉዳተኞችን አቅም በፈቀደ መጠን እረዳለሁ ሲል ሌሎችም እንዲረዱት በማሰብ ነው፡፡ በእርግጥ መንግሥት አካል ጉዳተኞችን ‹‹አቅም በፈቀደ›› ሳይሆን በሙሉ አቅም መርዳት አለበት፡፡ ከሌሎች እኩል የምንማርበት፣ የምንታከምበት፣ የምንጓዝበት፣ የምንኖርበት ዕድል መፈጠር አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- አሁን ላይ የተሻሉ ዕድሎችና አሠራሮች ብቅ እያሉ ነው ብለው አያምኑም?

አቶ ዮሴፍ፡- የተሻለ ነገር አለ፡፡ ከዜሮ አንድ ይሻላል፡፡ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት የዓይነ ስውራን ማኅበር ተመሥርቷል፡፡ የደረት፣ የእጅ፣ የእግር አካል ጉዳት ያለባቸው ማኅበር ለመመሥረት በ1980ዎቹ ጥረት ስናደርግ አልተሳካም ነበር፡፡ አሁን ላይ ተደራጁ እየተባልን ነው፡፡ የዘርፍ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የአካል ጉዳተኛው ጉዳይ እየተካተተ ነው፡፡ የሚኒስቴርና የዘርፍ መሥሪያ ቤቶች የአካል ጉዳተኞችንና የኤድስ ሕሙማንን አካተው እንዲሠሩ አዋጅ ወጥቷል፡፡

ሪፖርተር፡- አዋጆች፣ መመሪያዎችና ፖሊሲዎች ቢኖሩም መተግበሩ ላይ ክፍተት አለ ይባላል፡፡ ማኅበራችሁ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ምን ይሠራል?

አቶ ዮሴፍ፡- በተለይ ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ብዙ ሕጎች ወጥተዋል፡፡ ሆኖም አፈጻጸም ላይ መንግሥት ዛሬም ወገቤን ይላል፡፡ በአካል ጉዳተኛ ዙሪያ ያለው የመልካም አስተዳደር ችግር ከፍተኛ ነው፡፡ በመከራ ደረጃ እየወጡ የተማሩ አካል ጉዳተኞች ሥራ አላገኙም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ቁጭ ያሉ አሉ፡፡ ፖሊሲዎች አካል ጉዳተኛውን በሚደግፍ መልኩ ተቀምጠዋል፡፡ አስፈጻሚዎች የት አሉ? አስፈጻሚው የግድ አካል ጉዳተኛ መሆን አለበት? በከተማዋ ያሉት ሕንፃዎች ሁሉንም በእኩል አያስተናግዱም፡፡ አንድ ሕንፃ ለተለያዩ አገልግሎቶች ተገንብቶ ለአካል ጉዳተኛው ግን ተደራሽ አይደለም፡፡ አንድ ሕንፃ ሲገነባ ምን ማሟላት እንዳለበት በአዋጅ፣ በመመሪያ ተቀምጧል፡፡ በቅርቡ የተገነቡት እንኳን መመሪያውን አያሟሉም፡፡ አካል ጉዳተኛውን ሊታደግ የሚችል መንግሥት የለም ወይ? እስኪባል አብዛኞቹ ሕንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አይደሉም፡፡ አንዳንዶቹ ለአካል ጉዳተኛ መረማመጃ ቢሠሩም ምቹ አድርገው አልሠሯቸውም፡፡ በጣም የተንጋለሉ ናቸው፡፡ የተሠሩ መወጣጫዎች (ራምፖች) ምቹ አይደሉም፡፡ አንዳንድ ቦታዎች እሥረኛ ሊፍቶች አሉ፡፡ አካል ጉዳተኛውን ብቻ ሳይሆን ነፍሰጡርና አረጋውያንን ጭምር ያስጨንቃሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሊፍቶች ከሁለተኛ አንዳንዶቹ ከአራተኛ ፎቅ ይጀምራሉ፡፡ ጎዶሎ ቁጥር የማይሠሩባቸው አንድ ወደላይ ወይም አንድ ወደታች እንዲወርድ የሚያስገድዱም አሉ፡፡ እሥረኛ ሊፍቶች በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በተለያዩ ተቋማትም አሉ፡፡ ሕጉ ከወጣ መከበር አለበት፡፡ ግን እየተከበረ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- እንደ ማኀበር አካል ጉዳተኛውን ያማከለ ሕንፃ እንዲገነባ ሕንፃ ዲዛይን ከሚያደርጉ ባለሙያዎች ጋር ተመካክራችሁ አታውቁም?

አቶ ዮሴፍ፡- ሕጉ ራሱ ሕንፃ ዲዛይን የሚያደርጉ ሰዎች አካል ጉዳተኞችንም ታሳቢ እንዲያደርጉ ያዛል፡፡ ለአካል ጉዳተኛ የሚያስፈልግ መፀዳጃ፣ ሊፍት ውስጥ ለዓይነ ስውራን የሚሆን ብሬልና ሌሎችም መሟላት ያለባቸውን ሁሉ አንድ ሕንፃ እንዲያሟላ በሕጉ ተቀምጧል፡፡ በእኛ በኩል አቅም ያላቸውንና ጨረታ ተወዳድረው ሊያሸንፉ ይችላሉ ያልናቸውን አርክቴክቶች ጠርተን በአዲስ አበባና በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ውይይት አካሂደናል፡፡ በእነሱ በኩል የተነሳው ጉዳይ የሕንፃው ባለቤት እንደፈለገ የሚያዝ በመሆኑ ሕጉን ለመተግበር አለመቻሉን ነው፡፡ ሆኖም ችግሩ ከሕንፃ አስገንቢዎችም ቢሆንም አርክቴክቶች ባለሀብቶችን ስለሕጉ መምከር አለባቸው፡፡ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ፣ መኖሪያ ቤቶችም አካል ጉዳተኛውን ታሳቢ አድርገው መሠራት አለባቸው፡፡ የአቅም ችግርና ተጨማሪ ወጪ የሚሉት ጉዳይ ቢኖርም፣ አካል ጉዳተኛውም ተጨማሪ አገልግሎት ፈላጊ ይሆናል፡፡ አካል ጉዳተኛው ገንዘቡን ባንክ አስቀምጦ የማያወጣበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው፡፡ ብዙዎቹ በደረጃ የሚወጡ ናቸው፡፡ ዓይነስውራን ገንዘባቸውን ባንክ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ለማውጣት ግን እማኝ አብሮ መገኘት አለበት፡፡ ይህ ሁሉ ባንኮች በብሬልም ስለማያስተናግዱ ነው፡፡ በአውሮፓ ከአፍሪካም በደቡብ አፍሪካ ዓይነስውራን በራሳቸው ገንዘባቸውን ባንክ ማስገባትም ሆነ ማውጣት ይችላሉ፡፡ ሥርዓቱ ተዘርግቷል፡፡ አሳታፊ ሕግና ፖሊሲ ቢኖረንም ካልተገበርነው ዋጋ የለውም፡፡

ሪፖርተር፡- የተማረውን አካል ጉዳተኛ፣ በአካል ጉዳተኛው ዙሪያ ማሳተፍ ችግሮችን ለማቅለል ይረዳል፡፡ ማኅበራችሁ እነዚህ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይጎተጉታል?

አቶ ዮሴፍ፡- በግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራው አንዱ ጉዳያችን የተማረውን አካል ጉዳተኛ እባክህ ተሳተፍ እያልን መወትወት ነው፡፡ አንዳንዶች ደፍረን ወጥተናል፡፡ አንዳንዶች ለራሳቸው ብቻ ሆነው ቀርተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ መክረናል፣ ተወያይተናል፡፡ አመለካከት መገንባት ግን አስቸጋሪ ነው፡፡ የአካል ጉዳተኛውን ጉዳይ ልናስታምመው የሚገባ ፖለቲካ ነው፡፡ ብዙ መገለል፣ ጫና፣ ማኅበራዊ ነውጥ አለ፡፡ ሥራ ማግኘት፣ መማር መከራ ነው፡፡ በትምህርት ላይ ያለው አካቶ ትምህርት መልካም ነው፡፡ ጥሩ ነገር አለ፡፡ ግን አፈጻጸም ላይ ገና ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉንም ያሳተፈ ትምህርት ለማዳረስ ቢተጋም አካል ጉዳተኞችን የሚያሳትፉ ትምህርት ቤቶች እምብዛም የሉም፡፡ በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ቢሆን በጣት የሚቆጠሩት ናቸው ለአካል ጉዳተኛው የሚሆኑት፡፡ ይህም የግንዛቤ ክፍተት መኖሩን ያሳያል፡፡ ማኅበራችሁ ይህንን ለመቀልበስ ምን ይሠራል?

አቶ ዮሴፍ፡- የአካቶ ትምህርት ቢባልም፣ አካል ጉዳተኞችን የሚያስተናግዱ መሠረተ ልማቶች ገና ናቸው፡፡ ለምሳሌ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ላለባቸው ልጆች የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡት ጥቂት ናቸው፡፡ ማኅበራችን መንግሥትን በማስገንዘብና ችግሮችን በማሳየት ማኅበረሰቡ አካል ጉዳተኛ ቤተሰቡን ወደ ትምህርት እንዲልክ እንሠራለን፡፡ አካል ጉዳተኝነት ዘሎ የሚገባበት አይደለም፡፡ የመኪና አደጋ፣ የሕንፃ መፍረስ ብዙ ሌሎች አጋጣሚዎች ሙሉ አካል የነበረውን አካል ጉዳተኛ ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የአካል ጉዳተኛ አብዮት ተቀጣጥሎ ለውጥ እንዲመጣ፣ የተማረው አካል ጉዳተኛ መሳተፍ አለበት የምንለው፡፡ ብዙዎቹ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ተጎድተዋል፡፡ ይህ የአካል ጉዳተኛውን መብት ካለመጠበቅ የመጣ ነው፡፡ ስለአካል ጉዳተኛው በዓመት አንዴ ሳይሆን ችግሩ እስኪረግብና መስመር እስኪይዝ በየጊዜው መሠራት አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- የአካል ጉዳተኛው የአካል ድጋፍ ለማግኘት እንደሚቸገር በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የማኅበራችሁ አስተዋጽኦ ምን ይመስላል?

አቶ ዮሴፍ፡- ማኅበሩ የአካል ድጋፍ በነፃ አስመጥቶ ለአካል ጉዳተኛው ያከፋፍላል፡፡ የዚህ ተጠቃሚ የሚሆኑት የገቢ ምንጭ እንደሌላቸው የሚያረጋግጡና በተለይ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚኖሩ ናቸው፡፡ 2008 ዓ.ም. ላይ ግን የአካል ድጋፍ ጥራቱ የጎደለ ስለነበር አልሰጠንም፡፡ የአካል ጉዳት ድጋፍ በአብዛኛው የሚያስፈልገው ከዘራ፣ ክራንችና ብሬስ (ደግፎ የሚይዝ ብረት) ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለአካል ጉዳተኛ የሚያስፈልግ ድጋፍን በተመለከተ ያለው አገልግሎት እዚህ ግባ አይባልም፡፡ ዋጋው ውድ ከመሆኑም በላይ በጥራት አይሠራም፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ አምራች ነው ያለው፡፡ እሱም ችግር አለበት፡፡ ችግሩን የሚያውቁት መንግሥታዊ አካላትም መልስ አይሰጡም፡፡ በአካል ድጋፍ ችግር አካል ጉዳተኛው ጭንቀት ላይ ነው፡፡ ካለድጋፍ የማይንቀሳቀስ አካል ጉዳተኛ ምን ይሁን? አንዳንድ ክልሎች አገልግሎቱ አላቸው፡፡ ከአዲስ አበባ የአካል ድጋፍ ፍለጋ አርባ ምንጭ፣ ደሴ፣ ጂማ ድረስ የሚሄዱም አካል ጉዳተኞች አሉ፡፡ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መልስ መስጠት አለበት፡፡ ሌላው አገር ውስጥ መኪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች ለአካል ጉዳተኛው ከቀረጥ ነፃ አገልግሎት አይሰጡም፡፡ እኛን የሚያነጻጽሩን አውሮፓ ካለ አካል ጉዳተኛ ጋር ነው፡፡ በአገራችን አቅም ቢያነጻጽሩ ኖሮ አገር ውስጥ የተመረተውን መኪና ከቀረጥ ነፃ እንድንገዛ ይፈቅዱ ነበር፡፡ በአካል ጉዳተኛው ላይ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ችግሮቹም አካል ጉዳተኝነታችንን እንዳንረሳ እያደረጉን ነው፡፡ ደረጃ መውጣት ሲያቅተን፣ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ መግቢያ ስንቸገር እናስታውሰዋለን፡፡ ሥራ ለመቀጠር አሻራ መስጠት ግድ ነው፡፡ ጣት የሌለው ሰው በምኑ አሻራ ይሰጣል? እንደዚህ ዓይነት ክፍተቶችን እያዩ ማመቻቸት የመልካም አስተዳደር አንዱ አካል ነው፡፡ አካል ጉዳተኛው ሥራ ማግኘትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች የተገለለበትን ዘመን የሚክስ አሠራርና አፈጻጸም ያስፈልጋል፡፡

ሪፖርተር፡- አካል ጉዳተኞችን በትምህርቱ ማሳተፍ ችግሮችን ለመቅረፍ ወሳኝ ቢሆንም፣ ትምህርት ገብተው ሲያቋርጡ፣ ጭራሹንም ሲቀሩ ይስተዋላል፡፡ ማኅበራችሁ በዚህ ላይ ምን ሠራ?

አቶ ዮሴፍ፡- በ1990ዎቹ ዓ.ም. መጀመሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተነጋግረን በማታው ክፍለ ጊዜ አንድ ክፍል ውስጥ ሦስት ተማሪዎች በነፃ እንዲማሩ አድርገን ነበር፡፡ ቀን ይነግዳሉ ማታ ይማራሉ፡፡ ይህ ከ1ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ነበር፡፡ ሆኖም ከአራት ዓመት በላይ መሄድ አልቻለም፡፡ በኋላ ‹‹የልዩ ፍላጎት›› የሚል አጀንዳ መጣ፡፡ ብዙ ታግለን አሁን መሠረት ይዟል፡፡ ሆኖም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለአካል ጉዳተኛው የተመቸ ነገር የለም፡፡ ገና ናቸው፡፡ በግንዛቤ ሥራችን ሁሌም የምንወተውተውም የትምህርትን ጉዳይ ነው፡፡

 

 

Standard (Image)

‹‹ራሴን የለውጥ መሪ አድርጌ እመለከታለሁኝ›› ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

$
0
0

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በ1957 ዓ.ም. ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በባዮሎጂ ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ማስተርስ ዲግሪያቸውን ደግሞ በለንደን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በኖቲንግሪም ዩኒቨርሲቲ ሠርተዋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በመሆን ከ1998 ዓ.ም. እስከ 2004 ዓ.ም. ያገለገሉ ሲሆን እስከ 2009 ዓ.ም. መጀመሪያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሠርተዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለመሆን በመወዳደር ላይ ሲሆኑ ከተመረጡ የመጨረሻ ሦስት ዕጩዎች መካከል መሆን ችለዋል፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ‹‹ቱጌዘር ፎር ኤ ሄልዚየር ወርልድ›› በሚል መሪ ቃል ለዚህ ዓለም አቀፍ ኃላፊነት የሚያደርጉትን ውድድር በተመለከተ ዲቬክስ ከተሰኘ ድረ ገጽ ጋር ያደጉት ቃለ ምልልስ ወደ አማርኛ ተመልሶ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ጥያቄ፡- ይህንን ኃላፊነት መረከብ ለምን ፈለጉ?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- በእውነት ይህን ሥራ የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ፡፡ ልምድም እንደዚሁ፡፡ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ሥርዓት ማሻሻያዎች እንዲደረጉ አድርጌያለሁ የዚህን ውጤትም ማየትም ችያለሁ፡፡ በጤናው ዘርፍ እንዲሁም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባካበትኩት ልምድ አስፈላጊው የቴክኒክ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ዕውቀት አለኝ፡፡ ሥራውን የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ ስል የተወለድኩት፣ ያደግኩትም አፍሪካ ውስጥ ነው፡፡ በሽታ ማኅበረሰቦችን፣ የራሴን መንደርና እኔን ራሴን እንዴት እንዳጠቃን አውቃለሁ፡፡ እንደ ወባ ያሉና ሌሎች በሽታዎች የጤና ብቻም ሳይሆን የሚያስከትሉትን ኢኮኖሚያዊ ጫናም ተመልክቻለሁ፡፡ ይህን ማወቅ የኢኮኖሚክስ ዕውቀት አይጠይቅም፡፡ ሰዎች አልጋ ላይ ውለው ሰብል የሚሰበስብ ጠፍቶ ነበር፡፡ ሰዎች ለምን እንዲህ ይሰቃያሉ? ለምን ልናድናቸው አልቻልንም? ይህን ችግር ለምን አንፈታውም? የሚሉና ሌሎችንም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እንዳነሳ አድርጎኛል፡፡ ከዚያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በተለይም የወባ መቆጣጠሪያ ፕሮግራም አባል በመሆን የወባ ወረርሽኝ ምን ያህል ጥፋት እንዳደረሰ ተመለከትኩኝ፡፡ መከላከያዎችን በማድረግ ሕክምናዎችን በመስጠት ብዙዎችን ረዳን፣ የብዙዎችን ሕይወት አተረፍን፡፡ ቢሆንም የወረርሽኙ ተፅዕኖ በጣም ከባድ ስለነበር የሠራነው በቂ መሆን አልቻለም፡፡ ብዙዎች የአልጋ ቁራኛ በመሆናቸውና በመሞታቸው ሰብል የሚሰበስብ አልነበረም፡፡ ነገሩ አዕምሮ የሚረብሽና ሊቀበሉትም የሚከብድ ነበር፡፡ ለዚህ ነው ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ለጤናው ዘርፍ የምችለውን ሁሉ ማበርከት አለብኝ ያልኩት፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የሁለተኛ ዲግሪ ከዚያም ፒኤችዲና ሌሎችንም ጥናቶቼን ያደረግኩት፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበርኩበት ወቅት ወባ ላይ በጣም ሠርቻለሁ፡፡ ለዚህም ነው ባለፉት አሥራ ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የወባ ወረርሽኝ ያልታየው፡፡ ይህ የተሠራው ሥራ ክፍያ ውጤት ነው፡፡

ጥያቄ፡- ከራስዎ ልምድ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚያመጡት ተሞክሮ?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- በጠንካራ የጤና አገልግሎት ሥርዓት አስፈላጊነት አምናለሁኝ፡፡ እንደ ወባ ዓይነቱን በሽታ መዋጋት የሚቻለው በዚህ ዓይነቱ ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ እኛ ያደረግነው ወባን እየተዋጋን ጎን ለጎን የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት፣ የመረጃ መሠረተ ልማት፣ የሰው ኃይልና የጤና ዘርፍ ፋይናንሲንግ ግንባታ ጀመርን፡፡ በእርግጥ ረዥም ጊዜ ያገለገልኩ የአፍሪካ ሚኒስትር ነኝ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች አሳክተናል፡፡ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ሞትን በሁለት ሦስተኛ፣ የእናቶች ሞትን በ71 በመቶ፣ የኤችአይቪን ሞት በ90 በመቶ፣ እንዲሁም የቲቢ ሞትን በ64 በመቶ ቀንሰናል፡፡ የጠቀስኩት የጤና አገልግሎት ሥርዓት ማሻሻያና ግንባታ የተሠራው በዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ መሠረት ነው፡፡ ድርጅቱ ሁሉም የጤና ዘርፍ አካል ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ይፈልጋል፡፡ እኛም የተከተልነው ይህንኑ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ልምድ አለኝ፡፡ ኃላፊነቱንም በሚገባ ልወጣው እችላለሁ ስልም የዓለም ጤና ድርጅትን መመሪያ ስለተገበርኩት፣ በመመሪያው መሠረት የጤና ዘርፍ ማሻሻያዎችን ስላደረግኩኝና አገሮች ይህን እንዲተገብሩ መርዳት ስለምችል ነው፡፡ በዚህ በደንብ አምናለሁ፡፡ አድርጌዋለሁና በዓለም አቀፍ ደረጃም በተሻለ ደረጃ መመሪያው ተግባራዊ እንዲሆን አደርጋለሁ፡፡ የቦርድ ሰብሳቢ በመሆንም እንደ ግሎባል ፈንድ፣ የተመድ የኤድስ ድርጅት፣ ዓለም አቀፍ የእናቶች፣ የጨቅላና ሕፃናት ጤና አጋርነት ድርጅትና ሮልባክ ማሌሪያ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን መርቻለሁ፡፡ እንደ ጋቪና ቫክሲን አልያንስ ያሉ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቦርድ አባልም ነኝ፡፡ በተለይም በግሎባል ፈንድ እ.ኤ.አ. ከ2009 እስከ 2011 ያገለገልኩ ሲሆን ዓለም አቀፍ ልምድ አለኝ፡፡ ግሎባል ፈንድ ከግራና ከቀኝ ወቀሳ ሲሰነዘርበት ማሻሻያዎችን በማድረግ ለውጦች እንዲደረጉ አድርጌያለሁ፡፡ በዚህ ራሴን የለውጥ መሪ አድርጌ እመለከታለሁኝ፡፡ ዛሬ ግሎባል ፈንድ እንዴት እየገሰገሰ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይህ ይመስለኛል እኔን ከሌሎች ዕጩዎች የሚለየኝ፡፡ የሚፈለገው ልምድ አለኝ ስል እንዲሁ ዝም ብሎ ማውራት ሳይሆን የምለው የኖርኩትን፤ ያደረግኩትን ነው፡፡ የችግሮች ተጠቂ ነበርኩኝ፣ ችግሮችን እንደ ሚኒስትር ተጋፍጫለሁ፣ የጤናው ዘርፍ ላይ ለውጥ ማድረግ ብቻም ሳይሆን ውጤትም አስመዝግቤያለሁ፡፡ ይህን ኃላፊነት የፈለግኩበት ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ያለኝን የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲና የቴክኒክ ዕውቀቴን ያገናዘበ ነው፡፡ ለልማት የዋሉ የፋይናንስ ድርድሮችን በመምራት ለውጤት አድርሻለሁ፡፡ እነዚህ እነዚህ ልምዶቼ ሚዛን በጠበቀ መልኩ የዓለም ጤና ድርጅትን ይጠቅማሉ፣ ወደ ፊት ያራምዳሉ ብዬ አምናለሁኝ፡፡ ድርጅቱ እንዲሁ የቴክኒክ ድርጅት አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ ዕርምጃ ዓለም አቀፍ መሪም ያስፈልገዋል፡፡ የቴክኒክ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ዕውቀት ሚዛን መጠበቅ ያስፈልገዋል፡፡

ጥያቄ፡- የዓለም ጤና ድርጅት ዋነኛ ተግዳሮቶች ምንድናቸው ብለው ያስባሉ?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- ድርጅቱ ላይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ውጤታማ፣ ብቃት ያለውና ግልፅነት የተሞላ አሠራር ያለው ተቋም ያስፈልገናል፡፡ እዚህ ላይ የለውጥና መረጋጋት ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊነት ወሳኝ ነው፡፡ ማሻሻያ ስናደርግ ነገሮች እንዲፈጸሙ ማድረግ ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን፡፡ ምክንያቱም ዓለም ፈጣን ውጤቶችን ይጠብቃልና፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የድርጅቱን ተዓማኒነት ማረጋገጥ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡- ማሻሻያ ሊደረግባቸው ይገባል የሚሏቸው የተለዩ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- የማሻሻያ ለውጥ ስል ሰፋ አድርጌ ነው ነገሩን የምመለከተው፡፡ አንድ ነገር ይዞ ለውጥ አድርጌአለሁ አይባልም፡፡ ለውጥ የሚጀምረው መረጃዎችን ከመስማት፣ አገሮችን፣ አባል አገሮችን ከማድመጥ፣ ለውጥ የሚያስፈልገው የት ላይ እንደሆነ ከማወቅ ነው፡፡ የቱ ነገር ላይ ማሻሻያ ይደረግ ብቻም ሳይሆን መቼ የሚለውንም ማሰብ፣ ሁሉም አገር መሳተፍም ይኖርበታል፡፡ እኔ የማደርገው ይህን ነው፡፡ ሁሉንም የሚያሳትፍ የለውጥ ሒደት፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ሒደቱን የጀመርነው ያለውን ሁኔታ ከመገምገም ነው፡፡ በጥናቶች ውጤት መስማማት የማኅበረሰቡን ይሁንታም ማግኘት ነበረብን፡፡ ይህ ብቻም አይደለም የፖለቲካ መሪዎች፣ አገሮች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሲቪል ማኅበራትን ይሁንታ ማግኘት ነበረብን፡፡ እንደዚህ ነው ውጤታማ ማሻሻያ ማድረግ የቻልነው፡፡ ከሐሳብ ጀምሮ ማሻሻያና ለውጥ አካታች መሆን አለባቸው፡፡ እውነቱም ለውጦች መጀመር ያለባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ በማድመጥ መሆኑ ነው፡፡ ማሻሻያው ብዙ ነገሮችን ሊሸፍን ይችላል፡፡

ጥያቄ፡- ፋይናንሲንግ ከዓለም ጤና ድርጅት ችግሮች በዋነኝነት ይጠቀሳል፡፡ መጠቀም የሚችሉት የበጀቱን ሃያ በመቶ ብቻ በመሆኑ መጪው ዋና ዳይሬክተር ጫና ውስጥ ይገባል፡፡ ይህን በምን መንገድ ለመወጣት ያቅዳሉ?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- አባል አገሮች በ20 በመቶ መዋጮ ድርጅቱን የራሳቸው ማድረግ አይችሉም፡፡ በአንድ ኩባንያ ከ50 በመቶ በታች ሼር ካለህ ትልቅ ባለድርሻ አይደለህም፡፡ ቀላል መርህ ነው፡፡ ይህን ድርጅት የራሳችን እንዳላደረግነው ይህም ያለን ድርሻ 20 በመቶ ብቻ በመሆኑ እንደሆነ የዕጩዎች ፎረም ላይ ሐሳብ አንስቼ ነበር፡፡ መዋጮአችንን ከፍ በማድረግ ቁርጠኝነታችንን ማሳየት ይኖርብናል፡፡ ይህን ማድረግ የምንችለው በትንሹ 51 በመቶ መዋጮ በማድረግ ነው፡፡ አብላጫ ባለድርሻ ለመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይህ የሚታመንበት ነገር ነው፡፡ በዚህ መልኩ መዋጮ ጥሩ ካልሆነ ድርጅቱ የሚጠበቅበትን ማድረግ አይችልም፡፡ በአሁኑ ወቅት የአባል አገሮች በድርጅቱ ላይ ያላቸው በራስ መተማመን ዝቅተኛ ነው፤ ለዚያም ነው አገሮች አስተዋጽኦዋቸውን ከፍ እንዲያደርጉ የምጠይቀው፡፡ እኛም በፍጥነት ውጤት በማምጣት አገሮች በድርጅቱ እንዲተማመኑ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ነገሮች ተከውነው ውጤት መምጣት መቻል ይኖርበታል፡፡

ጥያቄ፡- የሚሏቸው ፈጣን ውጤቶች ምንድን ናቸው?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- ሊነሱ የሚችሉ ወረርሽኞችን መገመት ባንችልም ዝግጁ በመሆን የተሻለ መሥራት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ኢቦላ ላይ የነበረው ነገር የዓለም ጤና ድርጅት ክፍተት የታየበት ነበር፡፡ መሠረታዊ ነገሮቹ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ቀድሞ ማወቅ፣ አፋጣኝ ምላሽ፣ የቅኝት ሥርዓትን ማጎልበት፣ በአገሮች መካከል ያለውን ተግባቦት ማሻሻልና ዓለም አቀፍ የጤና ቁጥጥሮችን በታማኝነት ተግባራዊ ማድረግ ናቸው፡፡ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ይኖራሉ፡፡ አምስቱን ለይቼ አውጥቻለሁ፡፡ የመጀመሪያው ድርጅቱ ላይ ማሻሻያዎችን ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ዩኒቨርሳል የጤና ሽፋን ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ በተቀናጀ የመንግሥት ሥርዓት ቀድሞ ከማወቅ ጀምሮ የድንገተኛ ምላሽ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ አራተኛው በብዙ አገሮች ትኩረት የማይሰጣቸው እናቶች፣ ሕፃናትና ታዳጊዎች ላይ ማተኮር ነው፡፡ የሕዝብን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ክፍል ስታገልል ዕርምጃህ ያን ያህልም ተፅዕኖ አይኖረውም፡፡ አምስተኛው ደግሞ የአየር የአካባቢ ለውጥ ነው፡፡ ብልፅግና የሚያመጣው ጤናማ ማኅበረሰብ እንደሆነ በማመን የዓለም አቀፍ የልማት አጀንዳ ዋነኛ ነጥብ ጤና መሆን አለበት፡፡ ሁሉም መንገድ ወደ ዩኒቨርሳል ጤና ሽፋን የሚያመራ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ዩኒቨርሳል የጤና ሽፋን ማለት ማንም ከኋላ አይቀርም ማለት ነው፡፡ ተላላፊ፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣ የእናቶች ጤና በጉዳት ወይም በእርጅና ማንም ወደኋላ አይቀርም፡፡ የጤና ሽፋኑ የሥነ ሕዝብ ለውጦችንም የሚመለከት በመሆኑም በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ የዓለም ትኩረት ዩኒቨርሳል የጤና ሽፋን ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህን ሁሉም ይረዳል፣ ችግሩ ለውጥ አለማድረጋችን ነው፡፡ ማድረግ ብንችል ግን ብዙዎቹ የጤና ችግሮች መፍትሔ ያገኛሉ፡፡ ስለዚህም ትኩረታችን በዚህ መልኩ መቃኘት ይኖርበታል፡፡ በእርግጥ ትግበራው ቀላል አይሆንም፡፡ ይህ ኢትዮጵያ እንዴት ነው የሆነው? የሕክምና ባለሙያዎችን ማቆየት ትልቅ ችግር ሆኖ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ የሰው ኃይል ቀውሱ መሠረት የተማረ የሰው ኃይል ነው ብለን ማሰባችን ስህተት ነበር፡፡ ችግሩ ግን ውስጣዊ ነው፡፡ ያለውን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ እያሠለጠንን አልነበርንም፡፡ ስለዚህም ለሁለት ዓመታት በየዓመቱ ቅበላችንን ከ300 ወደ 3000 አሳድገን ነበር፡፡ ብዙዎቹን ትልልቅ ሆስፒታሎችን ወደ ማስተማሪያ ሆስፒታልነት ቀየርን፡፡ በተማረ የሰው ኃይል ፍልሰት አሁንም የሠለጠኑ ሰዎቻችንን እያጣን ቢሆንም በዓመት ከ2000 በላይ እያስመረቅን ነው፡፡ መፈታት ያለበት መሠረታዊ ችግሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ችግሩን የፈታነው እንዲህ ነው፡፡

ጥያቄ፡- የፈንድ አመዳደብ ላይ ያሉ ነገሮችን እንዴት ያስተናግዷቸዋል? ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ከሚገኘው ፈንድ ከፍተኛው ለኤችአይቪ የሚውል ነው፡፡  

ዶ/ር ቴድሮስ፡- ያደረግነው ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር መደራደር ነበር፡፡ ትልቅ የጤና ችግር የሆነው በሽታ ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ነገር ግን ደግሞ የጤና ሥርዓቱ ወደፊት የሚመጡ የጤና ችግሮችን መፍታት የሚችል ይሆን ዘንድ የጤና አገልግሎት ሥርዓቱ ላይም መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ነገርናቸው፡፡ በዚህ መሠረትም የጤና አገልግሎት ሥርዓቱ የመረጃ ፍሰት፣ የመድኃኒት አቅርቦት፣ የሆስፒታሎች ማኔጅመንትና የጤናው ዘርፍ ፋይናንስ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ችለናል፡፡ ሥርዓቱን እንዲሁ በጥቅል ሳይሆን ወባ፣ ኤችአይቪ፣ ቲቢ እንዲህ እንዲህ እያልን ነው የተመለከትነው፡፡ ቢሆንም ሥርዓቱንም በጥቅል መመልከት የሚያስፈልግበት ምክንያት አለ፡፡ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ሥርዓት ማሻሻያው በፔፕፋር፣ ግሎባል ፈንድ፣ በእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ድርጅትና በሌሎችም አገሮች ድጋፍ አግኝቶ ነበር፡፡ እናም የጤና ሥርዓቱ አሁን በጣም ጠንካራ ነው፡፡ ያደረግነው ድርድር በጣም ጥሩ ነበር፤ የጤና ሥርዓቱ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያለውን ጠቀሜታ ማሳየት ችለን ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ኢቦላን በሚመለከት ከተስተዋለው ነገር ለዓለም ጤና ድርጅት ትምህርት ይሆናል የሚሉት ነገር?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- ያሉንን ነገሮችና አመቺ ሁኔታዎች መመልከት ያለብን ይመስለኛል፡፡ በላይቤሪያ፣ ጊኒና ሴራሊዮን ችግሮች የነበሩ ቢሆንም በናይጄሪያ ግን ኢቦላ በጥሩ ሁኔታ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ናይጄሪያዎችን ይህን ማድረግ ያስቻላቸው ቀደም ሲል ለፖሊዮ የዘረጉት ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ ሌላ ነገር ከመፈለግ ይልቅ እጅ ላይ ያለውን ነገር መጠቀም መቻል ትልቅ ነገር ይመስለኛል፡፡ ለፖሊዮ በተዘረጋው ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ለኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ መስጠት ይቻላል እያልኩኝ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሥርዓቱ ለኢቦላ ኬዝም አገልግሏል በዚህ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ሌላ አማራጭ መፈለግ ጠቃሚ ሆኗል፡፡

ጥያቄ፡- ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ላይ ብዙ ወቀሳዎች ይሰነዘራሉ፡፡ አሁን እርሶ ለዓለም አቀፍ ኃላፊነት እየተወዳደሩ ነው፡፡ ለእነዚህ ወቀሳዎች ምላሽዎ ምንድን ነው?

ዶ/ር ቴድሮስ፡- የኢትዮጵያ መንግሥት በቁርጠኝነት ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት ላይ እየሠራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዴሞክራሲ ሒደት እንደሆነ የምንረዳውም ነው፡፡ ዴሞክራሲ የሚያድገው የሚጎለብተውም ከውስጥ እንጂ ከውጭ ይሆንሃል ተብሎ የሚታዘዝ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ደግሞ በግንባታ ላይ ያለ እንደመሆኑ ጉድለቶች ሊኖሩበት ይችላል፡፡ ዴሞክራሲ ሒደት ነውና፡፡ 

Standard (Image)

ዕውቅና ያልተቸረው ሐይቅ አሻጋሪ እጅ

$
0
0

 

 አቶ ስሜነህ ቃበቶ ይባላሉ፡፡ በዝዋይ ሐይቅ ካሉት አምስት ገዳሞች ደብረ አብርሃ በሚባለው ተወልደው ያደጉ ሲሆን በሐይቁ ላይ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የአቅማቸውን ለማበርከት ሞክረዋል፡፡ ተሰማርተውበት ከነበረው ንግድ ወደ ጀልባ ሥራ በመዞር ብዙ ጀልባዎችን ሠርተዋል፡፡ አሁንም ጀልባዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የእንጨትና የሞተር ጀልባዎች የሚሠሩትን አቶ ስሜነህን በሥራቸው ዙሪያ እንዲሁም ወደፊት ሊሠሩ ስላቀዱት ታምራት ጌታቸው አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የት ተወለዱ ዕድገትዎስ ምን ይመስላል?

አቶ ስሜነህ፡-የተወለድኩት ከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዝዋይ ከተማ ዝዋይ ሐይቅ ላይ ሲሆን፣ በሐይቁ ካሉት አምስት ደሴቶች ደብረ አብርሃ (አይሠት) በሚባለው ውስጥ ነው፡፡ ውልደቴም ከዛይ ማኅበረሰብ ሲሆን የቄስ ትምህርት በገዳሙ በመማር፣ ዘመናዊ ትምህርቴን ደግሞ በአካባቢው ከነበረው ስዊድን ሚሽን አዳሪ ትምህርት ቤት ተከታትያለሁ፡፡ የተግባርና የቴክኒክ ትምህርቴን እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቅኩት በዝዋይና በመቂ ከተማ ነው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እንዳጠናቀቅኩ ወዲያው ወደ ዓሳ ማጥመድና መንገድ ነበር ሥራዬ፡፡ ገዳሙንም በመልቀቅ በከተማዋ መኖር ጀመርኩ፡፡ በደርግ ዘመነ መንግሥት ከሐይቁ ዓሳ አጥምዶ መሸጥ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት ተግባር ስለነበር ፈቃድ በማውጣት ወደ አዲስ አበባ በመላክ ሥራውን በደንብ መሥራት ቻልኩ፡፡

ሪፖርተር ፡-ጀልባ ለመሥራት ምን አነሳሳዎት ንግዱ አላዋጣዎትም?

አቶ ስሜነህ፡- ሥራው ለእኔ በጣም አዋጭ ነበር፡፡ ምክንያቱም እንደዛሬው ሰዎች አልበዙበትም፡፡ የምንሠራው ጥቂት ሰዎች ነበር፡፡  ጀልባ እንድሠራ ያነሳሳኝ እኔ ያደግኩበት አካባቢ በሐይቅ የተከበቡ ደሴቶች ላይ ነው፡፡ እኔን ጨምሮ እዚህ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ከመሬት የራቁ በመሆኑ ከፍተኛ ትራንስፖርት ችግር በመኖሩ ዕድገታቸው ኋላ ቀር ነበር፡፡ ሕክምና ለማግኘት አስቸጋሪ ስለነበር ሟች ይበዛ ነበር፡፡ በተለይ ደሴቶቹ የተራራቁ በመሆናቸው መረዳዳት እንኳን አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሌላው በነዚህ ገዳማት በርካታ ጥንታዊ ቅርሶች ያሉ ሲሆን፣ ነዋሪው ማኅበረሰብ በራሱ ፈቃድ ነው የሚጠብቀው፡፡ ታዲያ ሁሌም ዓሳ ለማጥመድ ወደ ሐይቁ ስመላለስ ችግራቸውን በመመልከት ሐይቁ ላይ ለሚኖረው ኅብረተሰብ ትልቅ ችግር የሆነውን የውኃ ላይ ትራንስፖርት ላይ ብሠራ ነገሮችን እንደማሻሻል በማሰብ ነው የጀመርኩት፡፡

ሪፖርተር ፡-ጀልባ ለመሥራት ዕውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ይመስለኛል አደጋ እንኳን ቢደርስ በቦታው ቶሎ ለመድረስ ስለሚያስቸግር እንደዚህ ያሉ ነገሮችን ከግንዛቤ ማስገባት አላስፈለገም?

አቶ ስሜነህ፡-በመጀመሪያ የባህር ላይ ትራንስፖርትን ስቃዩን አውቀዋለሁ፡፡ ነገር ግን ደግሞ የተግባርና የቴክኒክ ተማሪ መሆኔ መነሻ ሆኖኛል፡፡ ከዛም በማንበብ የመርከብና የጀልባዎችን ንድፍ ዲዛይን እመለከት ነበር፡፡ ለአካባቢው እንዲመች በማድረግ የመጀመሪያዋን የእንጨት ጀልባ በ1984 ዓ.ም. ለወንድሜ በመሥራት ሙከራዬ በትክክል ተሳካ፡፡ ለእሱ የሠራሁት የሰው ማጓጓዣ ሲሆን፣ ሌላ የዓሳና የዕቃ መጫኛ ጨምሮ አሠራኝ፡፡ የእሱን እያዩ ለ16 ግለሰቦችና ለ20 ማኅበራት በጠቅላላው 36 የሰው ማጓጓዣ፣ ለዓሳ ማጥመድ፣ እንዲሁም የዕቃ ማጓጓዣ የሚሆኑ የእንጨት ጀልባዎችን በመሥራት ለኅብረተሰቡ አቀረብኩ፡፡ ስለዚህ ያለምንም ተጨማሪ ዕውቀት በመሥራቴ እንደልብ ባይሆንም የደሴቷ ነዋሪዎች መንቀሳቀስ ቻሉ፡፡ የሐይቁ ላይም ትራንስፖርት መሻሻል አሳየ፡፡

ሪፖርተር፡-መሥሪያ የሚሆን ግብዓትስ ከየት ነው የሚያገኙት በዲዛይን ስህተት ይሁን በአጠቃቀም እስካሁን በሠሩዋቸው ጀልባዎች ላይ የደረሰ አደጋ የለም?

አቶ ስሜነህ፡-ከአጠቃቀም ጉድለት የደረሰ አንድ አደጋ አስታውሳለሁ፡፡ በተረፈ  አላጋጠመኝም፤ ምክንያቱም ጀልባዎቹ ሲሠሩ ከራሳቸው ክብደት ውጪ እንደየአገልግሎቱ የመጫን አቅማቸው በምን ዓይነት የአየር ፀባይ እንደሚሄዱ ይለጠፍባቸዋል፡፡ ጀልባ አንደኛው ትምህርት እየወሰድኩ ነው የምሠራው፡፡ ሌላው ጊዜያቸውን ጠብቀው ይታደሳሉ በተለይ ውኃው የሚያገኘውን የጀልባ ክፍል የቅርብ ክትትል ይደረግለታል፡፡ ምክንያቱም ወደ ጀልባዋ ውኃ ገባ ማለት አደጋን መጥራት ማለት ነውና፡፡

ሪፖርተር ፡- ከባህላዊ ጀልባዎች የሞተር ጀልባዎች ለባህር ላይ ጉዞ ተመራጭ እንደሆኑ የአካባቢ ተጠቃሚዎች ይገልጻሉ፡፡ ይህንን ፍላጎት ለማሟላት ቶሎ ቶሎ መሥራት ይቻላል?

አቶ ስሜነህ፡- አንድ ጀልባ ሙሉ በሙሉ ሠርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ወር ይፈጃል፡፡ እኔ አሁንም የምሠራው በግቢዬ ውስጥ ነው፡፡ የምጠቀምበትም ማሽን መስኮትና በር በምሠራበት ማሽን ነው፡፡ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የመጣው የቁሳቁስ ዋጋ እንደልብ ሊያሠራኝ አልቻለም፡፡ ካፒታልም ስለሌለኝ በተሰጠኝ ቀብድ ነው ሥራውን የምጀምረው፡፡ ዛሬ የሚሠሩት ጀልባዎች ከ50-60 ሰው የመጫን አቅም ያላቸው፣   ለበርካታ ዓሳ አጥማጆች፣ እንዲሁም ብዙ ዕቃ ሊያጓጉዙ የሚችሉ ናቸው፡፡ እንደ ባለቤቱ ፈቃድ በሚገጠምላቸው ሞተር ፍጥነታቸውም የተለያየ ቢሆንም ከባህላዊዎቹ እጥፍ ይፈጥናሉ፡፡ የአገልግሎት ዘመናቸውም ቢሆን እድሳት እየተደረገላቸው ከአሥር እስከ 15 ዓመት አገልግሎት እየሰጡ ይቆያሉ፡፡ በዝዋይ ሐይቅ ላይ አሁን ከሚታዩት በርካቶቹ በእኔ የተሠሩ ናቸው፡፡

ሪፖርተር ፡- በሐይቁ ላይ ከሚታዩት ጀልባዎች ብዙዎች የአደጋ መከላከያ መንሳፈፊያ ልብስ የላቸውም፤ አደጋ ቢመጣ እንዴት ነው ሊከላከሉ የሚችሉት?

አቶ ስሜነህ፡-እኔ በመሠረቱ በዋናነት የምሠራው ጀልባውን ነው፡፡ በጀልባ ላይ ማዕበል ቢመጣ፣ ውኃ ወደ ውስጥ ገብቶ ጉዳት እንዳያደርስ መከላከያ ይሠራለታል፡፡ ሚዛን እንደጠበቀ በፍጥነት እንዲጓዝ ከአደጋ የጸዳ ጀልባ ማዘጋጀት ነው፡፡ ሁለተኛው ልክ እንደ እንጨት ጀልባዎች ሁሉ የሞተር ጀልባዎችም ላይ ስለጀልባዋ ሙሉ መረጃ የሚሰጥ ጽሑፍ ይለጠፍበታል፡፡ እዚህ ድረስ የእኔ ኃላፊነት ሲሆን፣ ይህን ብዬ ግን አልተውም፡፡ ከሠራሁላቸው በኋላ በተለጠፈው መሠረት እንዲጠቀሙበት እንዲሁም በሚጭኑት ሰው ልክ የአደጋ ማንሳፈፊያ እንዲያዘጋጁ በየጊዜው ውኃ የጀልባው የሚነካው አካል እንዲታደስ እንዲያደርጉ ትምህርት እሰጣለሁ፡፡ ግን ተግባራዊ አያደርጉም፡፡ የ40 ሰው መጫኛ ጀልባ ላይ 60 ሰው የሚጭኑም አሉ፡፡ ይህንን ባለማክበር የደረሰም አደጋ ነበር፡፡

ሪፖርተር፡-መቼ ነው አደጋው የተፈጠረው የደረሰው ጉዳትስ?

አቶ ስሜነህ፡-አደጋው የተከሰተው በ1998 ዓ.ም. ታኅሣሥ ወር ላይ ነበር፡፡ በወቅቱ ጀልባዋ ለዓሳ ማጥመጃና ማጓጓዥ የተሠራች  ነበረች፡፡ ባለቤቱ ግን ዓሳውንም፣ ሰውም፣ እንዲሁም በላይዋ ላይ የእንጨት ጀልባ ጭኖ ነበር የሚጓዘው፡፡ ከጀልባዋ አቅም በላይ የተጫነች በመሆኗ ሐይቁ ላይ በተነሳው ትንሽ ማዕበል የሰዎች ሕይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ እንግዲህ መጀመሪያ ላይ የመከላከል ሥራ ነው መሠራት ያለበት፡፡ ይህን ሁሉ አልፎ አደጋው ቢከሰት ደግሞ እንደድሮው ሳይሆን አሁን ጀልባዎች በሐይቁ ላይ በብዛት ስለሚንቀሳቀሱ መተያየት ይችላሉ፡፡ እሱም ካልሆነ ደግሞ ሞባይል በመጠቀም በአካባቢው ያሉ ጀልባዎች ቶሎ ስለሚደርሱ አደጋው ሳይከፋ መድረስ ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- ይህን ሥራ ሲሠሩ ያገኙት ድጋፍ አለ? ፈቃድስ አግኝተዋል?

አቶ ስሜነህ፡-ይህን ሥራ ከጀመርኩ ከሃያ ዓመት በላይ ሆኖኛል፡፡ 36 ባህላዊ ጀልባዎች፣ ከ30 በላይ ደግሞ የሞተር ጀልባዎችን ሠርቼ ለኅብረተሰቡ አቅርቤያለሁ፡፡ እነዚህን እየሠራው የዕውቅና ጥያቄ እንዲሁም የማምረቻ ፈቃድ፣ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጀምሮ እስከታችኛው ድረስ ጥያቄ አቅርቤ እስካሁን መልስ አላገኘሁም፡፡ በተጨማሪም ከየትኛውም የመንግሥት አካል ምንም ነገር አላየሁም፡፡ ሥራዬንም አይቶ አስተያየት የሰጠኝም የለም፡፡ ለወደፊት ይመጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- አንዳንዶች የጀልባ ዋጋ እየጨመረብን ነው ይላሉ፤ አንድ ጀልባ በምን ያህል ነው የሚሠሩት?

አቶ ስሜነህ፡-እኔ ይህን  ሥራ ስጀምር ማኅበረሰቡ እንዲያገለግል እንጂ ገንዘብ ለማግኛ ብዬ አልነበረም፡፡ ቀስ በቀስ ግን ሥራው መኖሪያዬ እየሆነ ስለመጣ በአነስተኛ ዋጋ እጠይቃለሁ የምሠራው በቤቴ በመሆኑ ከሚሠራበት ዕቃና ትንሽ የጉልበቴን በመጨመር ነው የማስከፍለው፡፡ አሁንም በሐይቁ ላይ ትራንስፖርት ተስፋፍቶ ማየት እንጂ እየነገድኩ አይደለም፡፡ ተወደደ የተባለውም ከዓመት ዓመት እየጨመረ በመጣው የዕቃዎች ውድነት እንጂ ለራሴ ጨምሬ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- እስካሁን በሠሩት ኅብረተሰብ ተጠቃሚ ሆኗል ብለው ያስባሉ? ወደፊትስ ምን አስበዋል?

አቶ ስሜነህ፡-እኔ ተሳክቶልኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ የሐይቁን የትራንስፖርት ችግር ቢያንስ 60 በመቶ ፈትቻለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ማረጋገጫው ምንድነው ቢባል፣ በሐይቁ ላይ የሚገኙ ደሴቶችና ገዳሞችን ለማየት የሚመጡ ቱሪስቶች መጨመር፣ ሌላው በተፈለገ ጊዜ ሲወጣ ትራንስፖርት መኖሩና በኮንትራትም መገኘቱ ነው፡፡ ለወደፊት በልጄ ረዳትነት እንዲሁም በቤቴና በተለመደ ማሽን መሥራት ይከብደኛል፡፡ መረዳዳት ያስፈልገኛል ብዬ አምናለሁ፡፡ እነዚህ እየተስተካከሉ የሚሄዱ ከሆነ ጣራ፣ መስኮት ምቹ መዝናኛ ያላቸው ቅንጡ ጀልባዎችን መሥራት እፈልጋለሁ፡፡ በቅርቡ ግን እሠራዋለሁ ብዬ የማስበው፣ ፈጣን የጀልባ አምቡላንስ ነው፡፡ አሁንም በአካባቢው የሚኖሩ ማኅበረሰቦች የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙት ሐይቅ አቋርጠው ነው፡፡  ስለዚህ ሙሉ የሕክምና መስጫ መሣሪያ የተገጠመለት ጀልባ ሆኖ ቢያንስ ሐይቁን እስከሚሻገሩ ሕክምና እያገኙ ይሄዳሉ፡፡ ሐይቁንም በደቂቃዎች ስለሚያቋርጡ ቶሎ ምድር ወዳለው ሕክምና መስጫ ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡

 

 

 

Standard (Image)

‹‹ሥነምግባርን በተመለከተ በትምህርት አሰጣጥ ላይ ክፍተት አለ››

$
0
0

ዶ/ር ደረጀ ንጉሤ፣ የኢትዮጵያ የፅንስና የማሕፀን ሐኪሞች ማኅበር ፕሬዚዳንት

ዶ/ር ደረጀ ንጉሤ የማሕፀንና ጽንስ ሕክምና ስፔሻሊስትና የኅብረተሰብ ጤና ባለሙያ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ1992 ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከ1997-2001 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማሕፀንና ጽንስ ሕክምና ስፔሻላይዝ አድርገዋል፡፡ በ2008 ዴንማርክ ከሚገኘው ኮፐንሀገን ዩኒቨርሲቲ በምርምር መስክ የድህረ ምረቃ ዲፕሎማ እንዲሁም በ2015 በኅብረተሰብ ጤና ከኩንዳን ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ጽንስና የማሕፀን ሀኪሞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡

የአፍሪካ የማሕፀንና ጽንስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባልና የዓለም የማሕፀንና ጽንስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አባልም ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማሕፀን ሐኪሞች ማኅበር (ኢሶግ) እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ዙሪያ ምሕረት አስቻለውአነጋግራቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡- የኢትዮጵያ የጽንስና ማሕፀን ሐኪሞች ማኅበር (ኢሶግ) ከ25 ዓመታት በፊት ሲመሠረት ዓላማው ምን ነበር?

ዶ/ር ደረጀ፡-እ.ኤ.አ በ1987 ናይሮቢ ኬንያ ላይ የሥነ ተዋልዶና የእናቶች ጤና ደኅንነትን በተመለከተ ጉባዔ ተካሄዶ ነበር፡፡ በ1989 ደግሞ አዲስ አባባ ላይ የዚሁ ጉባዔ ቀጣይ ስብሰባ ተደርጎ፣ በዋነኛነት በወቅቱ የነበረውን ከፍተኛ የእናቶች ሞት ለመቀነስ የባለሙያዎች ርብርብ አስፈላጊነት በምክረ ሀሳብነት የወጣበት ወቅት ነበር፡፡ ከዚህ ምክረ ሐሳብ በመነሳት ባለሙያዎችን አስተባብሮ የሚሠራና ስነ ተዋልዶ ላይ በቂ የሥራ ድርሻ ሊኖረው የሚገባ የሙያ ማኅበር ማቋቋም አስፈላጊነት ተሰምሮበት ነበር፡፡ ከዚህ በመነሳት የኢትዮጵያ የጽንስና የማሕፀን ሐኪሞች ማኅበር በ1992 ተቋቋመ፡፡ ሲቋቋም ራዕይ አድርጎ የተነሳው ማኅበረሰቡ የሥነ ተዋልዶ ጤናንና ይዘቶችን በሚገባ እንዲረዳ፣ የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ሲጠቀም ማየት ሲሆን፣ ራዕዩን ለማሳካት ደግሞ ሙያዊ ትግበራ የሚኖርበት ተገቢ መድረክ ማግኘት ነው፡፡ በተልዕኮ ደረጃ መረጃን መሠረት ባደረገ መልኩ የኅብረተሰብ ጥምር ትግበራ፣ የማኅበረሰብ አባላትን እንዲሁም የአገር ውስጥና የውጭ አጋሮችን በንቃት በማሳተፍ የሥነተዋልዶ ጤናን በአገሪቱ ማስፋፋት ነው፡፡ እንደ ግብ የተቀመጠው የሥነ ተዋልዶ ጤናን ደረጃ ሥነምግባር በጠበቀ ሁኔታ መደገፍና ማሻሻል ነው፡፡ ከእነዚህ ራዕይ፣ ተልዕኮና ግብ አንጻር ዘርዘር ያሉ ዓላማዎችም ተካተዋል፡፡ ከእነዚህ ከእነዚህ የሴቶችና ሕፃናት ጤና አጠባበቅና አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡ በተያያዘም በሥነ ተዋልዶ ጤና መስክ ላይ የሚወጡ ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ የዕቅድ ተፅዕኖ መፍጠር፣ በሥልጠናና ተገቢ እውቀትና የሥነ ተዋልዶ ጤና አሠራሮችን በማስፋፋት የሙያ ልቀትን ማሻሻል፣ የሥነምግባር ደረጃዎችን መደገፍ፣ በሥነ ተዋልዶ ጤና የሚያከናውኑ ማኅበራትና ድርጅቶች ማለትም በአገር ውስጥና በውጭ ካሉት ጋር በንቃት መሳተፍ፣ በተጨማሪም ለማኅበረሰቡ የሥነ ተዋልዶ ጥቅሞችን ማስገንዘብ በአጠቃላይም ለአገሪቱ ልማት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማድረግ ነው፡፡

ሪፖርተር፡-ሲቋቋም ያስቀመጣቸው ግቦች በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ መሠረት አድርገው ነው፡፡ ካለው እውነታ አንጻር ኢሶግ ምን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር ችሏል?

ዶ/ር ደረጀ፡-ማኅበሩ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ለመጥቀስም ያህል ያልተቋረጡ ውጤታማ ዓመታዊ ጉባዔዎችን በ25 ዓመታት ውስጥ አከናውኗል፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት፣ በአምስት ክልል ከተሞች ውስጥ ስድስት በአጠቃላይ ስምንት ቢሮዎችና ሠራተኞችን በመያዝ ተግባሩን እያከናወነ ነው፡፡ ሁለት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዶችን በሥኬት ተግብሯል፡፡ ሦስተኛውን ስትራቴጂክ ፕላን ለመተግበር በዝግጅት ላይም ይገኛል፡፡ ሁሉም የማሕፀንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያዎች የማኅበሩ አባል ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ወደ 318 የሚደርሱ የሙሉ ጊዜ አባላትና 76 የሚሆኑ ተባባሪ አባላት አሉን፡፡ በአብዛኛውም የስፔሻሊቲ ትምህርት በመማር ላይ ያሉ ይገኙበታል፡፡

ሪፖርተር፡-በአገሪቱ የሚገኙ የማሕፀንና ጽንስ ሐኪሞች በሙሉ የማኅበሩ አባል ናቸው ማለት ይቻላል?

ዶ/ር ደረጀ፡-አዎ! ሙሉ ለሙሉ አባል ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ከተከናወኑ ተግባራት ጋር በተያያዘ ባለፉት 25 ዓመታት ቁጥራቸው 21 የሚደርሱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንና የምርምር ሥራዎችን ሥነ ተዋልዶ ጤና እንቅስቃሴ ላይ አከናውኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከአገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር አራት በትግበራ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ ሥነ ተዋልዶ እንቅስቃሴዎች ሁነኛ አጋር በመሆን ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ እውቅናን ማግኘት የቻለ ማኅበር ነው፡፡ በሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ በተለይ በሦስተኛ ደረጃ ምጥ ላይ ከሚከሰተው ደም መፍሰስና ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ወገኖች የሕክምና እንክብካቤ ከማድረግ ጋር በተያያዘ የሥልጠና ማንዋል ተዘጋጅቷል፡፡ የቤተሰብ ዕቅድና ደረጃውን የጠበቀ የማስወረድ ሕክምና አሰጣጥ መግለጫ (ጋይድላይን)ም አዘጋጅቷል፡፡ ከዚህ በተረፈ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና አውደ ጥናቶችን አከናውኗል፡፡ በአፍሪካ ደረጃ የምሥራቅ፣ የመካከለኛውና የደቡብ አፍሪካ አገሮች የጽንስና የማሕፀን ሕክምና ፌዴሬሽን አባል ነን፡፡ በአህጉር ደረጃ የአፍሪካ የማሕፀን ጽንስ ሕክምና ፌዴሬሽን አባል ነን፡፡  በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓለም አቀፍ የጽንስና ማሕፀን ሕክምና አባል ነን፡፡ ላለፉት 25 ዓመታት ሥራችንን ሥንሠራ ከአጋሮቻችን በዋናነት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የተለያዩ የሙያ ማኅበራት በተለይ ከአዋላጅ ነርሶች ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ የሕክምና ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ የሕፃናት ሕክምና ባለሙያዎች ማኅበርና ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ጋር አብረን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎችና የሕክምና ትምህርት ቤቶች አጋሮቻችን ናቸው፡፡ በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ ከሚሠሩ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት ሠርተናል፡፡ በተያያዘም ከተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር ሠርተናል፡፡

ሪፖርተር፡- በእነዚህ ዓመታት 21 ያህል ፕሮጀክቶች ተሠርተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥናቶችም አሉ፡፡ በትግበራ ላይ ያሉም አሉ፡፡ የጥናት ዋና ዓላማ በግኝቱ ላይ ተመስርቶ ለችግሮች የመፍትሔ ማመላከት ነው፡፡ ኢሶግ የሠራቸው ጥናቶችምን ያህል ለፖሊሲ ግብዓትነት ውለዋል?

ዶ/ር ደረጀ፡-ከቤተሰብ ዕቅድ ጋር በተያያዘ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የትግበራ ጋይድ ላይን እንዲወጣ ሚና ተጫውቷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ለግልጋሎት የሚውል የድንገተኛ ጊዜ የወሊድ መከላከያ ላይ ጥናት አድርጎ ስርጭቱን በፓይለት ፕሮጀክት ሠርቷል፡፡ ከዚያም ወደ ትግበራ እንዲገባ አድርጓል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ በእርግዝና ጊዜ በሚከሰተው የደም ግፊት ሳቢያ በመድኃኒት እጥረት ተገቢ ሕክምና መስጠት የማይቻልበት ሁኔታ ነበር፡፡ ለዚህም በፓይለት ፕሮጀክት መድኃኒት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በማስመጣት፣ ሥልጠናም ተሰጥቶ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለይ ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃት ለሚደርስባቸው ሴቶች ሕክምና ከማሰጠት አኳያ እንዲሁም የችግሩን ስፋት በዳሰሳ ጥናት ከተረጋገጠ በኋላ ስድስት ቦታዎች ላይ ሞዴል ክሊኒኮች እንዲከፈቱ አድርጓል፡፡ በአዲስ አበባና በዋና ዋና ክልል ከተሞች በተከፈቱት ክሊኒኮች ባለሙያዎችን በማሰልጠን የሚያስፈልገውን ቁሳቁስና የሕክምና መርጃ መሳሪያ በመስጠት፣ በኋላም ሥራውን በሚሠሩበት ወቅት ተገቢውን ሙያዊ ድጋፍና ክትትል በማካሄድ፣ የሥልጠና መመሪያ ዶክመንቶችንና ጋይድ ላይኖችን አውጥቷል፡፡

ሪፖርተር፡-አስቸጋሪ የምትሏቸው ነገሮች ምን ነበሩ?

ዶ/ር ደረጀ፡-ማኅበረሰቡ ሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ ያለውን ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በቋሚነት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ‹‹ላንቺና ላንተ›› በሚል አምድ ግንዛቤ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ባለፈ ላለፉት ሰባት ዓመታት በሬዲዮ ፕሮግራም ላንተና ላንቺ በሚል ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ሆስፒታል በማሕፀን መውጣት ችግር ይሰቃዩ ለነበሩ 204 ሴቶች  አባላቶቻችንን በማስተባበር ሕክምና ሰጥተናል፡፡ በዚሁ ወቅት ለ546 ሴቶች ቅድመ የማሕፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ አድርጓል፡፡ ወደ ችግሮቹ ሲገባ የሥልጠና ጥራት ችግር አንዱ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ካሉን አራት ፕሮግራሞች አንዱ ከአሜሪካ  የማሕፀንና ጽንስ ሕክምና ማኅበር ጋር በተጓዳኝነት የምንሠራው ሥራ ስድስት ወር ሆኖታል፡፡ በዋነኝነት የስፔሻሊቲ ሥልጠና በተሻለ ጥራት እንዲሰጥ ለማድረግ የቴክኒክ ድጋፍ እያገኘን ሲሆን፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጋር በመሆንም እየሠራንበት ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ የቢሮ ችግር ዋናው ነው፡፡ ቢሮ በውድ ዋጋ ተከራይተን የምንሠራ በመሆኑ ከዘላቂነት አኳያ እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአምስት ክልሎች ውስጥ ስድስት ቅርንጫፍ ቢሮዎች አሉን፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች መልካም ፈቃድ ቢሮ አግኝተን እየሠራን ነው፡፡ ፋይናንስን በተመለከተም የምናገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት ከአስተዳደር ጋር አያይዘን ገንዘብ ባለመጠየቃችን ጥሩ የገንዘብ አቅም ላይ አልደረስንም፡፡ በአመዘጋገባችንም ገንዘብ በሚያመጣ ተግባር ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ ስለማንችል የገንዘብ አቅማችን የተገደበ ነው፡፡ ለአሁኑ ከአባላቶቻችን ባገኘነው የዓመት መዋጮና በዓመት አንዴ በሚኖረው ጠቅላላ ጉባዔ ከስፖንሰሮች በምናገኘው እንጠቀማለን፡፡

ሪፖርተር፡-የሕክምና ባለሙያዎች በየአምስት ዓመቱ ፈቃድ ለማደስ መውሰድ ያለባቸውን ሥልጠና ነው?

ዶ/ር ደረጀ፡-አዎ፡፡ መንግሥት በሕግ ደረጃ አስቀምጦታል፡፡ በየአምስት ዓመቱ የሙያ ፈቃድ ሲታደስ ባለሙያው በአምስት ዓመት 150 ወይም በዓመት 30 ተከታታይ የሥልጠና ክፍል መውሰድ አለበት፡፡ ይህንን በዓመታዊ ጉባዔ ወቅት በሚሰጡ ተከታታይ ትምህርቶች ብቻ ማሳካት አንችልም፡፡ ስለሆነም በየአካባቢው ባሉ ቢሮዎች  ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ተከታታይ ትምህርቱን ለመስጠት እያሰብን ነው፡፡ ይሁንና ባሰብነው መጠን ማካሄድ አልቻልንም፡፡ በኢንተርኔት መቆራረጥ ምክንያት በዚህ ይሰጥ የነበረው ሥልጠና ላይ ችግር ገጥሞናል ማለት እችላለሁ፡፡ ሌላው የማኅበሩን አባላት ዳታ ቤዝ በተገቢው ሁኔታ አደራጅተን እስካሁን አልያዝንም፡፡ በመጪው ዓመታት ክፍተቶችን ለመሙላት ጥረት እናደርጋለን፡፡

ሪፖርተር፡- እንደ ችግር ከተነሱት አንደኛው የገንዘብ አቅም ነው፡፡ አንዱ ገቢያችሁም የአባላት መዋጮ ነው፡፡ በብዙ ሙያዊ ማኅበራት የቁርጠኝነት ችግር አለ፡፡ በሙያም በገንዘብም ለመርዳት ብዙም ጥረት ሲደረግ አይታይም፡፡ በአብዛኛው ያለው አመለካከት ከማኅበሩ ተጠቃሚነት ላይ ነው፡፡ የአባላት መዋጮ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?

ዶ/ር ደረጀ፡-እስካሁን ማኅበራችን ከአባላት በዓመት የሚቀበለው 100 ብር አሁን ካለው ግልጋሎት አንጻር በቂ አይደለም፡፡ በመሆኑም ዓመታዊ ጉባዔ ላይ አቅርበነው ለማሻሻል ከስምምነት ተደርሷል፡፡ ያም ቢሆን ሥራዎችን ለማከናወን በቂ አይደለም፡፡ ከዚሁ ጋር በተጓዳኝ አባላት ጊዜ አግኝተው ለማኅበራቸው የማገልገል ችግር አለ፡፡ አብዛኛው አባላት በሆስፒታሎች፣ በጤና ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስለሚሠሩ ባሉበት ደረጃ በተገቢ ለማኅበሩ አስተዋፅኦ አድርገዋል ለማለት ይከብዳል፡፡ ለወደፊት አባላት በተገቢው ሁኔታ ይሳተፉ ዘንድ ከሳምንት በፊት ባደረግነው ጠቅላላ ጉባዔ ከስምምነት ተደርሷል፡፡ አባላት በየተሰማሩበት ቦታ ሆነው ማኅበሩን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ኢሶግ  ከሥነምግባር አንጻር የሚሠራቸው ተግባራት አሉ፡፡ በአገራችን በተለያዩ ጊዜያት የሕክምና የሥነምግባር ጉድለቶች እንሰማለን፡፡ ዳሰሳ ያደረጉ ሰዎች በተለይ በግሉ ዘርፍ ይበልጥ አትራፊ የመሆን ነገር እንዳለ ይናገራሉ፡፡ ይህ በሌላው ሕክምና ቢኖርም ወደ ማሕፀንና ጽንስ ሕክምና ሲመጣ  ተጋንኖ ይታያል፡፡ ለምሳሌ ነፍሰጡሮች በምጥ መውለድ እየቻሉ በቀዶ ሕክምና እንዲወልዱ የመገፋፋት ነገር ይስተዋላል፡፡ ሌሎችም የሥነ ምግባር ጉድለቶች ይስተዋላሉ፡፡ ይህን  እንደ ማኅበር መሪም ሆነ እንደ ባለሙያ እንዴት ያዩታል፡፡

ዶ/ር ደረጀ፡-የሥነ ምግባር ሁኔታን ከአባላት የሕክምና አተገባበር ጋር ስናይ፣ ማኅበሩ በግቦቹ ውስጥ ተገቢ ሥነ ምግባሩን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጥ በሚል አስቀምጦታል፡፡ እንደተባለው ያነሳሻቸው ችግሮች ይከሰታሉ፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ በቂ የሆነ የሕክምና ሥነ ምግባርን የተመለከተ ትምህርት አለመሰጠት እንደ አንድ ክፍተት አይተነዋል፡፡ ከዚህም በኃላ በተለያዩ የግል ሆስፒታሎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ባለሙያዎች ገንዘብ ከማግኘት አንጻር ብቻ በመገፋፋት ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን ሊያከናውኑ እንደሚችሉ ግንዛቤው አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከሥነ ምግባር ውጭ የሆኑ ነገሮች ሊከሰቱ የሚችሉት ራስን ከጊዜው ጋር ካለማስኬድና ከግዴለሽነት ጋር ተያይዞ ነው፡፡ አብዛኛው የማኅበሩ አባላት በተሰለፉበት ሙያ ተገቢውን አገልግሎት የሚሰጡ ቢሆንም ማኅበሩ አልፎ አልፎ ችግሩ እንዳለ ያምናል፡፡ ስለዚህ ይህንን ለመወጣት ሥነ ምግባርን በተመለከተ በሥራ አመራር ቦርድ የሚመራ ቋሚ ኮሚቴ አዋቅረናል፡፡ ኮሚቴው ከአሜሪካ የጽንስና የማሕፀን ሕክምና ማኅበር የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኝ ጠይቀን እያገዙን ነው፡፡ መሥራት የምንፈልገው በሥነ ተዋልዶ ጤና የሥነ ምግባር ደንብ እንዲኖረን፣ የማኅበሩ አባላት እንዲያውቁትና ተገዢ እንዲሆኑ ቅድመ ዝግጅት አድርገናል፡፡ ከዚህ ባለፈ ሥነ ምግባርን በተመለከተ በትምህርት አሰጣጥ ላይ ክፍተት አለ፡፡ ስለዚህ ለአባላት የተለያዩ ሥልጠናዎችን ከተከታታይ የሕክምና ትምህርት ጋር እንዲወስዱ፣ ባለሙያዎችን እየጋበዝን በሥነ ምግባር ላይ ያላቸው እውቀት የተሻለ እንዲሆን እየሠራን ነው፡፡ ሊሰመርበት የሚገባው ግን የእርጉዝ እናቶች ሕክምና እንደሌላው ሕክምና አለመሆኑ ነው፡፡ እርጉዝ ሴቶች በተፈጥሮ ደህና ይሁኑ እንጂ በያዙት ጽንስና ጽንሱ በሚያመጣው ስሜት የተነሳ ውስጣቸው ችግር አለ፡፡ ይህ እንደሌላው ሕመም በግልፅ ላይታይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ጤናማ መስለው እየታዩ ውስጣቸው ግን ችግር ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጽንሱ ለብቻው አንድ ፍጡር ነው፡፡ ስለዚህ እናትየው ባላት የተለያየ ችግር ጽንስ ሊጎዳ ይችላል፡፡ በመሆኑም ሁለት ፍጡሮችን በአንድ ጊዜ ማከም ተጨማሪ ኃላፊነት ያስከትላል፡፡ ከዚህ በተረፈ ምጥ ላይ እንዲሁም ከምጥ በኋላ የሚከሰቱ ችግሮች ስላሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንኳን ብዙ ጊዜ ለየት ባለ መልኩ ተጋላጭነተ ያለበት የሕክምና ዘርፍ ነው፡፡ በአሜሪካ ብናይ ብዙዎች ወደ ማሕፀንና ጽንስ ሐኪምነት የማይሄዱት የኢንሹራንስ ክፍያቸው ስለሚበዛ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ልጅ ሲወለድ አተነፋፈሱ ትክክል ካልሆነ፣ ቤተሰብ ይከሳል፡፡ ኦክስጅን በሰውነቱ በትክክል ካልተዘዋወረ ሲያድግ አዕምሮው ሕመምተኛ ሊሆን ስለሚችል ሐኪሙ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በዓለም ደረጃም እንደሌላ የሕክምና ዘርፍ ቀላል አይደለም፡፡ ሁለተኛው ሁሉንም ዓይነት የእርጉዝ ሴቶች ችግር፣ በምጥ ወይም በእርግዝና ጊዜ የሚያጋጥማቸውን ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም እጅግ በሕክምናው መጥቀዋል በሚባሉት አገሮች ላይ ራሱ ማስቀረት አይቻልም፡፡ ይህ ማለት የእናቶች ሞት ዜሮ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ እኛ አገር 'አንድም እናት አትሙት'የሚባለውን ነገር አልስማማበትም፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ውስጥ የእናቶች ሞት በ1000 እናቶች በ412 ላይ ነው፡፡ እነ አሜሪካና ስዊድን የደረሱበት ደረጃም ከ1000 ሺሕ እናት ከ20-30 ነው፡፡ ስለዚህ አንድም እናት አትሙት ሳይሆን በቀላሉ ማወቅ፣ መከላከልና፣ ማከም በሚቻሉ ችግሮች አንድም እናት አትሙት እሚለው ያስማማናል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በቅርቡ ያወጣው ጥናት ማሕፀንና ጽንስ አስመልክቶ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ሁኔታ በቀላሉ መከላከልና ማከም የሚቻለው 82 በመቶ ብቻ ነው፡፡ 18 በመቶው አይቻልም፡፡ በአገራችን ያለው የባለሙያ እጥረት፣ የመድኃኒትና የሕክምና መስጫ አቅርቦት ሲታከልበት ደግሞ ችግሩ ገዘፍ ይላል፡፡ ለእርጉዝ እናቶች አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ እየተደረጉና የማኅበራችን አባላትም የሚችሉትን እየሠሩ ከሕክምናው ውስብስብነት አንጻር እናቶችም ሆኑ ጽንሱ ጉዳት ሊደርስባቸው ወይም ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ ይህ ሲታይ ሁሉም ባለሙያ በግዴለሽነት አድርጎታል ወይም ሁሉም ባለሙያ በሁሉም ሁኔታ ላይ የሚገባውን ስላላደረገ የሕክምና ስህተት ተፈጽሟል ማለት አይደለም፡፡ የሚገባውን ያላደረገ ባለሙያ መጠየቅ አለበት፣ ያስጠይቃልም፡፡ ግን በአንጻሩ ልናያቸው የሚገቡ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ስለዚህ የሙያ ማኅበሩ ሥነ ምግባርን በተመለከተ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው፡፡ ከጤና ጥበቃና ከኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር በጋራ እየሠራን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ማኅበሩ 25ኛ ዓመቱን ሲያከብር ጥናት የተደረገባቸውን ልዩ ልዩ ጉዳዮች አንስቷል፡፡ ከእናቶችና ጽንስ አንጻር ያለብን ችግር የትኛው ነው?

ዶ/ር ደረጀ፡-ከጥር 25-27 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴልና ስፓ የማኅበራችንን 25ኛ ዓመት ጉባዔና የአፍሪካ ፌዴሬሽን ሁለተኛ ጉባዔ አንድ ላይ አካሂደናል፡፡ በዚህ ዓመታዊ ጉባዔ 450 ኢትዮጵያውያንን ተሳትፈዋል፡፡ እንዲሁም ከኡጋንዳ፣ ከቤኒን፣ ከናይጄሪያ፣ ከማላዊ፣ ከሱዳንና ከሩዋንዳ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡ አቻ የሙያ ማኅበራችን ከአሜሪካ ኮሌጅ 12 ባለሙያ ልኮ ተከታታይ ትምህርት በመስጠት ተሳትፈዋል፡፡ በዓመታዊ ጉባዔያችን በዋነኛነት የጉባዔው መሪ ቃል በዘላቂ ልማት ግቦች የስነ ተዋልዶ ጤና ሁነኛ አማራጭና ተግዳሮቶቹ ለአፍሪካ ምንድን ናቸው የሚል ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ የማሕፀንና ጽንስ፣ ከአፍሪካ የማሕፀንና ጽንስ ሕክምና ፌዴሬሽን፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲሁም ከዓለም ጤና ድርጅት ፓናሊስቶች ነበሩ፡፡ በውይይቱ አማራጮችንና ፈተናዎችን አይተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አራት የፓናል ውይይቶች ነበሩ፡፡ አንዱ በእርግዝና፣ ወሊድና ከወሊድ በኋላ በደም መፍሰስ ችግር ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችና የየአገሩ ሕጎች ምን እንደሚመስሉ ተወያይተናል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ከእርግዝና በፊት የእናቶችን የሥነ ወሊድ ሁኔታን ማስተካከል፣ በእርግዝና ጊዜ የአመጋገብ ሁኔታ ከማስተካከል አኳያና እድሜያቸው ገፋ ብሎ የሚያረግዙ እናቶች የሚኖራቸው አመጋገብ ለጽንሱ ዕድገት ከሚኖረው ጠቀሜታ አንጻር ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎች ምን እንደሚመስሉ ቀርቧል፡፡ በሦስተኛ ደረጃ የሕክምና ሥነ ምግባርን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ የጽንስና የማሕፀን ሐኪሞች ማኅበር ምን እየሠራ ነው? ምን ችግሮች አጋጠሙት የሚለውና የኢትዮጵያ የመድኃኒት የምግብና ጤና ክብካቤ ቁጥጥር ባለሥልጣን እንደተቆጣጣሪ ባለሥልጣን  በአሰራሩ ላይ ምንድነው የሚጠብቀው? እስካሁንስ ያሉ ችግሮች ምንድን ናቸው? በሚል ውይይት ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቅድመ ኮንፍረንስና ከኮንፈረንስ በኋላ ተከታታይ ትምህርት አካሂደናል፡፡ እነዚህ በተለያዩ የማሕፀንና ጽንስ ችግሮች ላይ የተካሄዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ አልትራሳውንድ፣ ሂስትሮስኮፒ (የውስጥ ማሕፀንን አጉልቶ የሚመለከት)፣ ሳይንሳዊ ጽሑፎች አቀራረብ፣ የማሕፀን ጫፍ ካንሰር፣ የማሕፀን ግድግዳ ካንሰርና ያለመውለድ ችግር በመሳሰሉ ላይ በበርካታ ዓለም አቀፍ ምሁራን ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 70 ያህል ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፣ ትንታኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ባሉ የሥነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች፣ በቤተሰብ ምጣኔ፣ በእርግዝና በወሊድና ከወሊድ በኋላ ባሉ ችግሮች፣ በውርጅና በተለያዩ የሴቶች የጤና ችግሮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡ 25ኛ ዓመታችንን ምክንያት በማድረግ ለማኅበሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ፣ ለማሕፀንና ጽንስ ሕክምና ትምህርት የሙያ ድርሻ ላበረከቱና በህክምናው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላደረጉት ለሁለት አባላት ማለትም ለፕሮፌሰር ሉክማን ዮሱፍና ለዶ/ር ይርጉ ገብረ ሕይወት የሕይወት ዘመን ሽልማት ሰጥተናል፡፡ ሽልማቱ ባለፉት ሦስት አሥር ዓመታት በሙያቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠትና ወጣት የማኅበሩ አባላት ተገቢውን ሥነምግባር የጠበቀ ግልጋሎት ለማበርከት ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በድንገተኛ ቀዶ ሕክምና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በተመለከተ የማኅበሩ አስተዋኦ ምንድን ነው?

ዶ/ር ደረጀ፡-በቅርብ ጊዜ ያካሄድነው ጥናት አለ፡፡ በድንገተኛ ቀዶ ሕክምና የሰለጠኑ ባለሙያዎችና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተሰማርተው የማሕፀንና ጽንስ እንዲሁም የቀዶ ሕክምና ባለሙያ በሌለበት ተክተው እየሠሩ ነው፡፡ ቢሳካልንና ቢኖረን ሁሉም ጋር የማሕፀንና ጽንስ ሐኪም ቢኖር መልካም ነበር፡፡ ስላልቻልን ግን በማስተርስ ደረጃ ሰልጥነው እየሠሩ ነው፡፡ የእነዚህ ሥራ ምን ይመስላል በሚል በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ 97 ሆስፒታሎች ላይ የሥራ ትግበራ ዳሰሳ አድርገናል፡፡ በሽተኛ የመረመሩበትና ያከሙበት ሰንጠረዥ፣ ቀዶ ሕክምና ክፍል እንዴት እንደሚሠሩና ተያያዥ የሕክምና ሒደቶችን ዳሰናል፡፡

ሪፖርተር፡- ማሕፀንና ጽንስ ላይ ብቻ ነው? ወይስ አጠቃላይ ሕክምና ላይም?

ዶ/ር ደረጀ፡-በአብዛኛው የሰለጠኑት እርጉዝ እናቶችን እንዲረዱ ተብሎ ነው፡፡ ነገር ግን አልፎ አልፎ ድንገተኛ ጉዳት ለደረሰባቸውና አስቸኳይ ቀዶ ሕክምና ይሠራሉ፡፡ በዋነኛነት ግን ማሕፀንና ጽንስ ላይ ነው፡፡ ሥልጠናው ላይ አብዛኛው አባላቶቻችን በአስተማሪነት ተሳትፈዋል፡፡ ስለሆነም አሠራሩ እስከምን ድረስ ተሳክቷል፣ ችግሮቹስ ምንድን ናቸው? በሚለው ዙሪያ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጥናት ተደርጎ ውጤቱ ደርሶናል፡፡ ስለዚህ ጥሩ አሰራሮች እንዲቀጥሉ፣ ያጋጠሙ ችግሮች  ደግሞ ባለሙያዎቹ የተሻለ ድጋፍ እየተደረገላቸው ባሉበት ቦታ እንዲሠሩ ማድረግ ነው፡፡ ይህ የተሻለ ሥራ ሰራን የምንለው ተግባር ነው፡፡ ሌላው ከእናት ወደ ጽንስ ኤችአይቪ እንዳይተላለፍ ላለፉት ሰባት ዓመታት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከሲዲሲ ኢትዮጵያ እንዲሁም ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመሆን በ70 ጤና ተቋማት ላይ ደረጃውን የጠበቀ ሕክምና እንዲሰጥ እገዛ አድርገናል፡፡ ከ48 እስከ 50 የሚሆኑ አርቲክሎችም ታትመዋል፡፡

 

Standard (Image)

‹‹ልጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ ምግብ ይኑር ነው የምንለው››

$
0
0

ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የኢትዮጵያ ስኩል ሚል ኢኒሼቲቭ መሥራችና ዋና ዳይሬክተር

     ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው የኢትዮጵያ ስኩል ሚል ኢኒሼቲቭ መሥራች ባለቤትና ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡ የተወለዱት አዲስ አበባ ሲሆን ያደጉት ደግሞ ቻግኒ ነው፡፡ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባህርዳር ከተማ አጠናቅቀው ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ አቅንተው ከካሊፎርኒያ ሜሪት ኮሌጅ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በሂውማንና ሶሻል ስተዲስ የመጀመሪያ ዲግሪና በዚሁ ዩኒቨርሲቲ በዴቨሎፕመንት ስተዲስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል፡፡ የሦስት ልጆች እናት ናቸው፡፡ በኢኒሼቲቩ ዙሪያ ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሮዋቸዋል፡

ሪፖርተር፡- የኢትዮጵያ ስኩል ሚል ኢኒሼቲቭን ለመመሥረት ያነሳሳዎት ወይም ምክንያት የሆነው ምንድነው? የተቋቋመውስ መቼ ነው?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-የሕፃናት አዕምሮ (ብሬይን) በምግብ ዕጦት የተጎዳ ከሆነ አምራች፣ ፈጣሪ፣ አሳቢና ችግር ፈቺ አይሆኑም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ የማሰብ፣ ችግር የመፍታትና የመመራመር ችሎታው በቀጥታ ከምግብ ጋር ይያያዛል፡፡ የምግብና የአዕምሮ ሳይንስ የሚለውም ይህንኑ ነው፡፡ ምግቡ ይበልጥ የሚፈለገው ደግሞ ገና በሕፃናት ዕድሜ ላይ እያሉ ነው፡፡ ካደጉ በኋላ የተጎዳውን አካል በምግብ መጠገን አይችሉም፡፡ ይህም በምርምር የተረጋገጠ ነው፡፡ ሕፃናት እየተጎዱ ሌላ ሀብት ፈጠራ የሚባል ሊኖር አይችልም፡፡ ስለመብታቸው የሚሟገቱ ሕፃናትን ይዞ የማይሄድ ሀብት ወይም ሥርዓት (ሲስተም) መጨረሻው አያምርም፡፡ በዚህም የተነሳ በሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት ውስጥ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ምግብ መኖር አለበት ከሚል በጎ አመለካከት የተነሳ የኢትጵያ ስኩል ሚል ኢኒሼቲቭ በሚል መጠሪያ የሚታወቅ የበጎ አድራገጎት ማኅበር ኅዳር 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቋቋመ፡፡

ሪፖርተር፡-ኢኒሼቲቭ በስንት ክልሎች ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-እስካሁን የሠራነው በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ በተጠቀሱት ክልሎች በሚገኙ 23 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርተ ቤቶች የሚማሩ ሕፃናት በየቀኑ ወተት ይጠጣሉ፡፡ ለዚህም የሚሆን በድምሩ 233 የወተት ላሞች በትምህርት ቤቶች ተመድበዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል በአማራ ክልል በሚገኙ 13 ትምህርት ቤቶች 124፣ በኦሮሚያ ክልል ባሉ አራት ትምህርት ቤቶች 39፣ በትግራይ ክልል ሦስት ትምህርት ቤቶች 30. በአዲስ  አበባ ሁለት ትምህርት ቤቶች 20፣ በደቡብ ክልል አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ አሥር ላሞች ተመድቦላቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ፕሮግራሙን የሚያስተዳድረው ኢኒሼቲቭ ነው ወይስ ለትምህርት ቤቶቹ ተላፎ ነው የተሰጠው?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-ፕሮጀክቱን የቀረጽነው አስተዳደሩ በትምህርት ቤት እንዲመራ በማድረግ ነው፡፡ ስለዚህም ሠርተን፣ ሥልጠና ሰጥተን፣ እስረክበን በሰው ኃይል አደራጅተን ነው የምንወጣው እንጂ አናስተዳድረውም፡፡ የሚያስተዳድሩት ትምህርት ቤቶቹ ናቸው፡፡ ራሳቸውን እስከሚችሉ ድረስ ግን ለአንድ ዓመት ያህል ውጭ ሆነን እንደግፋቸውና ከዛ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ራሳቸውን ችለው ይመራሉ፡፡

ሪፖርተር፡-ልጆቹ ወተት ብቻ ነው የሚጠጡት?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-ወተትና ዳቦ ነው የሚሰጣቸው፡፡

ሪፖርተር፡- ልጆቹን ማን ነው የሚመርጣቸው?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-ትምህርት ቤቱ ራሱ እንዲመርጥ ነው የምናደርገው፡፡ ብዙ ጊዜ የምንመክረው ግን ከቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የሚመጡም ካሉ ከሕፃናት ጀምረው ወደ ላይ እንዲሄዱ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ለፕሮግራሙ ስኬታማነት ምን ዓይነት ሞዴል ነው የመረጣችሁት?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-ኤስኤስኤም ማለትም ሲምፕል፣ ሰስተነብል፣ ማኔጀብል የተሰኘ ሞዴል ፕሮግራም ነው የመረጥነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሞዴል ለሁሉም ነገር ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡ ማለትም የኢመርጀንሲ (የአደጋ ጊዜ)  ዕርዳታ ዓይነት አቀራረብ የሌለውና ወይም ዘላቂ የሆነ፣ ውስብስብ የሆኑ ማሽኖችን የማይጠይቅ፣ ዓይነት ሞዴል ነው እየተጠቀምን ያለነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ ሞዴል ፕሮግራም የሚጀምረው የሰው ኃይል አደራጃጀቱ፣ ገቢና ደጋፊ ማግኘቱ ወይም ራሱን መደገፉ ተረጋግጦ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ አዲስ ነገር ሳይሆን የአካባቢውን ሕብረተሰብ ዕውቀት መሠረት አድርጎ የተነሳ መሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ካወቁት ያስቀጥሉታል ካላወቁት ግን ይቋረጣል፡፡

ሪፖርተር፡- ይህን ዓይነቱ አካሄድ በቅድሚያ ሙከራ ደረጃ ሠርታችሁ ነው ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ የገባችሁት? ወይስ በአንድ ጊዜ ለሁሉም አድርሳችሁ ነው የጀመራችሁት?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-በመጀመሪያ በሙከራ ደረጃ ሠርተን ነው ወደ ሙሉ ትግበራ የገባነው፡፡ በተግባር የተደገፈ የሙከራ ሥራ የተከናወነውም ሰበታ ከተማ በሚገኝ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ የሙከራ ሥራው የተከናወነው ለአራት ወራት ያህል የነበረ ሲሆን መጀመሪያ ጊዜያዊ በረት ሠራን፣ ላሞችን አስገባን፣ በዚህም የተገኘው ውጤት በጣም ጥሩና ያልተጠበቀ ሆነ፡፡ ወዲያው ታልቦ ለሕፃናቱ ስለሚሰጥ ፍሪጅ አላስፈለገም፡፡ በትራንስፖርት ችግር ምክንያትም አይቋረጥም፡፡ ምክንያቱም ላሞቹ ያሉት በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ወተቱ ከበረት በቀጥታ ወደ ክፍሎች ነው የሚሄደው፡፡ በበረቱና በመማሪያው ክፍሎች መካከል ያለው ርቀት በጣም ትንሽ ነው፡፡ ምግብ በራቀ ቁጥር በጥራትና በተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖራል፡፡ ምግብ ቅርብ በሆነ ቁጥር ርካሽና ትኩስ (ፍሬሽ) ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡- ወተቱን አፍልተውና ዳቦ የሚያቀርቡት እነማን ናቸው?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-አዘጋጅቶ የማቅረቡን ሥራ የሚያከናውኑት በደመወዝ የተቀጠሩ የተማሪዎች ወላጆች ናቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ዘመናዊ ዳያሪ ፋርም ዓይነት ነው ያቋቋምነው፡፡ በየዳያሪ ፋርሙ አንድ የእንስሳት ሐኪም፣ አምስት አላቢዎችና ወተቱን አፍልተው ለልጆች የሚሰጡ አሉ፡፡ እነዚህ ደመወዛቸው ከየት ይከፈል ስንል ወተት መሸጥ አለበት የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስን፡፡ ልጆቹ ተጠቅመው የተረፈውን እንዲሸጥ ለማድረግ በቀን ስንት ሊትር ወተት መመረት አለበት የሚለው ጥያቄ ተነሳ አንድ የፈረንጅ ላም በቀን በአማካይ 20 ሊትር ትሰጣለች፡፡ ስለዚህ ከአሥር የወተት ላሞች በቀን ከ100 ሊትር በላይ ወተት ይመረታል፡፡ ከዚህ አንፃር በቀን 35 ሊትር ያህሉን ለማኅበረሰቡ ብንሸጥ፣ የቀረውን ለልጆቹ ቢሰጥ ጥሩ ነው ብለን ነው ያሰላነው፡፡ አንድ ሊትር ወተት ደግሞ ለስድስትና ለሰባት ልጆች በቂ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በአንድ ትምህርት ቤት 10 የወተት ላሞች ቢገቡ በቀን  500 የሚሆኑ ልጆች ወተት እንዲያገኙ በማድረግ የዓመት ወጪ መሸፈን ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- ለአንድ ትምህርት ቤት ስንት ላሞች ነው የተመደበው?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡የሙከራው ሥራ ከተጠናቀቀ በኃላ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚተገበር ደረጃ (ስታንዳርድ) አወጣን፡፡ በዚህም ደረጃ ዳይሪ ፋርሙ በደንብ የተደራጀ እንዲሆን፣ አሥር የፈረንጅ ላሞች እንዲኖሩት፣ የምግብ ማብሰያውና የወተት ማፍያው ቤት፣ ስፋት፣ ቁመትና ርዝመት፣ እንዲሁም የሚቀጠሩ ሰዎች፣ የምን የምን ባለሙያዎች እንደሚሆኑ ትምህርት ቤቱ ደግሞ እዚህ ውስጥ ገብቶ ለመምራት ምን ዓይነት ሥልጠና ያስፈልገዋል የሚያደራጀውስ ኮሚቴ ምን መምሰል አለበት፣ የሚለውን በሚመለከት አንድ ዓይነት ደረጃ (ስታንዳርድ) አውጥተን በተንቀሳቀስንባቸው ክፍሎች ሁሉ ተግባራዊ አደረግን፡፡

ሪፖርተር፡- በወተት ላይ ብቻ ለምን ትኩረት ተደረገ? እንዳይሰለች ማለዋወጥ አይሻልም ነበር?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-ልጆች ወተት በየቀኑ ቢጠጡ አይሰለቻቸውም፡፡ በዛ ላይ ደግሞ ብዙ ንጥረ ነገር ያለው ነው፡፡ ሌላ ምግብ ቢቀርብላቸው ለአንድና ለሁለት ቀናት ያህል እሺ ብለው ሊመገቡ ይችላሉ፣ ዋል አደር ሲል ግን ይሰለቻቸዋል፡፡ የልጆች ባህሪ እንደዚህ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ምርጫችን ትክክል ነው፡፡ አዮዳይዝድ የሆነ ወይም በአዮዲን የበለፀገ ጨው ተጨምሮበት ከዳቦ ጋር ይሰጣቸዋል፡፡ ዳቦው የሚዘጋጀው በየአካባቢው ከሚገኘውና ከተለያዩ ጥራጥሬ ከተፈጨ ዱቄት ነው፡፡ ልጆቹ ወተቱ የሚሰጣቸው በቀን አንዴ ጠዋት ብቻ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶቹ እየተጠናከሩ ሲሄዱ ቁርስና ምሳ የማብላት አቅም ይኖራቸዋል፡፡ በተለይ ከሦስት ዓመት በኋላ ትምህርት ቤቶቹ ምሳ መስጠትና ሌላም ነገር መጨመር ይችላሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ቀጣዩ ዕቅዳችሁ ምንድነው?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-ኢትዮጵያ ውስጥ ከ23,000 በላይ የሚሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ በሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት ውስጥ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ምግብ እንዲኖር ማድረግ እናስባለን፡፡ ይኼንንም ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠይቀው በክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ የምግብ ፕሮግራሞችን ዲዛይን ማድረግ  ነው፡፡ ይኼም ማለት እኛ በየክልሉ እየተንቀሳቀስን የምግብ ፕሮግራም እንጀምራለን ማለት ሳይሆን የሚመለከታቸውን ተቋማት ማለትም ዩኒቨርሲቲዎች፣ የትምህርት ቢሮዎችንና የግሉን ዘርፍ ሁሉ በመቀስቀስ ወደ የሚፈለገው ፕሮግራም የማምጣት ጥረት ማድረግ ነው፡፡

ሪፖርተር፡-በእንቅስቃሴያችሁ ውጤት ላይ ያገኛችሁት ግብረ መልስ ምን ይመስላል?

ወ/ሮ ፍሬዓለም፡-ወተቱ በተጀመረ በወሩ ዘግይተውና እየቀሩ የሚመጡ ልጆች ቁጥር ቀንሷል፡፡ ልጆች በትምህርት አቀባበላቸው ላይ ንቁ ሆነዋል፡፡ ትምህርት የመቀበል ፍላጎታቸው ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ትምህርት ቤቶች በየቤቱ እየተዘዋወሩና ቅስቀሳ እያደረጉ ነበር ወተት የሚጠጡትን ልጆች የሚመዘግቡት፡፡ አሁን ግን ምንም ዓይነት ቅስቀሳ ሳይደረግና የምዝገባውም ጊዜ ሳይደርስ ወተት መጠጣት የሚፈልጉ ልጆች ቁጥር ጨምሯል፡፡ ልጆች ትምህርት ቤት ከመጡ በኋላ ወተት መጠጣታቸው የአዕምሮ እድገታቸው (ብሬይን ዴቨሎፕመንት) ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል? ወይስ አያደርግም የሚሉ ክርክሮች አሉ፡፡ አንዳንድ ሳይንቲስቲስቶች ልጆቹ እስከ 11 ዓመታቸው ምግብ ካገኙ የማስታወስ ችሎታቸው እንደሚሻሻል የተረጋገጡ መረጃዎች አለንም ይላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በዋናነት ጉዳት የሚደርሰው በ1,000 ቀናት ላይ ስለሆነ ከእነዚህ ቀናት ካመለጡ ለአካላቸው አስዋጽኦ አለው እንጂ የአዕምሯቸው ዕድገት ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም የሚሉ አሉ፡፡ እኛ በዚህ ምግብ ፕሮግራም በተጨባጭ ያየነው ውጤት ግን ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም አንድ ብርጭቆ ወተትና አንድ ዳቦ ተሰጥቶ ነው፡፡ ይኼ ሊሆን የቻለው ወተቱ ተፅዕኖ አድርጎ ነው ወይስ ሳይቀሩ ክፍል በመገኘታቸው ብቻ የተገኘ ውጤት ነው የሚለውን ደግሞ በሌላ ምርምር ማረጋገጥ ይጠበቅብናል፡፡

 

Standard (Image)

‹‹ለኢንዱስትሪ ፓርኩ መጋቢ ግንባታ ቦታ ተዘጋጅቷል› ›አቶ ደስታ ደንቦባ፣ በሲዳማ ዞን ዳዬ ከተማ ሽግግር አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

$
0
0

አቶ ደስታ ደንቦባ ይባላሉ፡፡ በሲዳማ ዞን የዳዬ ከተማ ሽግግር አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ናቸው፡፡ ዳዬ ከተማ የተቆረቆረችው በ1940ዎቹ አካባቢ ነው፡፡ በከተማው 6 ቀበሌዎች አሉ፡፡ ከ45 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የተመዘገቡ ነዋሪዎች አሏት፡፡ በዳዬ የተለያዩ ፓርኮች፣ ደኖች፣ እንዲሁም ፏፏቴዎች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በቱሪስት መስህብነት የተመዘገበው የቦቦራ ፏፏቴ አንዱ ነው፡፡ የከተማውን የልማት ሁኔታ በተመለከተ ሻሂዳ ሁሴንአቶ ደስታ ደንቦባን አነጋግራቸዋለች፡፡

 ሪፖርተር፡- ዳዬ የሽግግር ከተማ ሆና ማገልገል የጀመረችው መቼና እንዴት ነው?

አቶ ደስታ፡-ከዚህ ቀደም የወረዳ ጽሕፈት ቤት ሆኖ ያገለግል የነበረው ኛማ የሚባል ከተማ ነበር፡፡ ይሁንና ቦታው ወጣ ያለና ገጠራማ በመሆኑ ለአሠራር አይመችም ነበር፡፡ በመሆኑም በ1954ዓ.ም. ለብዙዎቹ ወረዳዎች ማእከል ሆና ዳዬ የወረዳ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቱ መገኛ በመሆን እንድትሠራ ተወሰነ፡፡ 2007 ዓ.ም. ሐምሌ ወር ላይ ደግሞ የሽግግር ከተማ አስተዳደር እንድትሆን ተደረገ፡፡ ከሽግግሩ ወዲህ በነበሩት 3 ቀበሌዎች ላይ ተጨማሪ 3 ቀበሌዎች ተጨመሩ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ሥራውን የጀመረው 2008 ዓ.ም. ጥቅምት ወር ላይ ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- የከተማው ኢኮኖሚ በምን ላይ የተመሠረተ ነው?

አቶ ደስታ፡- የከተማዋ ኢኮኖሚ ምንጭ ቡና ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴም ያለበት ቦታ ነው፡፡ እድገቷም በዚሁ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በአካባቢው ከቡና ውጪ የተለያዩ ሰብሎችም በጥሩ ሁኔታ ይመረቱበታል፡፡ አገሩ ለም ነው፡፡ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ገብስና የመሳሰሉት ሰብሎች ይመረታሉ፡፡ በሌሎች ገጠራማ በሆኑ አካባቢዎች ማለትም በ3 ቀበሌዎች ውስጥ እንሰትና ቡና በብዛት ይመረታሉ፡፡ በእነዚህ ቀበሌዎች የሚሠሩ አርሶ አደሮች በሰብል ወቅት በሚያገኙት ገንዘብ ኑሯቸውን ያሻሽላሉ፡፡ ወደዚህ እየመጡም ቤት ይሠራሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ከተማዋ የተቆረቆረችው በ1940ዎቹ ነው፡፡ ይህ ረጅም ዓመት የሚባል ቢሆንም ግን ዕድገት አላሳየችም፡፡ ይህ ከምን አንጻር ነው?

አቶ ደስታ፡- እኛ ከተማዋ ወደኋላ ቀርታለች የሚል እምነት የለንም፡፡ ምክንያቱም ከ100 ዓመት በላይ የቆዩ ከተሞች ነገር ግን ይህች ከተማ የደረሰችበት ገና ያልደረሱ ብዙ አሉ፡፡ ለምሳሌ ወደ ዳዬ ስትመጡ መንገዱ ላይ በንሳ ቀባዱ የሚባል ከተማ አለ፡፡ ከተማው ከዚህ ከተማ በፊት የተቆረቆረ ነው፡፡ ነገር ግን ከተማ ሳይሆን ቀበሌ ነው የሚመስለው፡፡ በዞናችን አሉ ከሚባሉ ከተሞች ውስጥ ፈጣን ዕድገት ያሳየው የኛ ከተማ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም ለከተማው ዕድገት መሠረት የሚሆኑ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡ ኅብረተሰቡም ደግሞ ታታሪና በደንብ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ጠንካራ የገቢ ምንጭ እንዲኖር አስችሎናል፡፡ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ የከተማው ተወላጅ የሆኑ ኢንቨስተሮች ሁሉ አሉ፡፡ እነዚህ ባለሀብቶች በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ በመሰማራት ለከተማው እድገት የበኩላቸውን እያደረጉ ነው፡፡ በከተማው ከ20 በላይ ሕንፃዎች አሉ፡፡ ብዙዎችም ሕንፃ ለመገንባት ፈቃድ አውጥተው ወደ ሥራ እየገቡ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከወረዳ ተለይቶ ከወጣ ወዲህ ትልቅ ለውጥ ታይቷል፡፡ በሁለት ዓመት ውስጥ ከተማዋ የራሷን በጀት ይዛ የራሷን አስተዳደር ይዛ ስትንቀሳቀስ ብዙ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡

ሪፖርተር፡- በከተማው ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ መሆኑን ሰምተናል፡፡ እስቲ አጠቃላይ ስለግንባታ ሒደቱና መቼ ተጠናቆ ሥራ እንደሚጀምር ይንገሩን?

አቶ ደስታ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በ2007 ዓ.ም. ዳዬን ጎብኝተው ነበር፡፡ በወቅቱ የአካባቢው ኅብረተሰብ ዩኒቨርሲቲ እንዲከፈት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ በተጠየቀው መሠረትም ፈቃዳቸውን ሰጥተው ግንባታው በዚህ ዓመት ተጀምሯል፡፡ ይህ ለከተማው ፈጣን ለውጥ እንደሚፈጥር ተስፋ አለን፡፡ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ በ2010 ዓ.ም. ተጠናቆም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡

ሪፖርተር፡- በከተማዋ ትልቅ የመንገድ ችግር ይስተዋላል፡፡  ችግሩን ለመቀነስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አሉ?

አቶ ደስታ፡- በከተማው ያለው የአስፓልት መንገድ አንድ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ በዚህ ዓመት የሚጀመር የ3 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ አለ፡፡ ጨረታ ወጥቶ ሥራው በቀጣይ ሚያዝያ ወር ይጀመራል ተብሎ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ የዚህ መንገድ ግንባታ በጀት በፌደራል መንግሥት የሚደገፍ ነው፡፡ ሌላው ከዳዬ እስከ ጅሪ የሚሠራ የ7 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ግንባታ ነው፡፡ ይህም በፌዴራል መንግሥት የሚሠራ ነው፡፡ እነዚህ መንገዶች ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ የከተማዋን ገጽታ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀይሩ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- በከተማው የተጀመሩ ሌሎች የልማት ሥራዎችስ አሉ?

አቶ ደስታ፡- ለወደፊት ኢንዱስትሪ ፓርክ በአካባቢው ለመገንባት መንግሥት ዕቅድ ይዟል፡፡ ዋናው የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚቋቋመው ይርጋለም ሲሆን እዚህ ለማቋቋም የታሰበው መጋቢውን ነው፡፡ ለዚህ ግንባታ የሚሆን ቦታም ተዘጋጅቷል፡፡

ሪፖርተር፡- በከተማው ምን ያህል የጤና ተቋማት አሉ?

አቶ ደስታ፡- በጤናው ረገድ እየታየ ያለው ለውጥም ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ከተማችን ውስጥ ለወረዳው አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ አንድ ትልቅ ጤና ጣቢያ አለ፡፡ በየቀበሌው የሚገኙ የተለያዩ ጤና ኬላዎችም አሉ፡፡ በ2008 ዓ.ም. ሥራ የጀመረ አዲስ ሆስፒታልም አለ፡፡ ሆስፒታሉ በአካባቢው ያሉ ወረዳዎችን ጭምር የሚመግብ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለመገንባትስ የታሰበ ነገር አለ?

አቶ ደስታ፡- የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታ በተወሰነ ደረጃ ተጀምሯል፡፡ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ተጀምሯል፡፡ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች ግንባታ ተጠናቋል፡፡ የድንጋይ ንጣፍም በዚህ ወር ይጀመራል፡፡ ይህ እንደተጠናቀቀ ነው የሚታሰበው፡፡ ሌላው ጨረታ ወጥቶለት ወደ ሥራ ሊገባ ያለ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አለ፡፡ ግንባታው ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት እስከ ጤና ጣቢያ የሚዘረጋ ነው፡፡ ሥራውም በዚህ ወር  ይጀመራል፡፡

ሪፖርተር፡- በከተማው የውኃ ችግር መኖሩን ተመልክተናል፡፡ አጠቃላይ የንጹህ ውኃ ተደራሽነት ምን ይመስላል? ተደራሽነቱን ከማስፋት አኳያስ የከተማው መስተዳድር ምን እያደረገ ይገኛል?

አቶ ደስታ፡- ውኃ የምናገኘው ከሁለት አቅጣጫ ነው፡፡ ከሰሜናዊና ከደቡባዊ ክፍል ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ግን ከደቡባዊ ክፍል የነበረው አንድ ፓምፕ በአጋጣሚ ተቃጥሎ በጥገና ላይ ነው፡፡ ይህ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚፈታ ችግር ነው፡፡ አካባቢያችን ደግሞ የውኃ ችግር የለበትም፡፡ ከዚህ በፊት ተከስቶ አያውቅም ወደ ፊትም አይከሰትም፡፡ በዙሪያችን የተለያዩ ምንጮች አሉ፡፡ ከሰሜናዊው ክፍል የሚመጣው ውኃ ደግሞ እንደ ድሮው በደምብ አላጠገበም እንጂ አልተቋረጠም፡፡ ከሱ የሚገኘው በፈረቃ ለተለያዩ ቀበሌዎች እየተሰጠ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? የመንገድ መብራቶች አለመኖራቸውን ታዝበናል፡፡

አቶ ደስታ፡- የመብራት ችግር የአገሪቱ ችግር ነው፡፡ የኃይል ማነስ ቢኖርም አገልግሎት እየሰጠ ነው የሚገኘው፡፡ ሰሞኑን ደግሞ አንድ ትራንስፎርመር ተቃጥሏል፡፡ ነገር ግን ከሞላ ጐደል ደህና ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የመቆራረጥ ሁኔታ ነበር፡፡ አሁን እየተሻሻለ ነው፡፡ የተቃጠለውም ቢሆን በቅርቡ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡ መንግሥት ነገሮችን በቅርበት ስለሚከታተል፣ ኅብረተሰቡም እኛ ለምንጠይቀው ጥያቄ ወዲያው ምላሽ ስለሚሰጥ ችግር የለም ማለት ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- በከተማው ያለው የትምህርት ተደራሽነት ምን ያህል ነው? ምን ያህል ትምህርት ቤቶችስ አሉ?

አቶ ደስታ፡- ከከተማችን አንጻር ያለው የትምህርት ተደራሽነት ጥሩ የሚባል ነው፡፡ አንድ የመሰናዶ ትምህርት ቤት አለ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም እንደዚሁ፡፡ ሁለት መለስተኛና አንደኛ ደረጃ፣ እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ አንድ ኢንደስትሪያል ኮንስትራክሽን ኮሌጅም አለ፡፡ ብዙ ወጣቶች በኮሌጁ በሙያ እየሠለጠኑ በግል በመደራጀት የተለያዩ ሥራዎች እየሠሩ ይገኛሉ፡፡

ሪፖርተር፡- አዲስ እየተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ሕንጻዎች አሉ፡፡ ይኼ በመልሶ ማልማት የሚታይ ነው ወይስ ከተማዋ አዲስ ፕላን አላት?

አቶ ደስታ፡- የቆዩ አሮጌ የመንግሥት ቤቶች አሉ፡፡ እነሱ እየተነሱ ባለሀብቶች እንዲገነቡበት ይሰጣቸዋል፡፡ አዲስ የሚከፈቱ መንገዶችም አሉ፡፡ የተሠሩት እየተነሱ በአዲስ ፕላን እየተሠሩ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በተገቢው መጠን እድገት ለማስመዝገብ ምን አይነት ድጋፍ ትፈልጋላችሁ?

አቶ ደስታ፡- ከተማዋ ጅምር ላይ ነች፡፡ ወደፊት ጥሩ ለውጥ ይመጣል ብለን እናስባለን፡፡ መንግሥት ከጎናችን ሆኖ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግልን እንፈልጋለን፡፡ ከዚህ ሌላ ደግሞ አካባቢው ካሽ ክሮፕ የሚመረትበት፣ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦች ያሉበት ሲሆን በእነዚህ ላይ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች በራችን ክፍት ነው፡፡

  

 

 

Standard (Image)

‹‹የኛ ባለድርሻዎች አብረውን ካልሠሩ ኤጀንሲው የቱንም ያህል ቢፍጨረጨር ስንዝር መጓዝ አይችልም››

$
0
0

አቶ ዘውዱ ወንድም፣ የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን፣ የትምህርትና የሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ተቋቁሞ ሥራ ከጀመረ ከአምስት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ የሦስተኛ ወገን መድን ላይ አተኩሮ የተቋቋመው ኤጀንሲው በሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ በኩል የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ይሠራል፡፡ ሆኖም ችግሮች አሁንም ይስተዋላሉ፡፡ ኤጀንሲው የሚስትዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን፣ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ዘውዱ ወንድም፣ ምሕረት ሞገስአነጋግራቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡- ከአምስት ዓመት በፊት የሦስተኛ ወገን መድን አስገዳጅ ሲደረግ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች መድኑን ለመግባት ብዙም ፍላጎት አላሳዩም ነበር፡፡ አሁን ላይ ይህ አመለካከት ተቀይሯል?

አቶ ዘውዱ፡-ኤጀንሲው በተለይ ወደ ተግባር ከገባ ከአምስት ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት በእያንዳንዱ ዘርፎች ለውጦች ይታያሉ፡፡ በ2004 ዓ.ም. ላይ ካሳ መክፈል ስንጀምር የነበረውንና አሁን የደረሰበትን ስናይ መሻሻሎች አሉ፡፡ በፊት በነበሩ ሕጐችም አንድ ተሽከርካሪ ጉዳት ሲያደርስ አሽከርካሪው ተይዞና ተጠይቆ ተጐጂውን የማሳከምና የማስካስ ሥራዎች የመድን ፈንድን አስመልክቶ በ559/2000 የወጣውና በኋላም በ799/2005 የተሻሻለው ነበር፡፡ አዋጅ መውጣቱ ያስገኘው ጠቀሜታ ለተሽከርካሪ ባለቤቱም ነው፡፡ በፊት በነበረው አሠራር ጉዳት አድራሹ ይያዛል፣ ክስ ይመሠረትበታል፣ ይወሰንበታል፡፡ ለሕክምናና ለካሳ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ይህ ተጐጂው ሕክምናና ካሳ እንዲያገኝ ሲያደርግ፣ ጉዳት አድራሹ ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ጉዳት በማድረሱ ካሳ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ይህም የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ያደርግ ነበር፡፡ አዋጁ መውጣቱ የተሽከርካሪ ባለቤቶች በዓመት አንድ ጊዜ በሚያወጡት ተመጣጣኝ የአረቦን ክፍያ መሠረት ዓመቱን በሙሉ እነሱን ተክቶ ኡንሹራንስ ኩባንያው እንዲከፍላቸው ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ወደ መጀመሪያው አካባቢ ይህን ካለመረዳት ብዙ ክፍተቶች ነበሩ፡፡ አደጋ ለማናደርሰው በየዓመቱ ለምን እንከፍላለን የሚሉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን አደጋ ቢያጋጥመንስ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ባጃጅ ወይም ባለሦስት ጐማ ተሽከርካሪ በዓመት ለሦስተኛ ወገን የሚያዋጣው ወደ 348 ብር ነው፡፡ በከፈለበት ዓመት ውስጥ ድንገት አደጋ ቢያጋጥም የኢንሹራንስ ኩባንያው በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ የሞት አደጋ ከ5 ሺሕ እስከ 40 ሺሕ ብር ካሳ ይከፍላል፡፡ በአካል ላይ ለሚደርስ ጉዳት እስከ 40 ሺሕ ብር ካሳ ይከፍላል፡፡ በንብረት ላይ ለሚደርስ እስከ 100 ሺሕ ብር ይከፍላል፡፡

ሪፖርተር፡- የሕክምናውስ?

አቶ ዘውዱ፡- ሁለት ዓይነት ሕክምና አለ፡፡ አንደኛው አስቸኳይ ሕክምና ሲሆን ሦስት ቦታዎች ላይ ይሰጣል፡፡ አደጋው በደረሰበት ቦታ፣ ወደ ሕክምና በሚጓጓዝበት ጊዜ በአምቡላንስ ውስጥና ሆስፒታል ደርሶ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ የሚሰጥ ሕክምና አስቸኳይ ሕክምና ይባላል፡፡ ይህ ሕይወትን ለማቆየት ለአልኮል፣ ለኦክስጅንና ለሌሎችም የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምናዎች ሲሆን እስከ 2 ሺሕ ብር በሚደርስ መታከም ይቻላል፡፡ ሁለተኛው ጉዳቱ ከፍተኛ ሆኖ ተመላልሶ ወይም ተኝቶ እንዲታከም ሐኪሙ በሚያዝበት ጊዜ አስቸኳይ ሕክምና መሆኑ ያበቃል፡፡ ተጐጂው ለካሳ ከሚሰጠው ገንዘብ ላይ እየታሰበ ቋሚ ሕክምና የሚከታተልበት አሠራር አለ፡፡ መድን መግባቱ ይህን ጥቅም ስለሚሰጥ አሁን ላይ ከአስገዳጅነቱ ባለፈ ይጠቅመናል በሚል ብዙ መሻሻሎች አሉ፡፡ ይህ ማለት ግን አመለካከቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀርፎ፣ ሁሉም አስፈላጊነቱን አምኖበታል ማለት አይደለም፡፡ የተሽከርካሪ ባለንብረት መድን ገብቶም አተገባበሩ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች አሉ፡፡ የአስቸኳይ ሕክምና ወጪን ለመሸፈን ከኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ከኤጀንሲው በአገሪቱ ይኖራሉ የሚባሉ ተጐጂዎችን መሠረት አድርጐና ገንዘብ ተዋጥቶ፣ የክልል ጤና ቢሮዎች በከፈቱት አካውንት ገብቶላቸዋል፡፡ ሆኖም ከክልል ክልል አተገባበሩ ላይ ልዩነቶች አሉ፡፡ የተሽከርካሪ ባለቤት የሦስተኛ ወገን መድን ገብቶ እያለ አደጋ ሲያደርስ ከኪሱ ከፍሎ የሚያሳክምበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለሆነም የተሽከርካሪ ባለንብረቶች መድን መግባታቸው የሰጣቸው ጠቀሜታ እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ እውነታም አላቸው፡፡ አሠራሩን ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ባለፈው ሪፖርት ስታቀርቡ አንዳንድ ክልሎች በተሽከርካሪ አደጋ ጉዳት ለሚደርስባቸው ወገኖች እንዲያውሉ የተሰጣቸውን ገንዘብ አለመጠቀማቸው ተነስቷል፡፡ ችግሩ ምን ነበር?

አቶ ዘውዱ፡- ሁሉም ክልሎች የሦስተኛ ወገን መድንን ሙሉ ለሙሉ ይተገብራሉ ወይም አይተገብሩም ማለት አይቻልም፡፡ ታዳጊ ያልሆኑ ክልሎች ተልዕኮ ወስደዋል፡፡ አፈጻጸሙ ከቦታ ቦታ ልዩነት ቢኖረውም ሕክምና ተቋማት አስቸኳይ ሕክምናውን ከሰጡ በኋላ ቅጽ ሞልተው ገንዘባቸው እንዲመለስ ሲጠይቁ ገንዘቡን መመለስ ጀምረዋል፡፡ እያንዳንዱ የተሽከርካሪ አደጋ ተጐጂ በየትኛውም ጤና ተቋማት ሄዶም ያለምንም ወጪ ሕክምና የማግኘት መብት እንዳላቸው እየተረዱ ነው፡፡ የሕክምና ተቋማትም ገንዘቡን እንዴት ማስመለስ እንደሚችሉ ሙሉ ግንዛቤና በራስ መተማመናቸው ዝቅተኛ ቢሆንም ይህንን ሕክምና በነፃ መስጠት እንዳለባቸው ተረድተው በነፃ የመስጠት ሁኔታዎች አሉ፡፡ ሆኖም ታዳጊ ክልሎች ሆነውም ገንዘቡን ያስቀመጡ፣ አዋጁን በቅጡ የማይተገብሩ አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ምክንያቱ ምንድን ነው?

አቶ ዘውዱ፡- የግንዛቤ ክፍተት አለ፡፡ አሳማኝ ምክንያት ባይሆንም አደጋ ብዙ ጊዜ አይከሰትም የሚሉ አሉ፡፡ በሌላ በኩል በሆስፒታሎች በኩል መተማመን አልተፈጠረም፡፡ ሕክምናውን ሰጥተን ቅጹን ሞልተን ገንዘቡን ማስመለስ እንችላለን ብለው መተማመን አላዳበሩም፡፡ ከዚሁ ጐን ለጐን ገንዘብ ለማስመለስ ፖሊስና ሕክምናውን የሰጠው ተቋም ቅጽ መሙላት አለባቸው፡፡ ብዙ ጊዜ አደጋ ሲደርስ ፖሊስ ይገኛል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ይህ ግን ሁልጊዜ እውነት አይሆንም፡፡ በመሆኑም የተጐዳውን ሌሎች ሰዎች ወደ ሕክምና ሊወስዱት ይችላሉ፡፡ ሌላም ሰው ቢወስደው ገንዘቡን ማስመለስ ይቻላል፡፡ በፖሊስ በኩል አደጋው ሲከሰት አልነበርኩም፣ ጤና ተቋሙ ያወጣውን ብር ለማስመለስ ቅጹን አንሞላም የሚሉ አሉ፡፡ አደጋ ቦታም ተገኝቶም ቢሆን በዕለቱ አደጋው መድረሱን ቅጹ ላይ ሞልቶ ሕክምና እንዲያገኝ ከረዳ በኋላ ሕክምናው አልቆ ጤና ተቋሙ ያመጣውን ወጪ ለማስመለስ በሚሞላው ቅጽ ላይ ፖሊስም እንዲሞላ ሲጠራ አለመገኘት አለ፡፡ ገንዘቡ በፍጥነት እንዳይመለስ ጤና ተቋማት ፖሊሲን፣ ፖሊስ ጤና ተቋማትን የማሳሰብ ነገር አለ፡፡ ይህ የሚታየው ወደ ሥራ የገቡት ክልሎችና ተቋማት ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ክልሎች ላይ ደግሞ ገንዘቡን ባንክ አስቀምጠው የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስን ተግባራዊ ያላደረጉበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ኢንሹራንስ አልጠቀመኝም እንዲሉ ረድቷል፡፡

ሪፖርተር፡- የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ከፍለው ነገር ግን አደጋ ባጋጠመ ጊዜ ተጠቃሚ የማይሆኑበት ሁኔታ በአንዳንድ ክልሎች ታይቷል፡፡ አሠራሮች እንዲቀየሩ ምን አድርጋችኋል?

አቶ ዘውዱ፡- የኛ ባለድርሻዎች አብረውን መሥራት እስካልቻሉ ኤጀንሲው የቱንም ያህል ቢፍጨረጨር አንድ ስንዝር መራመድ አይችልም፡፡ ለምሳሌ የአስቸኳይ ሕክምናን በሚመለከት ኤጀንሲው ገጭተው ባመለጡና መድን ሽፋን በሌላቸው ተሽከርካሪዎች የተጐዱ ወገኖችን መሠረት በማድረግ፣ 17ቱ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ደግሞ ባላቸው ደንበኞች ልክ ገንዘብ እናዋጣለን፡፡ ኤጀንሲውና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ያዋጡት ገንዘብ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በከፈተው አካውንት ገቢ ተደርጓል፡፡ ክልሎች ምን ያህል ተጐጂ ይኖራቸዋል በሚል ተሰልቶ ገንዘቡ ለአዲስ አበባና ለክልሎች ገቢ ተደርጓል፡፡ ኤጀንሲው በሕክምና ተቋማት ሥራ ስለማይገባ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለው መዋቅር ታች ድረስ ወርዶ ካልሠራ አንድ ስንዝር መራመድ አይቻልም፡፡ ገንዘብ ማስቀመጡ የመጨረሻ ግብ አይደለም፡፡ ለተጐጂዎች መዋል አለበት፡፡ ኤጀንሲው ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ክትትል እያደረገ ያሉትን ክፍተቶች ያሳያል፡፡ በዚህ ዓመትም ሁሉም ክልሎች ላይ አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ያለው ችግር ምንድን ነው ብለን ዳሰሳ አድርገናል፡፡ በ2007 ዓ.ም. ገቢ የተደረገን ብር አደጋ ቢኖርም ጥቅም ላይ ያላዋሉ አሉ፡፡ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ሥራው ላይ ስላልገቡ በ2007 ዓ.ም. ገቢ ተደርጐላቸዋል የተባለው ብር ገቢ አለመሆኑ የታወቀው በዚህ ዓመት ነው፡፡ ገቢ የተደረገውም ከሁለት ዓመት በኋላ ነው፡፡ አዋጁ የኅብረተሰብ ጥያቄን የሚመልስ፣ ሰዎች ጉዳት ተሸክመው ለሌላ ውጣ ውረድ እንዳይዳረጉ የሚያግዝ ስለሆነ የሚመለከተው በሙሉ ተባብሮ መሥራት አለበት፡፡ ኤጀንሲው ችግሮችን ለይቷል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ 23 የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችን አዘጋጅተናል፡፡ ከጤናውም ሆነ ከኢንሹራንሱ የሚመጡ አካላት ኃላፊነታቸውን በሚወጡበት ላይ እንወያያለን፡፡ ነገር ግን ተሽከርካሪዎች እስከገጠር ቀበሌ ከመግባታቸው አኳያ ሌላው ባለድርሻ ኃላፊነቱን ካልተወጣ ኤጀንሲው ብቻውን ለውጥ አያመጣም፡፡ ጥሩ መግባባቶችና ለውጦች ቢኖሩም ብዙ መሥራት ይጠይቀናል፡፡

ሪፖርተር፡- ጤና ተቋማት ያከሙበትን ብር ለማስመለስ የሚሞሉትን ቅጽ ፖሊስም መሙላት ይጠበቅበታል፡፡ ሆኖም ጤና ተቋማት ገንዘባቸውን ለማስመለስ በሚሞሉት ቅጽ አንዳንዴ የፖሊስን ትብብር ማግኘት አለመቻላቸው እንደ ችግር ተነስቷል፡፡ ይህንን ለመቅረፍ ምን ስልት ዘረጋችሁ? ፖሊስ በሌለበት መንገደኞች ተጐጂዎችን ሆስፒታል ቢያደርሱ እነሱን እማኝ ማድረግስ ይቻላል?

አቶ ዘውዱ፡- ፖሊስ ራሱ በባለቤትነት ሥራው የኔ ነው ብሎ መውሰድ አለበት፡፡ አደጋው ላይ የግድ መገኘት የለበትም፡፡ ሆኖም አደጋውን መመዝገቡ አይቀርም፡፡ በአደጋነት እስከተመዘገበ ድረስ፣ ጤና ተቋማት ለተጐጂው ያወጡትን ሕክምና ወጪ ተመላሽ እንዲያደርጉ ለሕክምና ተቋማቱ ማረጋገጫ መስጠት አለበት፡፡ ፖሊስ ካልመጣ ተጐጂ ከቦታው መነሳት የለበትም የሚል አሠራር የለንም፡፡ ተጐጂውን ይዞ የሄደ ሰው ተጐጂው ሕክምና እንዲያገኝ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ተቋሙ ያከመበትን ገንዘብ ለማስመለስ ግን ፖሊስ የሚፈርመው ነገር ካለ ተባባሪ መሆን አለበት፡፡ አደጋው እስከተመዘገበ ድረስ መተግበር ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ኦሮሚያ ላይ ጥሩ ተሞክሮ አለ፡፡ የኦሮሚያን ልምድ ለማለዋወጥም እየሠራን ነው፡፡ በአስቸኳይ ሕክምናና በአዋጁ ላይ በአብዛኞቹ ክልሎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አዘጋጅተናል፡፡ ሥልጠናም ተሰጥቷል፡፡ እስከ ወረዳ ድረስ ሁሉም በባለቤትነት ወስዶ መሥራትም አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- ከዚህ ቀደም ጤና ተቋማት አይከፈለንም በሚል ፍርኃት የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ለመስጠት አይፈልጉም ነበር፡፡ ይህ አመለካከት አሁን ላይ ተቀይሯል?

አቶ ዘውዱ፡- መሻሻሎች አሉ፡፡ በ2009 ዓ.ም. የመጀመሪያው ስድስት ወር ውስጥ ከ100 በላይ ጤና ተቋማት ብር እንዲመለስ አድርገዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የግል ሕክምና ተቋማት ላይ ከሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ መሻሻልም አለ፡፡ ይህ የሚያሳየው ወደ ሥራው እየተገባ መሆኑን ነው፡፡ ወደ ሥራ ባልተገባበት ጊዜ ችግሮችን እንኳን ለመለየት ተቸግረን ነበር፡፡ አሁን ብዙ ሕክምና ተቋማት አዋጁን ተግባራዊ እያደረጉ ነው፡፡ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ወደ ሥራ ያልገባ ክልል ብለን ከጥቂት ወራት በፊት ሪፖርት አቅርበን ነበር፡፡ ሆኖም ባለፈው አንድ ወር 60 ለሚሆኑ የተሽከርካሪ አደጋ ተጐጂዎች አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ ወደ ሥራው እየገቡ ስለመሆኑም ማሳያ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ገንዘቡ ለጤና ተቋማት ተመላሽ የሚደረገው ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች ነበር፡፡ ይህም ችግሮች ነበሩበት፡፡ አሁን ያለው አሠራር ምን ይመስላል?

አቶ ዘውዱ፡- ባልታወቀና መድን በሌለው ተሽከርካሪ ይጐዳሉ ተብሎ ለሚታሰበው ኤጀንሲው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ አዋጥቷል፡፡ 17 ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ባላቸው ደንበኛ ልክ አዋጥተዋል፡፡ በጤና ጥበቃ አካውንት ተከቶ እያንዳንዱ ክልል ምን ያህል ጉዳት ሊያጋጥመው ይችላል የሚለው ተሰልቶ የየክልልና የከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች አካውንት እንዲከፍቱ ተደርጐ ገንዘቡ ተልኮላቸዋል፡፡ አንድ የሕክምና ተቋም የግልም ሆነ የመንግሥት፣ በመኪና አደጋ ለሚጐዱ ወገኖች የሚሰጠውን አገልግሎት በገንዘብ አስልቶ ቅጽ በመሙላት ቅርብ ላለ ጤና ጽሕፈት ቤት ይሰጣል፡፡ አሥር ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ገንዘቡ እንዲተካም ይደረጋል፡፡ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር መሄድ አያስፈልግም፡፡ ሦስተኛ ወገን ስንል ካሳ ለመክፈል እንጂ አስቸኳይ ሕክምና ለመስጠት አይደለም፡፡ በፊት በነበረው አዋጅ 559/2000 ኢንሹራንሶች ይከፍሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ከመሆኑ አንጻር በርካታ ክፍተቶች ስለነበሩበት እንደገና አዋጁ ተሻሽሎ 799/2005 ከ2005 ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በፊት በነበረው አዋጅ አንድ የሕክምና ተቋም አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ጉዳት ላደረሰው ተሽከርካሪ ሽፋን የሰጠው ኢንሹራንስ የትኛው ነው ብሎ፣ ቅጹን ሞልቶ ከ17ቱ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ወደ አንዱ መሄድ ይጠበቅበት ነበር፡፡ ጉዳት ያደረሰው ተሽከርካሪ ያልታወቀ ከሆነ ብሩን ለማስመለስ መድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ መምጣት ይጠበቅ ነበር፡፡ አሁን ገንዘቡ እስከ ክልል ጤና ቢሮዎች አካውንት ስለገባ ቅጹን ሞልተው ወረዳ ጽሕፈት ቤት በመሄድ ገንዘቡ በአጭር ጊዜ እንዲመለስ ይደረጋሉ፡፡ አዲስ አበባ ላይም ጤና ቢሮ ገቢ የተደረገ ገንዘብ አለ፡፡ የግልም ሆነ የመንግሥት ጤና ተቋማት፣ አስተዳደሩ የሚያስተዳድራቸው ከሆኑ ከጤና ቢሮው፣ ፌዴራል የሚያስተዳድራቸው ደግሞ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ማስመለስ ይችላሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ካሳን በተመለከተስ?

አቶ ዘውዱ፡- ካሳ ሁለት ቦታ ይከፈላል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ ሦስት መሠረት ማንኛውም ተሽከርካሪ የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ሊኖረው ይገባል፡፡ ነገር ግን ይህ ሁልጊዜ እውነት አይሆንም፡፡ ኢንሹራንስ የገቡ ተሽከርካሪዎች ጉዳት ካደረሱ ኢንሹራንሳቸው እነሱን ተክቶ ካሳ ይከፍላል፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ጉዳት አድርሰው የሚሰወሩበት አጋጣሚ አለ፡፡ ስለዚህ በተሰወረ ተሽከርካሪ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ኤጀንሲው ይከፍላል፡፡ ተሽከርካሪው መድን ያልገባ ከሆነም የሚከፍለው ኤጀንሲው ነው፡፡ እኛ የምንክሰውን ከፖሊስ ጋር በመተባበር ተሽከርካሪው እንዲያዝ ተደርጐ ተጠያቂ ይደረጋል፡፡ ገንዘቡን ይከፍላል፣ ገጭቶ በማምለጡ በሌሎች ወንጀሎች በሚመለከተው አካል ተጠያቂ ይደረጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ካሳ ክፍያ ላይ ውጣ ውረዶች አሉ፡፡ አንዳንዶችም ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር መመላለስን በመጥላት ካሳቸውን ሳይወስዱ ይቀራሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች እናንተ ጋር ይመጣሉ? እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር የእናንተ ሥራ ምንድን ነው?

አቶ ዘውዱ፡- እንዲህ ዓይነት ችግሮች ያጋጥሙናል፡፡ ካሳ በኤጀንሲውና በኢንሹራንስ በኩል የሚፈጸም ቢሆንም አስፈጻሚው ኤጀንሲው ነው፡፡ ስለዚህ ዜጐች ኢንሹራንስ ኩባንያ ሄደው ካሳ በሚጠይቁበት ጊዜ የሚገጥማቸውን ችግሮች ኤጀንሲው ጋር ይዘው ይመጣሉ፡፡ የሕግ ክፍላችንም ወደ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እየደወለ የተሳሳቱ አሠራሮችን እናርማለን፡፡ አዋጁ የወጣው የተሽከርካሪ አደጋ ተጐጂ ሳያስብበት አደጋ አጋጥሞታል፣ አደጋ ተሸክሞ ሕክምናና ካሳ ለማግኘት መጉላላት የለበትም ከሚል ነው፡፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታም ሕክምናና ካሳ ማግኘት አለበት፡፡ በተሽከርካሪ ስለመጐዳቱ የፖሊስ ማረጋገጫ፣ የሞተ ከሆነ ደግሞ የሟች ወራሽነት ማረጋገጫ፣ የአካል ጉዳት ከሆነ የሕክምና ቦርድ ማስረጃ አሟልቶ እስከሄደ ተጐጂ ካሳውን ማግኘት አለበት፡፡ ተከራክሮ፣ ፍርድ ቤት ሄዶ የሚያገኝ ከሆነ የአዋጁ መውጣት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ አዋጁን በተሳሳተ መልኩ ከመረዳትና ከመተርጐም በመነሳት በአንዳንድ ኢንሹራንሶች ችግር ይታያል፡፡ ከአሽከርካሪው ወይም ከተሽከርካሪው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በማንሳትና ምክንያት በማስቀመጥ የተጐጂውን ካሳ መከልከል አይቻልም፡፡ ሆኖም በተገላቢጦሽ ሲደረግ ይታያል፡፡ ለምሳሌ መንጃ ፈቃድ ደረጃዎች አሉት፡፡ በዓይነትም ተከፋፍሏል፡፡ የደረቅ ተሽከርካሪ መንጃ ፈቃድ ኖሮት የሕዝብ ሲያሽከረክር ጉዳት አድርሷል በሚል ካሳ የሚከለክል አለ፡፡ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡ መድን ገቢውና መድን ሰጪው ተዋውለዋል፡፡ ከውለታ አንጻር የተፈጸመ ስህተት ቢኖር እንኳን ካሳውን ከፍለው ጉዳያቸው ሊሆን የሚገባው ኢንሹራንሱን ከገባው ጋር ነው፡፡ ተጐጂው በተሽከርካሪ መጐዳቱ ብቻ ከተረጋገጠ ካሳው ሊከፈለው ይገባል፡፡ መንጃ ፈቃድ በሌለው አሽከርካሪ፣ ከጭነት በላይ በጫነ ተሽከርካሪ የመጣ ጉዳት ካለ ለተጐጂ ካሳ ከፍለው የተሽከርካሪውን ባለቤት መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ከኢንሹራንስ ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች ወደ ኤጀንሲው ሲመጡ በተናጠል ቅሬታ የቀረበበት ኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር እንነጋገራለን፡፡ በእነዚህ ችግሮች ዙሪያ ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ነገር ግን ችግሩ ቀንሷል እንጂ አልቆመም፡፡ በተደጋጋሚ የምንወያይበት ይሆናል፡፡ የአዋጁ ጽንሰ ሐሳብ ተጐጂው ጉዳት ተሸክሞ ለሕክምናና ለካሳ ጥያቄ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥበት አይገባም የሚል ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ለሚያደርሱትና ለሚደርስባቸው ጉዳት ሙሉ ኢንሹራንስ (Comprehensive) ለሚገቡ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የሦስተኛ ወገን መድንም እንዲገቡ ይገደዳሉ፡፡ ለአንድ ተጐጂ ሁለት ካሳ የማይከፈል ቢሆንም መድን ለሚገባው ሁለት ወጪ ነው፡፡ ይህን ለማስታረቅ ምን ተሠርቷል?

አቶ ዘውዱ፡- ከዚህ ጋር ተያይዞ እየተከሰተ ያለ ችግር አለ፡፡ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ሦስተኛ ወገን ላይ ለሚደርስ ጉዳት ካሳ ለመክፈል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በሙሉ ኢንሹራንስ (በኮምፕርሄንሲቭ) አካተው ይሠሩ ነበር፡፡ አዋጁ ሲወጣ የራሱ አሠራር፣ ስቲከር ይዞ መጥቷል፡፡ አንዳንድ ኢንሹራንሶች በኮምፕሪሄንሲቭ አካተው ሲሰጡ አንዳንዶቹ ደግሞ ከኮምፕሪሄንሲቩ በተጨማሪ የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስም ያስከፍላሉ፡፡ ተገልጋዮች ሁለት ጊዜ ኢንሹራንስ እየከፈልን ነው ብለው ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ አዋጁ አስገዳጅ ስለሆነ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከኮምፕሪሄንሲቩ ውስጥ ሦስተኛ ወገንን ነጥለው እንዲያወጡ እየተነጋገርን ነው፡፡      

Standard (Image)

በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ቀውስ አለን?

$
0
0

 

አቶ ልዑል ተወልደ መድኅን ካሕሣይ ነዋሪነቱ በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ነው፡፡ ኮምቦልቻ ተወልዶ አዲስ አበባ ያደገ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1988 ዓ.ም. በአርክቴክቸርና በከተማ ፕላን በመጃመሪያ ዲግሪ ተመርቋል፡፡ ለአምስት ዓመታት የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት በሙያው ሠርቷል፡፡ ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ በማድረግ በሙያው እየሠራ ሲሆን፣ ባለው የቋንቋ ጥናት ዝንባሌም መሠረት በአማርኛና በትግርኛ ቋንቋዎች ላይ ጥናቱን እያከናወነ ነው፡፡ በቅርቡ “Proposed Language Reform for Ethiopia” የተሰኘ የጥናት መጽሐፉን በካናዳ ለኅትመት አብቅቷል፡፡ በመጽሐፉና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አቶ ልዑልን ሔኖክ ያሬድአነጋግሮታል፡፡   

ሪፖርተር፡- ያዘጋጀኸው መጽሐፍ ምንድን ነው? ይዘቱስ?

አቶ ልዑል፡- መጽሐፉ የተዘጋጀው በእንግሊዝኛ ነው፡፡ “Proposed Language Rerform for Ethiopia” የቋንቋ ሕዳሴ ለኢትዮጵያ እንደማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቋንቋዎቿን ታድስ ዘንድ ጊዜው አሁን ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በአገሪቱም የቋንቋ አጠቃቀም ተበላሽቷል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እንዲያውም መበላሸት ብቻ ሳይሆን የቋንቋ አጠቃቀም ቀውስ ውስጥ ነች እላለሁ፡፡ መጽሐፉ ውስጥ በዝርዝር ጠቅሼዋለሁ፡፡ ያም የሚያሳድረው ማኅበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ተጽእኖ ይኖራል፡፡ ኢትዮጵያ ለምታልመው ዕድገት እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች በቀውሱ ምክንያት ይኖራሉ፡፡

ሪፖርተር፡- የቋንቋ አጠቃቀም ቀውስ ውስጥ ነች ሲባል ምንድን ነው ማሳያው?

አቶ ልዑል፡- ቀውስ ያልተጠበቀ ውጤት የሚያስከትል ነገር ነው፡፡ አንድ ሒደት ባንድ መንገድ እንደሚሄድ ጠብቀኸው ውጤቱ ግን ከዚያ ውጭ ሆኖ ስታገኘው ለያዥ ለገላጋይ ያስቸገረ ነገር ቀውስ ተከስቷል ማለት ነው፡፡ በቋንቋ አጠቃቀማችን ውስጥ ቀውስ ስለመኖሩ እጅግ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ሰዋስዋዊ ጊዜ (ግራማቲካል ቴንስ) አንዱ ነው፡፡ ለምሳሌ ታምሜ ነበር፣ ታምሜያለሁ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ስለተከናወኑ ጉዳዮች ይናገራል፡፡ አግባብነት ያለውን ሰዋስዋዊ ጊዜ ካልተጠቀምኩኝ ግን መልዕክቴ የተዛባ ሊሆን ይችላል፡፡ በመግባባት ውስጥ ሰዋስዋዊ ጊዜ ትልቅ ተጽዕኖ አለው፡፡

ሌላው የሰዋስው ድምፆች አለመስተካከል በገቢርና ተገብሮ (አክቲቭና ፓሲቭ ቮይስ) የሚታየው ነው፡፡ ‹‹አበበ ጠረጴዛውን ሰበረው››፣ ‹‹ጠረጴዛው ተሰበረ›› ሁለቱ ተመሳሳይ መልዕክት ስለጠረጴዛው መሰበር አላቸው፡፡ ድርጊት የተፈጸመበት ነገር ጠረጴዛ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ሁለቱ ድምፆች አጠቃቀማቸው ለየቅል ነው፡፡ ገቢር ድምፅ ድርጊት ፈጻሚው ላይ ሲያተኩር፣ ተገብሮ ግን ድርጊት ተቀባዩ ላይ ነው ትኩረት የሚያደርገው፡፡

በአማርኛና በትግርኛ ላይ የማስተውለው ሰዎች ድርጊት ፈጻሚውንና ተቀባዩን አዛብተው ያስቀምጣሉ፡፡ ብዙ ናሙናዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ‹‹ራበኝ›› የሚለውን በምሳሌነት መውሰድ እንችላለን፡፡ በእንግሊዝኛ እንዳለው ተሸጋጋሪ ግሶች (transitive verbs) እና ኢተሸጋጋሪ ግሶች (intransitive verbs) በተጨማሪ በአማርኛና በትግርኛ ውስጥ እኔ እንደደረስሁበት ‹‹ኢተሸጋጋሪ›› በሁለት ይከፈላሉ፤ አክቲቭ ኢተሸጋጋሪና ፓሲቭ ኢተሸጋጋሪ የሚባሉ አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ገቢርና ተገብሮ ማለት ነው?

አቶ ልዑል፡- እንደዚያ ሊሆን ይችላል፡፡ የአማርኛውን ስያሜ ቃል ብዙ ስላለመድሁት፡፡ ‹‹ራበኝ›› ስንል ድርጊት ፈጻሚና ድርጊት ተቀባይ ልንከትበት ማለት ነው፡፡ ይህ የማይሻገር ግስ ስለሆነ መሆን ያለበት ‹‹ተራብሁ›› ነው፡፡ ሌላው ችግር ማብዛት ላይ ነው፡፡ ስሞችን፣ ቅጽሎችን ባጠቃላይ የቃላት አበዛዝ ላይ ችግሮች አሉ፡፡ አማርኛ የቃላት አበዛዝ ሕግጋት አሉት፡፡ በዢ ቃላትን ሳናበዛ ግን በብዙ ቁጥሮች ብቻ ተጠቅመን መጥቀስ ተገቢ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ‹‹ሁለት በሬ›› ብለን መቆም አንችልም፡፡ ‹‹ሁለት በሬዎች›› እንጂ፤ ረዥም ሰዎች ሳይሆን ረዣዥም ሰዎች፡፡ ብዜት ላይ የሚታይ ሌላው አንዳንዶች መንግሥታቶች፣ ዓመታቶች ይላሉ፡፡ ይኼ ድርብ ድርብርብ የሆነ የአበዛዝ ነገር በመሆኑ በሰዋስው አነጋገር ጸያፍ ነው፡፡ ዓመታት ከግእዝ የተወሰደ ነው፡፡ የአማርኛ የማብዣ መንገድ ‹‹ኦች››ን ወስደህ ይህን ከግእዝ በተወሰደው ብዛት አመልካች ‹‹ኣት›› ጨምሮ ማቅረብ አይገባም፡፡ ከግእዝ የተወረሱት የአበዛዝ መንገዶች ፎርም ከሥነ ጽሑፍ አንፃር ተወዳጅነት አላቸው፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ አንዱን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

ቀጥሎ ልጠቅስ የምችለው የቃላት አመራረጥ ነው፡፡ ከዚህ ጋር የሚያያዙ ይፋዊና ይፋዊ ያልሆኑ አነጋገሮች አሉ፡፡ ሊገኙ የማይገባቸው ቦታ ላይ የሚገኙ መንደርኛ አነጋገሮች አሉ፡፡ የቃላት አመራረጥን ስንመለከት የቃላት እጥረት ወይም ድህነት አለብን፡፡ ከብዙ አሠርታት በፊት ጀምሮ የታወቀ ድህነት ነገር ነው፡፡ አፄ ኃይለሥላሴ ለአንድ የቋንቋ ባለሙያ በ1920ዎቹ በጻፉት ደብዳቤያቸው ላይ የቋንቋ ድህነት እንዳለብን ጠቅሰው ነበርና የታወቀ ነው፡፡ ቮካብለሪያችን ወይም የቃላት ብዛት የለንም፤ ሲኖሩንም በአግባቡ አንጠቀምባቸውም፡፡

ለምሳሌ ሰዎች ‹‹ከእንቅልፌ ተነሳሁ›› ወይም ደግሞ ‹‹ተነሳሁ›› ይላሉ፡፡ ከመኝታ መንቃታቸውን ለማሳየት መሆን ያለበት ነቃሁ ነው፡፡ መነሳት በአካል ብድግ ብሎ መውረድን ያካትታል፡፡ አካላዊ ነገር ነው፡፡ መንቃት ግን አዕምሮአዊ ነገር ነው፡፡ እነኚህ በማኅበራዊ ሕይወት ብዙ ለውጥ ላያመጡ ይችላሉ፡፡ በሕክምና ወይም በሌሎች ረቂቅ አገባብ ላይ ግን ቁብ አላቸው፡፡ ስናድግ ሮኬት ወደ ሰማይ ማምጠቃችን፣ የኒኩለር ፊዚክስ፣ የአንጎል ቀዶ ሕክምና መሥራታችን አይቀር ይሆናል፡፡ እነዚህ ነገሮች በራሳችን ቋንቋ ልናከናውን የምንችልበት ብቃቱን ማዳበር የምንችለው ካሁኑ ነው፡፡

ሌላው ችግር የባዕዳን ቃላት በብዛት የመጠቀማችን ነገር አሳሳቢው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥር ሰዷል፡፡ የባዕዳን ቃላትን ያለመከልከል የመጠቀማችን ነገር ሰነፎች እንድንሆን አደረገን፡፡ የራሳችንን ቃላት እንዳንፈልግና እንዳናዳብራቸው አደረገን፡፡

ስለዚህ በስንፍና ባዕዳን ቃላት ላይ ማተኮር ጀመርን፡፡ ባሁን ዘመን ተስፋፍቶ የሚገኘው እንግሊዝኛ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ፈረንሣይኛና ሌሎች ቋንቋዎች ነበሩ፡፡ ያኔ ያሁኑን ያህል ብርታት አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም ቴክኖሎጂው፣ ግሎባላይዜሽንም አልነበረም፡፡ ትምህርትም ብዙም ተስፋፍቶ ስላልነበር ድሮ ይመጡ የነበሩት ባዕዳን ቃላት ጊዜ ጠብቀው ዓመታትን ፈጅተው ይቀላቀሉ ነበር፡፡ ቋንቋም በቃላት ረገድ በዚያ በኩል ስለሚያድግ ብዙ አስጊ አልነበረም፡፡ አሁን ያለው ግን ቋንቋዎችን ሊደፈጥጥ ሊጨፈልቅ ሰዋስውንም ሊያበላሽ በሚችል መንገድ እየገቡ ነው፡፡ እንደደረስሁበትና መጽሐፌ ላይ እንደጠቀስሁት፣ የኛን ቋንቋዎች ሰዋስው የሚጎዱት የእንግሊዝኛ ግሶች ናቸው፡፡ ስሞችና ቅፅሎችም ጉዳት ያደርሳሉ፣ ግሶች ግን የዐረፍተ ነገሮች መሠረታዊ አካል፣ የዐረፍተ ነገሮችን ቅርፅ (መዋቅር) እና ግንባታ ወሳኝ በመሆናቸው ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

ሪፖርተር፡- ከሥርዓተ ጽሕፈት ጋርስ የሚነሳ ነገር፤

አቶ ልዑል፡- የቋንቋው አጠቃቀም ቀውስ ሌላው ገጽታ ከጽሕፈት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ከዚህ ላይ የማያቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የኛ ፊደል አልፋቤታዊ አለመሆኑ ነው፤ ሲሌቢክ (ቀለማዊ) ነው፡፡ አልፋቤታዊ ተነባቢና አናባቢ ያሉት ፊደል መሆኑ ነው፡፡ የኛ ፊደል ግን ተነባቢና አናባቢው በሆሄያት ውስጥ ተቀላቅለው ስላሉ ስላልተነጣጠሉ አልፋቤታዊ አይደሉም፡፡ ቀለማዊ ፊደል ናቸው፡፡ ለ1,700 ዓመታት ያህል ድንቅ ሥራ የሠራ ሀገራችንን ከሌሎች ሀገሮች ያልተናነሰ የጽሕፈት ባህል ያላት ሀገር ያደረገ ፊደል ነው፡፡ ልንኮራበት ልንመካበት የሚገባ ፊደል ነው፡፡

ነገር ግን አሁን ሌላ ወቅት፣ ሌላ ትውልድ፣ ሌላ ቴክኖሎጂያዊ ፍላጎት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህንን የደረስንበትን የቴክኖሎጂ ዘመን የመግባቢያ ፍላጎት እየጎለበተ ለማሳካት የሚበቃ ዓለማቀፋዊ ብቃት ያለው ፊደል ሊኖረን ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ቀለማዊ ስለሆነ አዲስ ድምፅ በመጣ ቁጥር አዲስ ቀለም መፍጠር ሊኖርብን ሆነ፡፡ ወይም ድምፆች በተለያየ ሁኔታ ሲዋዋጡ ሌላ መልክ ይሰጧቸዋል፡፡ አንዳንድ የተባዙ ቃላትን ተመልክቶ መሠረታዊ ቃሉ የቱ እንደነበረ ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ያ ደግሞ ሌላ የሚያመጣው የስፔሊንግ ወይም የፍደላ ችግርን ነው፡፡ አንዱን ቃል እንዴት ነው የምፈድለው (ስፔል የማደርገው)፣ አንተ ከምትፈድለው የተለየ ሊሆን ይችላል? በአክሰንትም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ቀለሞቹ መሠረታዊ የሆነውን የቃሉን ፊደሎች ስለሚያዛቡ ማለት ነው፡፡

ከሥርዓተ ጽሕፈት ጋር በተያያዘ ሁለተኛው ችግር ያልኩት የሆሄያት አላግባብ የመብዛት ነገር ነው፡፡ በአማርኛ መሠረታዊ እቅፍ ውስጥ ያሉት ሆሄያት 33 ናቸው፡፡ እንደገና ሰባት ዐምዶች አሉ፡፡ ሲባዙ 231 ይሆናሉ፡፡ ቅጥያ እቅፍ ውስጥ ያሉ ሆሄያት ሏ፣ ሟ፣ ሯ፣ ሷ፣… የሚባሉት ሲታከሉበት ቁጥሩ ይጨምራል፡፡ በኦሮምኛና በሌሎች ቋንቋዎች እነሱንና ሌሎች ምልክቶችን ስንደምር ወደ 500 የሚጠጉ ዩኒኮድ ውስጥ የገቡ የኢትዮጵያ ሆሄያት ወይም ቀለማት አሉ፡፡ ፓንኩቴሽን መብዛቱ ችግር የለውም፡፡ ለጽሑፍ የምንጠቀምባቸው መሠረታዊ ሆሄያት ግን መብዛት የለባቸውም፡፡ ትምህርት ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖ አለ፡፡ ልጆች ፊደልን ለማጥናት የሚፈጅባቸውን ጊዜ የሚወስደው አሰልቺና አስቸጋሪ መንገድ ሊወገድ ይገባዋል፡፡

ሌላው የሆሄያቱ መብዛት የሚያስከትለው ችግር መዝገበ ቃላት ውስጥ ቃላትን ስንደረድር ፊደላዊ ቅደም ተከተልን ተከትለው እንዲመጡ ማድረግ አለብን፡፡ ሆሄያቱ ከበዙ ግን ያንን ቅደም ተከተል እንድንስት ያደርጋሉ፡፡ አብዛኛው ሰው ቅደም ተከተሉን አያስታውሰውም፡፡

ሁሉንም ለማስታወስ አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅደም ተከተላችን በቁመት አለ፣ እንደገናም በወርድ አለ፡፡ ሀለሐመሠረሰ ካልን በኋላ እንደገና ሁሂሃሄህሆ፡፡ የበለጠ አስቸጋሪ ያደርጉታል፡፡

ሪፖርተር፡- የሆሄያት መብዛት በተመለከተ አንዳንዶች ‹‹ለአንድ ድምፅ አንድ ምልክት›› የሚል ሥነ ልሳናዊ እይታ የሚያራምዱ አሉ፡፡ አማርኛ የወረሰው የግእዙን የፊደል ገበታ ነው የሚል ነገር አለ፡፡ አማርኛ የሞክሼ ሆሄያት ነባር ድምፅ ጠፍቶበታል፡፡ በሌላ በኩል በአገባብ ላይ ትርጉም ሊያመጣ የሚችል ይኖራል፡፡ ሥርዓተ ጽሕፈትን ለማስተካከል ምን መደረግ አለበት ትላለህ? በመጽሐፍህ የሰጠኸው የመፍትሔ ሐሳብ ምንድን ነው? ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዴሚ ሞክሼዎቹን ሆሄያት አስወግዶ ያዘጋጀው መዝገበ ቃላት አለ፡፡

አቶ ልዑል፡- በአማርኛ ከአንድ በላይ ቀለማት አንድ ድምፅ ወክለው ይገኛሉ፡፡ ወይም ደግሞ ለአንድ ድምፅ ተጠሪ ሆነው ይገኛሉ፡፡ በሌሎች ቋንቋዎች ለምሳሌ በትግርኛና በግእዝ የየራሳቸው አገባብ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ሀሌታው ሀ፣ ሐመሮ ሐ በትግርኛ የተለያየ አገባብ ነው ያላቸው፡፡ ድምፆቻቸውም እንዲሁ የተለያየ ነው፡፡ በግእዝም እንደዚያ እንደነበር መገመት አያዳግትም፣ የታወቀም ነው፡፡ በኋላ ላይ ግን አማርኛ ድምፆቹን እየሳተ፣ ድምፆቹን እያቀራረበ ሄደና የተወሰኑ ቀለሞች አንድ ድምፅ ብቻ እንዲተኩ እየሆኑ ሄዱ፡፡ ለምሳሌ አሌፉን አ እና ክቡን ዐ ብንመለከት በትግርኛ የተለያዩ ድምፆች ነው ያላቸው፤ በግእዝም እንደዛው፡፡ በአማርኛ ግን አንዳይነት ነው፡፡ ሁለቱን ፀ፣ጸ ብንመለከት ትግርኛ አንዱን ከፊደሉ አውጥቶታል፡፡ አማርኛ ግን ሁለቱን አቅፎ በአንድ ድምፅ ይዟል፡፡ ስለዚህ አሻሚ ናቸው፡፡ ፀሐይን የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መንገድ ነው የሚፈድሉት፡፡ መጽሐፌ ላይ አስፍሬዋለሁ፣ ለፀሐይ ብቻ ዐሥር የተለያዩ የአፈዳደል (ስፔሊንግ) ዓይነቶች አሉ፡፡ ይኸ ለዕድገት ጠቃሚ አይደለም፡፡ ሥርወ ቃላዊ (ኢቶሞሎጂካል) የሆኑ የቃላት መሠረት ተከትለህ ‹‹ዓይን›› የትኛውን እንደምትከተል ‹‹አሥር›› ወይም ‹‹አንድ›› ለሚለው የትኛውን እንደምትጠቀም ወደ ግእዙ ሄዶ መመልከትና ርሱን አስታከን እንምጣ የሚለውን ነገር መጠቀም ይቻል ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ምሁራን ሐሳቡን አቅርበው ተሞክሯል፡፡ ውጤቱ ግን እንደዚያ ሊሆን አልቻለም፡፡

አማርኛ ድምፆቹን አስቀድሞ ስለረሳቸው የአፈዳደል ችግር እንዲፈጠርብን አድርጓል፡፡ ቃላቱን በመዝገበ ቃላቱ በአግባቡ ካልደረደርናቸው አንድ ሰው ቋንቋን ለመማርም ሆነ ቋንቋን ለማሳደግ የተቀመጠ ነገር ላይኖረን ማለት ነው፡፡

የማቀርበው የመፍትሔ ሐሳብ እነኚህ ሆሄያት በመብዛታቸው ምክንያት የተፈጠረብን ችግር እጅግ ብዙ በመሆኑ ከዚህ በፊት ኢቶሞሎጂካሊ የሆነ ዓይነት ድምፅ የነበራቸውን ቀለማት ችላ ብለን አንድ ዓይነት ሆሄ ብቻ ስለሰጠናቸው የሚመጣው ችግር ብዙ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ ቃላቱ የሆሄያትን ብዛት ቀንሰን በአግባቡ ያሉንን ብንጠቀም የሚመጣው ጥቅም እጅግ በጣም የበዛ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ሰዋስውን (ግራመርን) በተመለከተስ ያነሳኸው ነጥብ አለ? በዘመናችን እንደ ክፍተት የሚነሳው የአማርኛ ሰዋስው እንደቀደመው ጊዜ እምብዛም ትኩረት እንዳላገኘ ይነገራልና፡፡

አቶ ልዑል፡- ስለሰዋስው በመጠኑ ጠቅሼያለሁ፡፡ የሚቀጥለው መጽሐፌ ግን ሙሉ በሙሉ ስለሰዋስው የምገልጽ ይሆናል፡፡ ሰዋስው ለአንድ ቋንቋ መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ የመግባቢያ ደንብ የቋንቋን ሕግጋት ይዟል፡፡ ለሒሳብ ሕግጋት እንዳሉት ሁሉ ለቋንቋም አሉት፡፡ ታሪካችን ቋንቋችን ብለን ለመኩራራት ሳይሆን የሰዋስው ሕግጋት እኛን እንድግባባ መሠረት ስለሚሆኑን ነው፡፡ እኔ የምረዳው የሰዋስው ሕግ ተጠቅመህ አንተ ስታናግረኝ ሐሳብህ ምን እንደሆነ ያለጥርጥር እረዳሃለሁ፡፡

ሰዋስውን መማር ተገቢ የሚሆነው ስለዚህ ነው፡፡ በዓመታት ውስጥ ለውጥ እንደሚኖርም ይታወቃል፡፡ ለውጥ ሲከሰት በከተማና በገጠር፣ ወይም በተማረውና ባልተማረው፣ በውጭ አገርና በአገር ውስጥ ባለው መካከል መግባባት ላይኖር ፍትሕ ሊጠፋ ነው ማለት ነው፡፡ መልካም አስተዳደር ከቋንቋ ጋር የተያያዘ ነገር እንዳለው በመጽሐፌ ውስጥ አበክሬ ጠቅሻለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በቋንቋ ውስጥ መዋዋስ ያለ ነገር ነው፡፡ እንግሊዝኛ ከላቲን ይወሰዳል፣ አማርኛም ከግእዝ እንዲሁ፡፡ ለክብረትም ለክብደትም ተብሎ የሚወሰዱ ቃላት አሉ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ‹‹ሳይቸግር ጤፍ ብድር›› ሆኖ ገላጭ ቃላት እያሉ ባዕድ ቃላት እየገቡ ነው፡፡ ለምሳሌ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዳይሬክቶሬት፣ ዳይሬክተር ጄኔራል፣ ትራንስፎርሜሽን ወዘተ እየታዩ ነው፡፡ መምሪያ፣ ዋና ዳይሬክተር፣ ውላጤ ማለት እየተቻለ በመዝገበ ቃላቱ ውስጥም ኖረው አገልግሎት እየሰጡ እያሉ መጠቀም አልተፈለገም፡፡

አቶ ልዑል፡- ለአንዳንድ ቃላት አቻ ስያሜ መፍጠር ይቻል ነበር፡፡ የትምህርት ቤት ዳይሬክተርን ርዕሰ መምህር ተብሎ እንደተጠራው ማለት ነው፡፡ ጥሩ ቃል ነው፡፡ የውጭ ቃላትን በመፍቀዳችን ምክንያት ችግር መጥቷል፡፡ አንዴ የከፈትከው በር መልሰህ ለመዝጋት በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ ቋንቋው እንዲበከል በማድረጋችን ሰዎች ለተራ ቃላት እንኳ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ሳጥን፣ መኪና፣ ሕንፃ፣ እናት፣ አባት እንግሊዝኛ መጠቀም ጀመሩ፡፡ አንዳንዴ ግለሰቦችን መውቀስ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ በአፄ ኃይለሥላሴ ቀዳሚ ዘመን ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ በእንግሊዝኛ መስጠት የተጀመረው በወቅቱ ብቁ የሆኑ መምህራን ባለመኖራቸው ከእንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ሕንድ መጥተው ያስተምሩ ስለነበር ነው፡፡

እኛ በቅኝ ሳንገዛ ኖረን አሁን ብዙ የተማረ ኃይል ኖሮ እንዴት በውጭ ቋንቋ ብቻ ትምህርቱ ይሰጣል? ያኔ የነበረው የመምህራን እጥረት አሁን የለም፡፡ በእንግሊዝኛ እስከ 21ኛው ክፍል ዘመን ዕውቀትን ትምህርትን ለምን እናስተላልፋለን፡፡ ባንድ በኩል ስናየው መንግሥት የቋንቋ አጠቃቀም ላይ የተዛባ ፖሊሲ ስላለው የመጣ ነገር ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት እንግሊዝኛ የመማርያ ቋንቋ እንዳይሆን ባለሙያዎች በወቅቱ መክረው ነበር፡፡ በደርግ ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ተቋቁሞ የነበረ አንድ የጥናት ቡድን እንግሊዝኛው ቀርቶ በአማርኛ እንዲሆን ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ [በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ዓመት የፍልስፍና ትምህርት በአማርኛ ለአንድ ዓመት ተሰጥቶ ነበር] በወቅቱ ጦርነትና ረሀብ የተለያየ ችግርም ስለነበረ አርቀን ማሰብ አልቻልንም፡፡ የአስተሳሰብ እጥረት ነው፡፡ ማንም ሀገር በባዕድ ቋንቋ ተጠቅማ ያደገች የለችም፡፡ ቻይና፣ ጃፓን፣ ኮሪያ፣ እስራኤል በራሳቸው ቋንቋ የበለጸጉ ናቸው፡፡ ከየት በመጣ ሞዴል ነው በተውሶ ቋንቋ እየተንገዳገድን የምንማረው? ይህ ክስተት ያመጣው ከእነዚህ ተቋማት የወጡ ምሁራን ሳይማር ያስተማራቸውን ገበሬውንም ሌላውን ኅብረተሰብ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መለማመጃ ያደርጉታል፡፡ ኅብረተሰቡ ምን እየተናገሩ እንደሆነ ላይገነዘብ ይችላል፡፡ እንደ ሕዝብ ልናፍር ይገባል፡፡ ባለሥልጣናት ያለመከልከል የእንግሊዝኛ ቃላትን እየቀላቀሉ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ ይህ የመልካም አስተዳደር እጥረት፣ ጉድለት ነው፡፡ ኢፍትሐዊ ነው ብዬ የማምነው፡፡ መንግሥት በዓዋጅ ደረጃ የአገሪቱ መማሪያ ቋንቋ ማስተካከል ይገባዋል፡፡

በሌላ በኩል ማስታወቂያዎች በጣም በሚገርም ሁኔታ በውጭ ቋንቋ ተወረዋል፡፡ ከአገሬ ከመውጣቴ በፊት አብዛኞቹ በየመንገዱ የሚለጠፉም ሆነ በጽሑፍ የሚሠራጩት ባብዛኛው በአገር ቋንቋ ነበር፡፡ አሁን ግን አንዳንዱ እንዲያውም የአገር ቋንቋ ፈጽሞ የሌለባቸው ማስታወቂያዎችም ተመልክቻለሁ፡፡ በጣም ነው የማዝነው፤ በዓዋጅ የቋንቋ ፖሊሲ አውጥቶ ማስገደድ አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- የመጽሐፉ ተደራሽነት ለማን ነው? በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ በካናዳ ነው የታተመው፤ በአማርኛስ አዘጋጅተኸዋል?

አቶ ልዑል፡- ተደራሽነቱ ለመንግሥት ሰዎች ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለከታቸው አካላት ነው፡፡ ፊደልን ያለአዋጅ ሕዳሴ ማድረግ አይቻልም፡፡ ምሁራንም ሊተቹበት ይገባል፡፡ በአማርኛ ያልጻፍኩት በስንፍና በቸልታ ምክንያት አይደለም፡፡ የተለያዩ ምክንያቶች ነበሩ፡፡ አንደኛው እንዲታደስ ሐሳብ የማቀርብበት ቋንቋ ራሱና ሥርዓተ ጽሑፉን ተጠቅሜ መጽሐፍ ብጽፍ ለማስረዳት እጅግ አድካሚ ይሆናል፡፡

ሌላ እንደምንም ተቸግሬ ልጻፍ ብል የሚመጣው ችግር ቴክኒካዊ ቃላትን በምን ልተካቸው እችላለሁ? በዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተሠሩትን አላየኋቸውም፤ አቻ ቃላትን ለማምጣት የራሴን ትርጉም ከሰጠሁት ሌሎች ላይረዱ ይችላሉ፡፡ መጀመሪያ ትኩረት መስጠት የምፈልገው የቋንቋ ሕዳሴና የፊደላቱ ሕዳሴ ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ ቃላት የምፈጥር ከሆነ ሰዎች ስለማይገነዘቡት ለነርሱ ለማስረዳት ሌላ ጣጣ ውስጥ መግባት ይሆናል፡፡ እነኚህ የመሰሉ ምክንያቶች አስገደዱኝ፡፡ በውጭ ዓለሙ የመታተሙ ነገር ነዋሪነቴ እዚያ በመሆኑ ነው፤ መንግሥት ግን የተወሰኑ መጻሕፍትን ገዝቶ በተለያዩ ቤተ መጻሕፍት በማስገባት ለተጠቃሚዎች ለአንባቢዎች መድረስ ይችላል፡፡ አነስተኛ ወጪ አውጥቶም ኅብረተሰቡ በሚገባው መልኩ ማስተርጐም ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ የራሷ አኀዝ (ቁጥር) አላት፤ ግን እምብዛም አይታወቅም፡፡ መጻሕፍት ሲታተሙ ከዋናው ገጽ በፊት ያሉት ገጾች ለማመልከት ከግእዝ ቂጥር ይልቅ የሮማን ቁጥር ይጠቀማሉ፡፡ ከዚህስ አንፃር የምትለው ምንድን ነው?

አቶ ልዑል፡- የቁጥር ምልክቶቻችንን አለማወቅ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ እንዲያውም በኢትዮጵያ የቋንቋ አጠቃቀም ቀውስ ስለመኖሩ ከሚያሳየን ነገር አንዱ የቁጥራችን ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው የሮማን ቁጥርን ተጠቅሞ Ⅲ አሳይቶ፣ የግእዙን ፫ ላያሳይ መፍቀዱ ከአዕምሮዬ በላይ ልገነዘበው በፍጹም አልችልም፡፡ ኢንዶ አረቢክ የሚባለው ከ0 እስከ 9 ያለው የቁጥር ምልክት ዓለማቀፋዊ መግባቢያ ሆኗል፡፡ ስሌትን ያለነርሱ መሥራት አይቻልም፡፡ የሮማንም ሆነ የግእዝ ቁጥሮች ለረቀቀ የዴሲማል ሒሳብ ሊሆኑ እንደማይቻል ይታወቃል፡፡

ነገር ግን ታሪካዊ የሆኑ የሮማን ቁጥሮችን ለመጠቀም በሚያስችል አቻ መልክ ላሉ ቦታዎች ሁሉ የራሳችንን የግእዝ ቁጥሮች መጠቀም የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ የግእዝ ቁጥሮችን ልንጠቀምበት የሚገባው ቦታ የመኪና ታርጋዎች ላይ ነው፡፡ እዚያ መደመር መቀነስ የለም፡፡ ቋሚ ነገር ሰለሆኑ ኅብረተሰቡም ሊያጠናቸው ይችላል፡፡ የመንገድ አመልካችና የቤት ቁጥሮችም ላይም መጠቀም ይገባል፡፡

ችግሩ የግለሰቦች ድክመት አይደለም፡፡ የመንግሥት ድክመት ነው የቋንቋ ራዕይ ስለሌለን ነው፡፡ ግለሰብ እስከተወሰነ ድረስ ነው የሚጥረው፤ ከዚያ በኋላ ይደክማል፡፡ ችግሩ መቀረፍ ያለበት ከሥርዓተ ትምህርቱ ጀምሮ ነው፡፡ እነዚህ ያገራችን ቁጥሮች በትምህርት ቤት ይሰጣሉ ወይ? መታየት አለበት፡፡ የመማርያ ቋንቋ በእንግሊዝኛ እስካደረግን ድረስ ከግድግዳ ጋር እንደመጣላት ነው፡፡ የመማርያ ቋንቋ ቢያንስ ቢያንስ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ በአማርኛ መሰጠት አለበት፡፡ ክልሎች የራሳቸው ቋንቋ እንዳላቸው እናውቃለን፡፡ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋ አማርኛ ስለሆነ እስከተወሰነ ድረስ መሰጠት አለበት፡፡

ሪፖርተር፡- ቋንቋና ፊደል በተመለከተ መነገር አለበት የምትለው ለየት ያለ ሐሳብ ምንድን ነው?

አቶ ልዑል፡- የቋንቋን ሕዳሴ አስመልክቶ የተለያዩ አገሮች በተለያዩ ዘመኖችና ትውልዶች የቋንቋን ሕዳሴ አድርገዋል፡፡ እኛም ራሳችን ከዚህ በፊት አድርገን ነበር፡፡ በመጽሐፌ ላይ እንደጠቀስኩት በንጉሥ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ፊደላችን የመጀመሪያው የግእዙ ዐምድ ብቻ ሆይ፣ ሎይ፣ ሐውት፣ ማይ፣ ዛት… ነበር፡፡ በኋላ በዒዛና ከካዕብ እስክ ሳብዕ ዐምዶች ተጨመሩ፡፡ እና ትልቁ የፊደል ሕዳሴ የተደረገው በንጉሥ ዒዛና ዘመን ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ በተለያዩ ዘመናት አነስተኛ ሕዳሴዎችም ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ ግእዙን እንደ ቋንቋ መጠቀም ካቆምንና አማርኛ ብሔራዊ ቋንቋ መሆን ከጀመረ በኋላ፣ ከኩሽ ቋንቋዎች ከኦሮምኛ፣ አገውኛ የገቡ ድምፆች ነበሩ፡፡ እንደነጨ፣ ጀ እና ቨ ገብተዋል፡፡ ይኼ የአሁኑ መጽሐፌ የዚያ ተከታይ ነው፡፡ ቱርክ የቋንቋና የፊደላት ሕዳሴ ነበር ያደረገችው፡፡ ብዙ አገሮች የፊደል ሕዳሴ የአንድ ያፈዳደል (ስፔሊንግ) ወይም የአንድ ሆሄ ሕዳሴ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ላስተላልፍ የምፈልገው መልዕክት ይህ ትውልድ መስዋዕትነት ከፍሎ ለሚቀጥለው ትውልድ የተለየች ኢትዮጵያን ይፈጥር ዘንድ አሁን የጀመርነውን ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ ዕድገት በበለፀገ መንገድ ይቀጥል ዘንድ ማስቻል አለብን፡፡ እስካሁን ያሉት የረቀቀ የቋንቋ መግባቢያ መንገድን አልጠየቁንም፡፡ ከአሁን በኋላ የሚመጡት የረቀቀ የመግባቢያ ቋንቋ መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ የኒኩለርና ሌሎች ሥራዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህንና ሌሎችን ለማድረግ መሠረቱን ካሁኑ መጣል አለብን፡፡ አባቶቻችን ከራቀው የጥንት ዘመን ተነስቶ፣ ከቅርቡም ከአፄ ምኒልክ ጊዜ ጀምሮ የቋንቋ አጠቃቀማችን ለማደስ ብዙ ደክመዋል፡፡ እኛም በዚህ ትውልድ ስኬታማ እንዲሆን ሁላችንም የተቻለንን እናድርግ፡፡            

Standard (Image)

የንግድ ሥራን በዕውቀት ለማስመራት የቆመው ማኅበር

$
0
0

በ1940ዎቹ በአብዛኛው በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት ዓረቦች በተለይም የመኖች መሆናቸው ይወሳል፡፡ ቅድመ አብዮት በነበሩት ዓመታት ውስጥ ችርቻሮ የሚፈጸምባቸው ቦታዎች ‹‹ዓረብ ቤት›› (ሱቅ) በመባል ይታወቁ የነበሩት፣ ነጋዴዎቹ ዓረቦች ስለነበሩ ነው፡፡ በኋላ ላይ ኢትዮጵያውያኑ በብዛት ንግድ ውስጥ ቢገቡም የንግድ ሥርዓቱን እምብዛም የማያውቁ ይገኙ በነበረበት አጋጣሚ ነው፣ በ1942 ዓ.ም. በያኔ አጠራሩ ‹‹የንግድ ሥራ ወጣቶች ማኅበር›› የአሁኑ የንግድ ሥራ ትምህርት ምሩቃን ማኅበር የተቋቋመው፡፡ በአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ትምህርት ቤት (የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ሥራ ኮሌጅ) የ1941 ዓ.ም. 12 ምሩቃን የተመሠረተው ማኅበር፣ በቀዳሚነት ባቋቋመው የንግድ ሥራ የማታ ትምህርት የመርካቶ ነጋዴዎችንና ስለ ንግድ ሥራ ትምህርት ፍላጎቱ ያላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞች ተከታታይ ትምህርት በየዓመቱ በመስጠት አስመርቋል፡፡ ከሦስት ዓመታት በኋላ 70 ዓመት በሚሞላው ማኅበር ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ የንግድ ሥራ ኮሌጁ የቀድሞ ተማሪና የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሆነው እያገለገሉ የሚገኙትን ወ/ሮ ፋንታዬ ሸዋዬን ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ማኅበሩ መቼና እንዴት እንደተቋቋመ ቢያስረዱን?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ማኅበሩ የተቋቋመው በ1942 ዓ.ም. ነው፡፡ ያቋቋሙትም በ1941 ዓ.ም. የተመረቁ 12 አባቶች ናቸው፡፡ ሊያቋቁሙት የቻሉበትም ከአዲስ አበባና ከየክልሉ መጥተው ለሁለት ዓመት የተማሩት በአዳሪነት ስለሆነ ከተመረቁ በኋላ እንዳይበታተኑ በማሰብ ሁልጊዜ ሊያገናኛቸው የሚችል አንድ ማኅበር እናቋቁም ከሚል ሐሳብ በመነሳት ነው፡፡ ይህንንም ሐሳባቸውን በወቅቱ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለነበሩት ለዶ/ር ዊልያም ናጊብ አማከሯቸው፡፡ ዳይሬክተሩም ማኅበር ካቋቋማችሁ ሰፋ ባለ መልኩ ፕሮፌሽናል የምሩቃን ማኅበር አድርጉት፡፡ ወደፊትም ትምህርት ቤቱ እየሰፋ ስለሚሄድ የቀሩት ምሩቃን በወጡ ቁጥር ሊቀላቀሏችሁ ይችላሉ የሚል ሐሳብ ይመክሯቸዋል፡፡ ዶ/ር ዊልያም በዚሁ ሐሳብ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተነጋገሩበትና ከሚኒስቴሩም ዕውቅና ተችሮት ‹‹የንግድ ሥራ ወጣቶች ማኅበር›› በሚል ስያሜ ተቋቋመ፡፡ ቢሮውንም በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከፈተ፡፡ ማኅበሩ በዚህ ስያሜ ሊጠራ የቻለው መሥራቾቹ በወቅቱ ወጣቶች ስለነበሩ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የንግድ ሥራ ወጣቶች ማኅበር ዓላማው ምን ነበር? ዓላማውን ለማሳካት ምን ዓይነት አካሄድ ያራምድ ነበር?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-በዛን ዘመን በአገራችን የንግድ ሥራ ትምህርት ብዙም አይታወቅም፡፡  ንግድ ሲባል እንደችርቻሮ ብቻ ነበር የሚታየው፡፡ ይህንን የችርቻሮ ሥራ ደግሞ ብዙም የአገር ልጆች ስለማይሠሩት ከየመን በመጡ ዓረቦች ብቻ ነበር ይካሄድ የነበረው፡፡ ይህም ሆኖ ግን ኢትዮጵያውያን እያደር በሥራው መሳተፍ ጀመሩ፡፡ ይህም ሆኖ ግን የንግዱን ሥርዓት አያውቁትም ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የማኅበሩ መሥራቾች የንግድ ሥራ ትምህርት በኢትዮጵያውያን ዘንድ አይታወቅም፡፡ ስለሆነም በጣም ጠቃሚ ትምህርት መሆኑን ለኅብረተሰቡ ማሳወቅ አለብን ከሚል ተነስተው ነው የማኅበሩን ዓላማ የነደፉት፡፡ በዚህም የተነሳ መሥራቾቹ መርካቶ እየሄዱ ለኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች የመዝገብና የሒሳብ አያያዝ፣ ታክስ እንዴት እንደሚቀመጥ፣ ኪሳራና ትርፍ ምን እንደሆነ ወዘተ የሚያስረዳ ትምህርት በነፃ ይሰጡ ነበር፡፡ ትልልቅ ሱቅ ያላቸውና ነቃ ያሉ ነጋዴዎች ‹‹እኛ እኮ አሁን ትምህርት ቢኖር ኖሮ እንማር ነበር፡፡ ቀን እንዳንማር ንግዳችንን ያስተጓጉላል›› የሚል ሐሳብ መሰንዘር ጀመሩ፡፡ መሥራቾችና  አባላቱም ነጋዴዎችን ማታ ማታ እንድናስተምር ክፍል ይፈቀድልን ሲሉ ትምህርት ቤቱን ጠየቁት፡፡ ትምህርት ቤቱም ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ፈቀደላቸው፡፡

ሪፖርተር፡-ትምህርቱ እየሰፋ ከመጣ የመምህራን ችግር አላጋጠመም?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-በአስተማሪነት የተመደቡት ፈቃደኛ የሆኑ የማኅበሩ አባላትና የትምህርት ቤቱ መምህራን ናቸው፡፡ አባላቱ ከክፍያ ነፃ በሆነ መንገድ ነው ሲያስተምሩ የነበሩት፡፡ ለመምህራኑ  ግን መጠነኛ የሆነ ክፍያ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ሥራ የማታ ትምህርት ማስተማር የጀመሩት የማኅበሩ አባላት ናቸው፡፡ የማታው ትምህርት ብዙ ፈላጊ እያገኘና እየታወቀ መጣ፡፡ በዚህም የተነሳ ሥርዓተ ትምህርቱ ሰፋ ብሎ ቢካሄድ ብዙ ሰው ይጠቀማል በሚል የተነሳ የማታውን ትምህርት ትምህርት ቤቱ ወሰደው፡፡ ይህም የሆነው ከማኅበሩ መሥራቾችና አባላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገበትና ከስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በዚህ ዓይነቱ አካሄድ ምሩቃኑ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በተጨባጭ ቢገለጽ ምን ይመስላል?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ምሩቃኑ የማታ ትምህርቱን የጀመሩት በ1950ዎቹ የነበረውን የንግድ ሥራ ባለሙያ ዕጥረት በማጤን ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በሥራ ላይ የነበሩ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎቻችን በጽሕፈት ሥራ ሙያ፣ በቢሮ አስተዳደር፣ በሒሳብ መዝገብ አያያዝ ወዘተ አሠልጥነውና አስመርቀው በወቅቱ የነበረውን የባለሙያዎች ክፍተት እንዲቀረፍ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የማታው ትምህርት በትምህርት ቤቱ ሥር ከሆነ በኋላ በማኅበሩ አባላት መካከል ክፍተት አልፈጠረም?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ትንሽ ክፍተት ተፈጥሯል፡፡ የትስ እንስባስባለን? ለምን ራሳችንን አንችልም? የሚል ጥያቄ በወቅቱ በነበሩት አባላት ዘንድ ተፈጠረ፡፡ በዚህም የተነሳ ከግል ኪሳቸው እያወጡ ትንሽ ገንዘብ ካጠረቃቀሙ በኋላ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት አካባቢ የማኅበሩ ክበብ አሁን ያለበትን 4,800 ካሬ ሜትር የሆነ ቦታ በ1954 ዓ.ም. ገዙ ገንዘቡን ከየትም ከየትም አጠረቃቅመውና ከራሳቸውም ኪስ ጨምረው በአሁን ጊዜ ያለውን የማኅበሩን አዳራሽ ሠሩ፡፡ የአዳራሹን ግንባታ በጀመሩበት ወቅት ግን የገንዘብ ድጋፍ ፍለጋ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘንድ ቀረቡ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም በጉዳዩ በጣም ተደስተው፣ አባላቱንም አበረታተው ለአዳራሹ ግንባታ የሚውል በግላቸው ወደ 35 ሺሕ ብር ለግሰዋል፡፡

ሪፖርተር፡-ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን ለአዳራሹ ግንባታ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል ይባላል፡፡ በዚህ ዙሪያ ቢያብራሩልን?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን የትምህርት ቤቱ ምሩቅ ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ የድራማ ክበብ ውስጥ ሆኖ ‹‹የእሾህ አክሊል›› በሚል ስያሜ የደረሰው ድርሰት ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎች፣ እንዲሁም በብሔራዊ (ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ቴአትር ለሕዝብ አቅርቦ ከፍተኛ ዝናን አትርፏል፡፡ በብሔራዊ ቴአትር በታየበት ወቅት የተገኘውን ገቢ በሙሉ ለአዳራሹ መሥሪያ እንዲውል አበርክቷል፡፡

    የአዳራሹ ግንባታ ተጠናቅቆ የተመረቀው በ1964 ዓ.ም. ሲሆን መርቀው የከፈቱትም አፄ ኃይለ ሥላሴ ናቸው፡፡ በሥነ ሥርዓቱም ላይ ባደረጉት ንግግር ‹‹ይህ ቤት በጽኑ ፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው›› በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህንንም አነጋገር እስከዛሬ ድረስ እንደ መመሪያችን አድርገን  እየተጠቀምንበት ነው፡፡ በቀድሞው ሥርዓት አዳራሹ ለመሠረተ ትምህርት አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ አሁንም ቢሆን የወረዳው አስተዳደር ስብሳባ ሲያደርግና አንዳንድ ዝግጅት ሲኖረው በነፃ ይገለገልበታል፡፡ ማኅበሩን ይህን ሊፈቅድ የቻለው የኅብረተሰቡ አንጡራ ሀብት ነው ከሚል በጎ አስተሳሰብ ነው፡፡

ሪፖርተር፡-ማኅበሩ በገዛው በተለይ የሠራው አዳራሹን ብቻ ነው? ወይስ ሌሎች መገልገያዎች አሉት?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-አዳራሹ ሁለገብ ነው፡፡ የካፍቴሪያና ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ወጪዎች ያሉት ሲሆን ለስብሰባም ያገለግላል፡፡ ሦስት ቴኒስ ሜዳዎችና በተሟላ የመገልገያ መሣሪያ የተደራጀ ጅምናዚየም፣ ቢሮና የኢንተርኔት አገልግሎት አሉት፡፡ በስተጀርባውም ባለ አንድ ፎቅ ቤትም አለው፡፡ በቅርቡም የመረብና የቅርጫት ኳስ ሜዳዎችን ለማሠራት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡

ሪፖርተር፡-አሁን ያሉት አባላት በዕድሜ እየገፉና እየደከሙ ሲሄዱ የሚተኳቸውን ወጣቶች ለማሰባሰብ ምን የታሰበ ነገር አለ?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ማኅበሩ እስካሁን ድረስ ከንግድ ሥራ ትምህርት ኮሌጅ ጋር የጠበቀ ቁርኝት አለው፡፡ ስለዚህ ኮሌጁ ወጣቶች ከማኅበሩ ጋር እንዲተዋወቁና እንዲቀላቀሉ ለማድረግ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ከሚደረጉትም ጥረቶች መካከል ተማሪዎች ሲመረቁ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ልዩ ልዩ ሽልማት በመስጠት፣ ታዋቂ ሰዎች በአዳራሹ ንግግር ሲያደርጉ መጥተው ልምድ እንዲቀስሙ በማድረግ ወጣቶችን እያሰብን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የማኅበሩ ስም የንግድ ሥራ ወጣቶች ማኅበር ከሚለው ወደ ‹‹ንግድ ሥራ ትምህርት ምሩቃን ማኅበር›› ተቀይሯል፡፡ መቀየሩ ለምን አስፈለገ?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ድሮ የንግድ ሥራ ምሩቃን የምንለው ከኮሜርስ የወጡትን ብቻ ነበር፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ብቸኛ የሙያ ትምህርት ቤት ስለነበረ ነው፡፡ አሁን ግን ትምህርቱ በየዩኒቨርሲቲው ተስፋፍቷል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ቢዝነስ ነክ በሆነ ሙያ ወይም በማኔጅመንት የተማሩና አንድ ዓይነት ባክግራውንድ (ዳራ) ያላቸው በጋራ የሚወያዩበት መድረክ ተፈጥሮ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ሁሉ መግባት አለባቸው በሚል የተነሳ የቀድሞ ቀርቶ ወደ ‹‹ንግድ ሥራ ትምህርት ምሩቃን ማኅበር›› ሊቀየር ቻለ፡፡

ሪፖርተር፡-የማኅበሩ የወደፊት ዕቅድ ምንድነው?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ማኅበሩ እስካሁን የሚንቀሳቀሰው በአባላት መዋጮ ነው፡፡ ሌላ ገቢ ማስገኛ እምብዛም የለውም፡፡ ጊዜው በጣም ውድ ነው፡፡ በአባላት መዋጮ ብቻ የትም አይደርስም፡፡ በዚህም የተነሳ ማኅበሩ ትንሽ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝበት ዘዴና ፕሮፌሽናሊዝምን ይዞ የሚጔዝበት መንገድ ይፈልጉለት ከሚል ቀና ሐሳብ በመነሳት ተጨማሪ ገቢ ለማስገኘት የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ለዕቅዱም ዕውን መሆን አምስት አባላትን ያቀፈ አማካሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ በዕቅዱ ላይ ተገቢውን ጥናት ካደረገና ጠቋሚ አቅጣጫን ከቀየሰ በኋላ ለማኅበሩ ቦርድ አቅርቧል፡፡ ለዕቅዱም ዲዛይንና ስትራቴጂክ ፕላን  ተዘጋጅቷል፡፡

ሪፖርተር፡-ዕቅዱ ምን ምን ሥራን ነው ያካተተው?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ ማዕከል ግንባታ፣ የሥልጠና አገልግሎት መክፈትና በአጠቃላይ ገቢውን ማሳመር ነው፡፡ ሥልጠናው በዓመት አራት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን የሚሰጠውም ለቢዝነስ ጀማሪዎች፣ ወይም ቢዝነስ ጀምረው ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ለመሄድ ለተደራጁ ሰዎች ወይም ከትምህርት ቤት ገና የወጡ ወጣቶች በቢዝነስ ዓለም ውስጥ እንዴት አድርገው ሊሳተፉና የትኛውን ኤቲክስ ተከትለው ምን መድረስ እንዳለባቸው ልምድ ካላቸው አባሎቻችን ትምህርት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ከዚህም ሌላ አዳራሹ ለስብሰባ፣ ለዓውደ ጥናት፣ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች በኪራይ መልክ አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡-የማኅበሩ መሥራቾች አሁን በሕይወት አሉ?

ወ/ሮ ፋንታዬ፡-ከመሥራቾቹ መካከል እስካሁን በሕይወት ያሉት አንድ አረጋዊ ብቻ ናቸው፡፡ 93 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ከቤታቸው ጠዋት ወጥተው እዚሁ ሲጫወቱ ውለው ለዓይን ያዝ ሲል ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

 

Standard (Image)

‹‹በአመራር ደረጃ የሚሳተፉ የስፖርት ባለሥልጣናት አስፈላጊው ዕውቀት ያላቸው አይደሉም››

$
0
0

አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ

ዋና ጸሐፊና የካፍ ፕሬዚዳንት አማካሪ

አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ የተወለዱት በአዲስ አበባ ውስጥ በ1927 ዓ.ም. ነበር፡፡ አባታቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ የነበሩ ሲሆን፣ የክለቡን ተጫዋቾች ከትምህርት ቤት ወደ ስታዲየም ይወስዱ ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ ከአባታቸው ጋር የመሆን ዕድል የነበራቸው አቶ ፍቅሩ በኋላ የስፖርት አስተማሪ ሆኑ፡፡ ከዚያም በ1949 ዓ.ም. በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ የመጀመሪያው የስፖርት ጋዜጠኛ ሆኑ፡፡ ከስታዲየም የስፖርት ፕሮግራምችን ማሠራጨት የጀመሩትም እሳቸው ናቸው፡፡ ከዚያም በኢትዮጵያ ሬዲዮ የስፖርት ፕሮግራም ጀመሩ፡፡ በጊዜው ምንም እንኳ ለስፖርት ጽሑፎች የነበረው ፍላጎት ዝቅተኛ የነበረ ቢሆንም፣ ኤዲተሮችን በማሳመን ስፖርት ተኮር የሆኑ የተለያዩ ጽሑፎችን የተለያዩ ጋዜጦች ላይ ይጽፉ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. የ1960 የሮም የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አጋጣሚ የኦሊምፒክ ታሪክን አሳታሙ፡፡ ከዚህ በኋላ ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ወደ ኮንጎ ተልከው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽኖችን መርዳት ጀመሩ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሕዝብ ግንኙነት፣ የቴኒስና የእግር ኳስ ሊግ ዋና ጸሐፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ መርሕ መሠረት በ1960 ዓ.ም. ዳግም ሲደራጅ በዋና ጸሐፊነት ሠርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በ1960 እና በ1968 ዓ.ም. የ6ኛውና 10ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫጨዋታን በማዘጋጀት ረገድ በልዩ ልዩ ኮሚቴዎች አባልነት ብዙ እገዛዎችን አድርገዋል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት አማካሪ የሆኑት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን ከ39ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባኤና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ጋር በተያያዘ ዳዊት ቶሎሳአነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ስለውጭ አገር የጋዜጠኝነት ሙያዎ ይነግሩኛል?

አቶ ፍቅሩ፡- ከኢትዮጵያ ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ ነበር የሄድኩት፡፡ እዚያም ለፍራንስ ፉትቦልና ኢኮፔ ጋዜጦች ሠርቻለሁ፡፡ በኋላ ግን በሁለት ቋንቋዎች እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ይታተም የነበረውን የራሴን ወርኃዊ መጽሔት ‹‹ኮንቲኔንታል ስፖርት›› ጀመርኩ፡፡ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚያሳትመው ኦሊምፒክ ሪቪው ዋና አዘጋጅ ነበርኩ፡፡ ለቢቢሲ፣ ለቪኦኤ፣ ለጀርመን ሬዲዮ እንዲሁም ለፍራንስ ኢንተርናሽናል ሬዲዮ ሠርቻለሁ፡፡ እንግዲህ የጋዜጠኝነት ሙያዬ ይኼን ይመስል ነበር፡፡ መጀመሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ስፖርት ላይ የመጻፍ ፍላጎት አደረብኝ፡፡ በዚህ መልኩ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን፣ እግር ኳስ ጨዋታዎችን፣ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ሊግን ላለፉት 14 እና 15 ዓመታት ዘግቤያለሁ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ በዓለም አቀፉ ስፖርት ትልልቅና ዋና ዋና ውድድሮችን ዘግቤያለሁ ማለት እችላለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- የካፍ ልዑክ በመሆን ከአሥር ዓመታት በላይ ሠርተዋል፡፡ በካፍ የነበረዎ ጊዜ ምን ይመስል ነበር?

አቶ ፍቅሩ፡-በአቶ ይድነቃቸው ተሰማ አማካይነት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በመወከል በካፍ ልዑክ ወይም ኮሚሽነር ነበርኩ፡፡ ከዚያ ደግሞ የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ሆንኩ፡፡ በዚህ የአፍሪካ እግር ኳስ እንዲተዋወቅ ተንቀሳቅሻለሁ፣ በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥም በበጎ ፈቃደኝነት ሠርቻለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- 39ኛውን የካፍ ጠቅላላ ጉባኤ እንዴት ተመለከቱት?

አቶ ፍቅሩ፡- እንደሚታወቀው እንደ ግብፅ፣ ሞሮኮና ፊፋ ያሉ የውጭ ኃይሎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ደግሞ የወቅቱን የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖን አልደገፉም ነበር፡፡ ስለዚህ በቅስቀሳው ወቅት የአፍሪካ አገሮችን ዞረው ነበር፡፡ ሒርዘን አዲስ አርፈው የነበሩት የአፍሪካ ልዑካን አብዛኞቹ በሙስና የተጨማለቁ ነበሩ፡፡ ያው አፍሪካ በሙስና የታወቀች ናት፡፡ ሁሌም ምርጫ ሲኖር ገንዘብ ሲሰጣቸው ድምጻቸውን ይሰጣሉ፡፡ እኔ በጣም የምጠላው ነገር ደግሞ የውጭ ኃይል መሣሪያ፤ መጠቀሚያ መሆንን ነው፡፡ ማርኬቲንግ ኤጀንሲው ለቴሌቪዥን ባለመብትነት የሚያስከፍለው ከፍተኛ ነው በማለት ግብፃውያን እንኳን በካፍ ላይ ተነስተው ነበር፡፡ ይህ የቲቪ ማሠራጨት መብት ያለጨረታ የተሰጠው ለኳታር ኩባንያ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ግብፅ፣ ሞሮኮና ፊፋ ጉዳዩን ከምርጫ ጋር አገናኙት፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደግሞ የራሱን ፍላጎት ለማራመድ ሲል በሌላኛው ቡድን ነበር የቆመው፡፡ ኢትዮጵያ ሁሌም የምትደግፈው በብዙኃን አፍሪካ አገሮች የሚያዝ አቋምን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ምርጫው ፍትሐዊ ነበር ብለው ያስባሉ?

አቶ ፍቅሩ፡- በእውነት ዴሞክራሲያዊ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም በሙስና ድምፅ ማግኘት የተቻለበት ነበርና፡፡ ስለማዳጋስካር፣ ላይቤሪያ፣ ጂቡቲና ሴራሊዮን እግር ኳስ ሰምተህ ታውቃለህ? ስለዚህ በፖለቲካዊ ሁኔታዎች በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ልትተማመን አትችልም፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ በአንድ ላይ አንድን ተወዳዳሪ በመደገፍ ድምፅ ለመስጠት ከስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ በመጨረሻው ሰዓት ግን ግማሽ የሚያህለው አፍሪካ ድምፁን ለሌላኛው ለመስጠት ወሰነ፡፡ ስለዚህ ማንንም መቆጣጠር አትችልም፡፡ ድምፃቸውን የሰጡት ለአንተ እንደሆነ ይነግሩኃል፣ እውነታው ግን በተቃራኒው ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡- አፍሪካ አንድ ተወዳዳሪ ብቻ ሊኖራት የቻለው በምን ምክንያት ነው?

አቶ ፍቅሩ፡- ችግሩ አዲሱን ትውልድ የማሳደግ ሥራ ስለማይሠሩ ነው፡፡ አሁንም በኃላፊነት ላይ ያሉ ብዙ ያረጁ ሰዎች አሉ፡፡ ስለዚህ ምርጫችን ሰፊ አይደለም፡፡ እዚህ የተመረጡት ሰዎች በሙሉ ጥሩ የሚባሉ አይደሉም፡፡

ሪፖርተር፡- የቀድሞውን ካፍ ፕሬዚዳንት ኢሳ ሃያቱን ከአዲሱ ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ ጋር እንዴት ያነፃፅሯቸዋል?

አቶ ፍቅሩ፡- የቀድሞው ፕሬዚዳንት በአካል ብቃት ትምህርት ላይ ልዩ ሥልጠና ያላቸው ናቸው፡፡ በስፖርት ሚኒስቴር ውስጥ ሠርተዋል፡፡ በካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊና ፕሬዚዳንት በመሆንም አገልግለዋል፡፡ የካሜሮን እግር ኳስ ቡድን አፍሪካን በዓለም ዋንጫ እንዲወክል ብቻም ሳይሆን የአፍሪካ ሻምፒዮን እንዲሆንም አስተዋጽኦ ያበረከቱ ናቸው፡፡ ኃላፊነቱን ከአቶ ይድነቃቸው ተሰማ የተቀበሉና የካበተ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ ሁሌም የአፍሪካ ፍላጎትን ሲያስቀድሙ የኖሩ ሰው ናቸው፡፡ በሌላ በኩል አዲሱ ፕሬዚዳንት የማዳጋስካር ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበሩ ናቸው፡፡ እንዲሁ የታጩና በሌሎች ዘመቻ መመረጥ የቻሉ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኢሳ ሃያቱ ለተጨማሪ ጊዜ ማገልገል ይችሉ ነበር፡፡ እየተባለ ስለሚነሳው ቅሬታ አስተያየትዎ ምንድን ነው?

አቶ ፍቅሩ፡- ሚዛናዊ ያልሆኑ መለኪያዎች አሉ፡፡ በአውሮፓ ተቀባይነት ያለው ነገር ለምን በአፍሪካ ተቀባይነት አይኖረውም? ለምሳሌ የሴፕ ብላተርን ጉዳይ ብንመለከት ለመጨረሻ ጊዜ ሲመረጡ 79 ዓመታቸው ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- የካፍን አቅም እንዴት ይገመግሙታል? ስለ ኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽኖችስ ወቅታዊ አቋም ምን ያስባሉ?

አቶ ፍቅሩ፡- በርግጥም ብዙ መሻሻሎች አሉ፡፡ በአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ጊዜ ገንዘብ አልነበረም፡፡ አሁን ግን የቴሌቪዥን ሥርጭት መብት ገቢ ማስገኘት ችሏል፡፡ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ገንዘብ የሚሰጡ ቢሆንም፣ አሁን ፊፋም ካፍም ጥሩ ገቢ ያላቸው ተቋሞች ናቸው፡፡ ስለዚህም ከገንዘብ አንፃር አሁን ያለው ነገር የተሻለ ነው፡፡ ይኼ በመሆኑ እንደ ዳኞች ሥልጠና፣ የአሠልጣኞች ሥልጠናና መሰል ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ይደግፋሉ፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስን ማስተዋወቅ ማሳደግ፣ ከተፈለገ በተለያዩ ቋንቋዎች የኢንተርኔት መረጃዎችን ማንበብ የሚችሉ አሠልጣኞችን ማሠልጠን ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን በዚህ ረገድ የተዘጋጁ መጻሕፍትን ማግኘት የሚቻልባቸው መደብሮች የሉም፡፡ ስለዚህ እንደ እግር ኳስና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያሉ ቤተ መጻሕፍት ሊገነቡ ይገባል፡፡ ስፖርትን የሚያሳድጉና የሚያስተዋውቁ ብዙ ብቁ ባለሙያዎች ያስፈልጉናል፡፡ በማናጀሮች ደረጃ ስለ አትሌቲክስ የሚያውቁ ሰዎች ካሉበት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተለየ መልኩ ብዙዎቹ ፌዴሬሽኖች ብቃታቸው እስከዚህም በሆነ ሰዎች የሚመሩ ናቸው፡፡ ያለ ብቁ ባለሙያዎች ስፖርቱን ማሳደግ አይቻልም፡፡

ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያዊው ይድነቃቸው ተሰማ ለ30 ዓመታት ያህል የካፍ ጥንካሬ የሆኑ ሰው ነበሩ፡፡ ስለ አቶ ይድነቃቸው አሻራ ሊነግሩን ይችላሉ?

አቶ ፍቅሩ፡- እሱ አሠልጣኜ ነበር፡፡ ብዙ ነገር የተማርኩት ከእሱ ነው፡፡ በጣም ጎበዝ የኢትዮጵያም የአፍሪካም ስፖርት አባት የነበረ ነው፡፡ የአፍሪካ ስፖርት ተቋማትን ይደግፍም ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- የእርሶ ዘመንና የአሁኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደረጃ በንፅፅር ይንገሩን?

አቶ ፍቅሩ፡- በእኔ ጊዜ ብዙ ተጫዋቾች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወጡ ነበሩ፡፡ እነ መንግሥቱ ወርቁ፣ አዋድ መሐመድ፣ ፍሥሐ ወልደ አማኑኤልና ሌሎችም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገኙ ነበሩ፡፡ ለኦሜድላ (ፖሊስ) እና ለንብ (አየር ኃይል) ይጫወቱ የነበሩ ልጆች ሁሉ ከትምህርት ቤት የተገኙ ነበሩ፡፡ ትልቅ ተሰጥኦ የነበራቸው ተጫዋቾች ነበሩ፡፡ አሁን ግን በትምህርት ቤት ያለው ስፖርት እንደ ቀድሞው አይደለም፡፡ ትምህርት ቤቶችም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የተመቹ አይደሉም፡፡ ልጆች እንኳ የሚጫወቱት መንገድ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ሳይሟሉ ስፖርት በኢትዮጵያ እያደገ ነው ልንል አንችልም፡፡

ሪፖርተር፡- ታዲያ መፍትሔ የሚሆነው ምንድነው?

አቶ ፍቅሩ፡- የትምህርት ቤት ስፖርትን ማሳደግ ይኖርብናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ ፍላጎትና ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች መንቀሳቀስ የሚያስችላቸውን ቦታ አላገኙም፡፡ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ሜዳዎች ላይ ክፍሎችን እየገነቡ ነው፡፡ እግር ኳስ መጫወቻ፣ ሌሎችንም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማዘውተሪያ ቦታ በትምህርት ቤቶች ሊኖር ይገባል፡፡ በአመራር ደረጃ የሚሳተፉ የስፖርት ባለሥልጣናት አስፈላጊው ዕውቀት ያላቸው አይደሉም፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ለስፖርት ቦታ እንዲመድብ መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ስፖርትን ማዘውተር የሚቻልበት ቦታ ሳይኖር እንዴት ስፖርትን ማሳደግ ይቻላል?

ሪፖርተር፡- ስለኢትዮጵያ እግር ኳስ ደረጃና ምን መደረግ እንዳለበት አስተያየት ይኖርዎታል?

አቶ ፍቅሩ፡- የመጀመሪያው ነገር ስለ እግር ኳስ የሚያውቁ ሰዎችን ማምጣት ነው፡፡ ከዚያ ደግሞ የወጣቶች ውድድሮች ማዘጋጀት ነው፡፡ ከ15 ዓመት በታች፣ ከ17 ዓመት በታችና ከ20 ዓመት በታች፣ እንዲህ ካልሆነ ሄደው ተጫዋቾችን የሚገዙበት ማምረቻ የለም፡፡ ወጣት ተጫዋቾችን መኮትኮት ያስፈልጋል፡፡ ወጣቶችን ዝግጁ ለማድረግ የትምህርት ቤቶች ውድድር ማድረግም ያስፈልጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ቀጣዩ ዕርምጃዎ የሚሆነው ምንድነው?

አቶ ፍቅሩ፡- አሁን ዕድሜዬ ከ80 በላይ ነው፡፡ በቅርቡ ለኅትመት ይበቃሉ ብዬ ተስፋ ያደረግኩባቸው ሁለት መጻሕፍት ላይ እየሠራሁኝ ነው፡፡ ሁሌም ስለኢትዮጵያና አፍሪካ ስፖርት ደረጃ አስባለሁኝ፡፡ በመሠረተ ልማት፣ በቴክኖሎጂና በመሳሰሉት በጣም ወደ ኋላ ቀርተናል፡፡ ስለዚህ ኳሱ እንዲያድግ ሁሉም በሚገባ የሚችለውን ማበርከት ይኖርበታል፡፡ በኢትዮጵያ ሊግ ያሉት ጠንካራ ክለቦች ሦስት ብቻ ናቸው፡፡ ደጋፊዎች ደግሞ እርስ በርስ የሚሰዳደቡ ናቸው፡፡ ይኼ የኢትዮጵያ ባህል ባለመሆኑ በመከባበር አብረን ልንጓዝ ይገባል፡፡   

Standard (Image)
Viewing all 290 articles
Browse latest View live